Saturday, 14 January 2023 10:41

“አሳንቲ” ዛሬ በሐገር ፍቅር ይመረቃል

Written by 
Rate this item
(4 votes)

   የደራሲ  ምርት ባቦ የበኩር ሥራ የሆነው “አሳንቲ “ የተሰኘ የአጫጭር ልብወለዶች መድበል ዛሬ  ቅዳሜ ከጠዋቱ 4 ሰዓት በሐገር ፍቅር ቴአትር ቤት እንደሚመረቅ ተገለጸ፡፡
በ212 ገጾች የተቀነበበው መጽሐፉ፤ አምስት አጫጭር ልብወለድ ታሪኮችን ያካተተ ነው፡፡
 በምርቃት  ፕሮግራሙ ላይ ሥራዎቻቸውን ከሚያቀርቡ  ታዋቂ የሥነጽሁፍ  ባለሙያዎች መካከል  ዶ/ር በድሉ ዋቅጅራ፣ ደራሲ ዘነበ ወላ፣ የህግ ባለሙያው ተክለሚካኤል አበበ፣ ገጣሚ  ሰለሞን ሳህለ፣ ተዋናይ ፍቃዱ ከበደና ሌሎችም ይገኙበታል ተብሏል፡፡
የምርቃት ፕሮግራሙን  ኒው አቢሲኒያ ባንድ በሙዚቃ  እንደሚያደምቀው ታውቋል፡፡

Read 1607 times