Saturday, 21 January 2023 20:17

የከተማዋ የትራንስፖርት ታሪፍ ምን ያህል ጨመረ?

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

  የባቡር ታሪፍም ከ4 ብር ወደ 7 ብር ጨምሯል



          በጥር ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ የተደረገውን የዋጋ ማስተካከያ ከግምት ውስጥ በማስገባት የትራንስፖርት ታሪፍ ላይ ማሻሻያ ማድረጉን የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ አስታውቋል፡፡
አዲሱ የታሪፍ ማሻሻያ ከነገ ጀምሮ ተግባራዊ ይደረጋል ተብሏል፡፡
በዚህም መሰረት ለሚኒባስ ታክሲዎች÷ እስከ 2 ነጥብ 5 ኪሎ ሜትር 3 ብር ከ50 የነበረው በተስተካከለው ታሪፍ 4 ብር፣ ከ2 ነጥብ 6 እስከ 5 ኪሎ ሜትር 6 ብር ከ50 የነበረው ታሪፍ በአዲሱ የታሪፍ ማሻሻያ 7 ብር ሆኗል፡፡
በተጨማሪም ከ5 ነጥብ 1 እስከ 7 ነጥብ 5 ኪሎ ሜትር 10 ብር የነበረው ታሪፍ በተመሳሳይ 10 ብር ሆኖ እንዲቀጥል ተወስኗል፡፡
የሃይገርና የቅጥቅጥ ታክሲዎች የታሪፍ ማሻሻያ ደግሞ÷ እስከ 8 ኪሎ ሜትር 5 ብር የነበረው ታሪፍ በነበረው እንዲቀጥል፣ ከ8 ነጥብ 1 እስከ 12 ኪሎ ሜትር 7 ብር ከ50 የነበረው በአዲሱ ማሻሻያ 8 ብር፣ ከ12 ነጥብ 1 እስከ 16 ኪሎ ሜትር 9ብር ከ50 የነበረው ታሪፍ በሚተገበረው ማሻሻያ 10 ብር እንዲሆን ተወስኗል፡፡
በተጨማሪም ከ16 ነጥብ 1 እስከ 20 ኪሎ ሜትር 12 ብር የነበረው ክፍያ በአዲሱ የታሪፍ ማሻሻያ 13 ብር እንዲሁም ከ20 ነጥብ 1 እስከ 24 ኪሎ ሜትር 14 ብር ከ50 የነበረው በአዲሱ የታሪፍ ማሻሻያ 15 ብር፣ ከ24 ነጥብ 1 እስከ 28 ኪሎ ሜትር 17 ብር የነበረው 18 ብር እንዲሆን መወሰኑን የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ አስታውቋል፡፡
ከ7 ነጥብ 6 እስከ 10 ኪሎ ሜትር 13 ብር የነበረው ታሪፍ በማሻሻያው 14 ብር፣ ከ10 ነጥብ 1 እስከ 12 ነጥብ 5 ኪሎ ሜትር 16 ብር ከ50  የነበረው ታሪፍ 17 ብር፣ ከ12 ነጥብ 6 እስከ 15 ኪሎ ሜትር 19 ብር ከ50  የነበረው ታሪፍ 20 ብር ከ50  እንዲሆን ተወስኗል፡፡
ከ15 ነጥብ 1 እስከ 17 ነጥብ 5 ኪሎ ሜትር 23 ብር የነበረው 24 ብር፣ ከ17 ነጥብ 6 እስከ 20 ኪሎ ሜትር 26 ብር ከ50  የነበረው በአዲሱ ማሻሻያ 27 ብር፣ ከ20 ነጥብ 1 እስከ 22 ነጥብ 5 ኪሎ ሜትር 29 ብር ከ50  የነበረው ታሪፍ በማሻሻያው 31 ብር ሆኗል፡፡
እንዲሁም ከ22 ነጥብ 6 እስከ 25ኪሎ ሜትር 33 ብር የነበረው ታሪፍ በማሻሻያው 34 ብር፣ ከ25 ነጥብ 1 እስከ 27 ነጥብ 5 ኪሎ ሜትር 36 ብር የነበረው ታሪፍ 38 ብር፣ ከ27 ነጥብ 6 እስከ 30 ኪሎ ሜትር 39 ብር ከ50 የነበረው ታሪፍ በአዲሱ ማሻሻያ 41 ብር መሆኑ ታውቋል፡፡
በተሻሻለው የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ታሪፍ ደግሞ እስከ 17 ኪሎ ሜትር 4 ብር የነበረው፣ በአዲሱ የታሪፍ ማሻሻያ 7 ብር እንዲሆን ተወስኗል፡፡




Read 2959 times