Saturday, 08 October 2022 09:24

የፖለቲከኛው የሺዋስ አሰፋ ልጆች ዛሬ መፅሀፍታቸውን ያስመርቃሉ

Written by  ናፍቆት ዩሴፍ
Rate this item
(2 votes)

 የእውቁ ፖለቲከኛ የሺዋስ አሰፋ ልጆች ዛሬ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ጀምሮ ጊዮን ሆቴል ውስጥ በሚገኘው ግሮቭ ጋርደን ዎክ  መፅሐፋቸውን በድምቀት ያስመርቃሉ፡፡
ከፖለቲከኛ አባታቸውና ከመምህርት እናታቸው የተገኙት ቅዱስ የሺዋስ እና ህሊና የሺዋስ በዛሬው ዕለት ሶስት መፅሀፍትን የሚያስመርቁ ሲሆን ሁለቱ መፅሀፍት የህሊና የሺዋስ አንዱ ደግሞ የቅዱስ የሺዋስ ነው ተብሏል፡፡
ተማሪ ቅዱስ የሺዋስ ከዚህ ቀደም “የአውሮፕላን የበረራ ምስጢሮች” የተሰኘ መፅሀፍ ለንባብ ያበቃና ግርምትን የፈጠረ ሲሆን ዛሬ ደግሞ “The Fundamental of Air Plane Design” የተሰኘውን አስደናቂ መፅሀፍ እንደሚያስመርቅ ተገልጿል። እህቱ ተማሪ ህሊና የሺዋስ ደግሞ “Anatomy and Physiology of The Heart” እና “ስለ ልብ የተነገሩ ምርጥ አባባሎች” የተሰኙ ሁለት መፅሀፍቶችን እንደምታስመርቅ  የምርቃቱ አዘጋጅ ሰምና ወርቅ ሚዲያና ኢንተርቴይመንት  አስታውቋል።
ወላጆች ልጆቻቸውን ይዘው መፅሐፍት ምርቃቱን እንዲታደሙና ከሁለቱ እህትና ወንድም ፀሐፊዎች መነቃቃትን እንዲቀስሙም ጥሪ ቀርቧል። በዕለቱም የልጆች መፅሐፍት ደራሲያን፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የፀሐፊያኑ ቅዱስና ህሊና ጓደኞችና በርካታ እንግዶች እንደሚታደሙ ታውቋል።

Read 31995 times