Saturday, 10 December 2022 13:25

“የጥበብ ውሎ በሲህን” የኪነ ጥበብ መሰናዶ ዛሬ ይካሄዳል

Written by  ናፍቆት ዩሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

  በመላኩ አምባው የማስታወቂያ ሥራዎችና ኢቨንት ኦርጋናይዘር በየወሩ በደሴ ከተማ የሚካሄደው 8ኛው ዙር “የጥበብ ውሎ በሲሂን” የተሰኘው የኪነ ጥበብ መሰናዶ ዛሬ ታህሳስ 1 ቀን 2015 ዓ.ም ደሴ ከተማ በሚገኘው ወ/ሮ ሲህን የፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ አዳራሽ ከረፋዱ 3፡00 ጀምሮ ይካሄዳል፡፡ ከፖሊ ቴክኒክ ኮሌጁ ጋር በትብብር የሚዘጋጀው ይህ የኪነ ጥበብ መሰናዶ “ንባብን ለአዕምሮ ልማት” በሚል ርዕስ የሚካሄድ ሲሆን በመድረኩ ግጥም፤ ጭውውት፤ መነባንብ፤ ልዩ ተሰጥኦ፤ አነቃቂ ንግግር፤ የወሩ ተሸላሚ እንግዳ፤ የልምድ ልውውጥና ሌሎችም መሰናዶዎች እንደሚቀርቡ አዘጋጁ መላኩ አምባው ለአዲስ አድማስ ገልጿል፡፡ በዚህ ዝግጅት ላይ የ38 መፅሀፍ ደራሲ የሆነው መሀመድ አሊ ብርሃን ተገኝቶ የማነቃቂያ ንግግር ያደርጋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ለማወቅ ተችሏል፡፡


Read 11006 times