ከሽንብራ ዱቄትና ከተለያዩ የምግብ ግብአቶች የሚዘጋጅ ብስኩት መመረት ጀመረ
በአገራችን የመቀንጨር አደጋ 37 በመቶ የደረሰ ምጣኔ ያለው ሲሆን ችግሩ በስፋት የሚታየው ዕድሜያቸው ከአምስት አመት በታች በሆኑ ህጻናት ላይ እንደሆነ ተገለፀ። ይህ የተገለጸው ለህጻናት አካላዊና አዕምሮአዊ ዕድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደርጋል የተባለና ከሽንብራ ዱቄትና ከተለያዩ የምግብ ግብአቶች የሚዘጋጅ ብስኩት መመረት መጀመሩ ይፋ በተደረገበት መርሃግብር ላይ ነው።
መሰረቱን በዴንማርክ ያደረገውና በልማትና እርዳታ ላይ አተኩሮ በአገራችን በአማራ፣ በኦሮሚያ፣ በአፋርና በጋምቤላ ክልሎች ውስጥ በስፋት የሚንቀሳቀሰው “Dan Church Aid (DCA)” ህፃናትና እናቶች ላይ ትኩረት ባደረገውና “Sustianable Food partnership for better Nutrition through inclusive value chain in Ethiopia (SFP)” በተሰኘው ፕሮጀክቱ፣ በሞያ የምግብ ኮምፕሌክስ መመረት የጀመረው ሰኒ ብስኩት፤ ህፃናትን ለመቀንጨር ችግር የሚዳርጋቸውን የተመጣጠነ ምግብ እጥረት ለመቅረፍ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደርጋል ተብሏል።
ይህ ለህጻናት እድገት አስፈላጊ በሆኑ የምግብ ግብዓቶች ተመርቶ የቀረበው ብስኩት፤ በአገራችን በተለይም ችግሩ ባለባቸው አካባቢዎች ላይ በስፋት ለማዳረስ ጥረት እንደሚደረግም በዚሁ ዝግጅት ላይ ተገልጿል።
Published in
ዜና
Latest from Administrator
- የእስራኤል እና የኢራን ፍጥጫ
- Insights on Israel's Response: Interview with Mr. Tomer Bar-Lavi, Chargé d’Affaires at the Embassy of Israel to Ethiopia
- Barr, a vocal Trump critic, says he will ‘support the Republican ticket’ in November
- Iran president warns of ‘massive’ response if Israel launches ‘tiniest invasion’
- "አልሞቷል" ፊልም ዛሬ በዓለም ሲኒማ ይመረቃል