Saturday, 20 August 2022 13:04

የወጣቶች የስነ ተዋልዶ ጤና ማበልጸግ

Written by  ሀይማኖት ግርማይ ከኢሶግ
Rate this item
(1 Vote)

ኢንጀንደር ኄልዝ የተባለው መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ከሚሰራቸው የተለያዩ ስራዎች አንዱ የወጣቶችን የስነ ተዋልዶ ጤና ማበልጸግ በሚል ፕሮግራም በአዲስ አበባ ከተማ በተለይም በአራዳ ክፍለ ከተማ ላይ እየተተገበረ ያለው ስራ ተጠቃሽ ነው፡፡ በዋናነትም ስምንት ትምህርት ቤቶች ላይ ማለትም ሶስት የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶችና አምስት የመሰናዶ ት/ቤቶች ላይ የሚሰራ ሲሆን ከዚህም በተጨማሪ ሆስፒታሎችን ጨምሮ በዘጠኝ ጤና ጣቢያዎች ላይ ይሰራል፡፡ አቶ ሬጋን መሐመድ በኢንጀንደር ኼልዝ የወጣቶችና የአፍላ ወጣቶች የስነተዋልዶ ጤና ኦፊሰር የሚሰሩት በተለይም ከትምህርት ቤቶች ጋር በትምህርት ሚኒስቴር የተደገፈ ከወጣቶችና ከአፍላ ወጣቶች የተዋልዶ ጤና ጋር በተያያዘ ተግባራዊ እንዲደደረግ ይሁንታን ያገኘ ፕሮጅክት ሲሆን በዚያ ላይ ህይወትን የመምራት፤ የተዋልዶ ጤና፤ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የመሳሰሉትን በውስጡ የያዘ ፕሮራም ነው፡፡  
ይህ ወደተማ ሪዎች እንዲደርስ በመጀመሪያ የአሰልጣኞች ስልጠና በየትምህርት ቤቱ ተሰጥቶአል። የሰለጠኑት መምህራና የጀንደር ክለብ አስተባባሪዎች፤ ክበባትን የሚያስተባብሩ ምክትል ርእሰ መምህራን፤ የባዮሎጂ መምህራን ከዋናው ካሪኩለም ጋር አዛምደው ትምህርቱን እንዲያሰርጹ እና እድሜያቸውን መሰረት አድርጎ ከስነተዋልዶ ጤና ጋር ያለውን ሁኔታ በአግባቡ መረጃ አግኝተው ማንታቸውን በማያበላሽ መልኩ እራሳቸውን ጠቅመው አገራቸውን እና ህዝባቸውን እንዲጠቅሙ የሚያስችል ፕሮጀክት ነው፡፡
ኢንጀንደር ኼልዝ በአዲስ አበባ አራዳ ክፍለ ከተማ ከሚሰራባቸው ስምንት ትምህርት ቤቶች መካከል ከአጼናኦድ፤ ከወ/ሮ ቀለመወርቅ፤ ከዳግማዊ ምኒሊክ እና ጥቁር አንበሳ ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ ተማሪዎች ከመምህራኖቻቸው ጋር በመሆን  ለስልጠና ወደ አዳማ ሄደዋል፡፡ የሚሰለጥኑት ተማሪዎች ሆነው ሳለ አስተማሪዎቻቸው አብረው የተገኙበት ምክንያት ተማሪዎቹ እድሜአቸው ከአስራ ስምንት አመት በታች ስለሆኑ አስተማሪዎቻቸው አብረው መሆን እንዳለባቸው የወላጆችም ጭምር ፍላጎት ስላለበት ነው፡፡ ለስልጠናው የተጋበዙት መምህራኖች እና ተማሪዎች የጀንደር ክበብ አባላት እንዲሁም  የኢትዮጵያ የወጣት መማክርት ካውንስል ስለሆኑ ያገኙት እውቀት ለሌሎችም እንደሚያካፍሉ ጥርጥር የለውም፡፡
አቶ ሬጋን እንደገለጹት በኢንጀንደር ኼልዝ የተጀመረው ይህ ፕሮጀክት እንደ ፕሮግራም የተጀመረው ዲሴምበር 2019 ሲሆን ዲሴምር 2022 ላይ ይጠናቀቃል፡፡ በእርግጥ ስራው ሲያበቃ የደረሰበት ውጤት የሚገመገም ሲሆን ሲጀመርም ለ27 ሰአት ያህል ጊዜ የፈጀ ቅድመ እውቀት የተዳሰሰበት ስራም ነበረው፡፡ በዚህም በፕሮጀክቱ የተያዙትን ቁምነገሮች በሚመለከት የነበራቸው እውቀት ምን ያህል እንደሆነ የታየበት ዳሰሳ ነበረው፡፡ ፕሮጀክቱ በነበረው ቆይታ የታየውን ለውጥ በሚመለከት አቶ ሬጋን እንደገለጹት ….የባዮሎጂ ትምህርት መምህራንን በምናናግርበት ሰአት እና የተሰራውን ዶክመንት መነሻ ስናደርግ የምናገኘው መልስ አንዳንድ ተፈጥሮአዊ የሆኑ አካላትን ስእሎች፤ አካላዊ ለውጦች በውስጡ ስለሚይዝ  ትምህርቱንም ከማገዝ አንጻር አስተዋጽኦ እንዳለው ለመገንዘብ ተችሎአል፡፡ በዚህ ክበብ የሚሳተፉ ተማሪዎች የትምህርት ውጤታቸው ጥሩ መሆኑ እና አላማቸው ላይ እንዲያተኩሩ መደረጉ፤ ሌላው ነገር ላይ እንደርሳለን ብለው ትምህርታቸው ላይ ሙሉ ትኩረታቸውን እንዲያደርጉ መቻሉ ብቁ ዜጋን ከማፍራት አንጻር በጎ ምላሽ አለው፡፡ እኔ የምማረው ለምንድነው፤ ወላጆቼ ከእኔ ምን ፈልገው ነው የሚያስተምሩኝ፤ አገሬስ ከእኔ ምን ትጠብቃለች ለሚሉትና ለመሳሰሉት ጥያቄዎች በቂ መልስ መስጠት የሚችል ወጣትን ለማፍራት የሚያስችል ጎዳና ነው ብለን እናምናለን ብለዋል አቶ ሬጋን፡፡
በአዳማ በነበረው ስልጠና ላይ ከነበሩት ተማሪዎች መካከል ያነጋገርናቸው  አሉ፡፡ ፍሬሕ ይወት ከወጣቶች የመማክርት ካውንስል የተወከለች ነች። እንደፍሬሕይወት እምነት የወጣቶች መማክርት ካውንስሉ የሚፈለግበትን ድርሻ ለመወጣት እንደዚህ ያሉ ስልጠናዎችን መውሰድ ያስፈልገዋል። እንደ ፍሬህይወት እምነት ከስልጠናው በሁዋላ ገና ብዙ ስራ ይጠበ ቅባቸዋል፡፡ ኢንጀንደር ኼልዝ በሚሰራባቸው ስምንት ትምህርት ቤቶች ሁሉ በመድረስ በስልጠናው ያገኙትን ነገር ለአፍላ ወጣቶችና ለወጣቶች ማዳረስ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ኢንጀንደር ኼልዝ የሚሰራባቸው ጤና ጣቢያዎች በዚያው በአራዳ ክፍለ ከተማ የሚገኙ ሲሆን በዚያም ቢሆን መረጃ የሌላቸው ባለሙያዎች መኖራቸው አይካድም። ስለ ጉዳዩ ያለውን ሁኔታ በትምህርት ቢያገኙትም ከወጣቶች ጋር እንዴት እንደሚገናኙ የማያውቁ ይገኙባቸዋል፡፡ ስለዚህም ወደ እነሱም ሄደን ወጣቶችን በደስታና በፈገግታ ነጻ ሆነው በግልጽነት እንዲያወሩአቸው ማስቻል ሌላው ትኩረት የሚሻ ጉዳይ ነው፡፡ ስለሆነም በዚህ ስልጠና ላይ በቆየንባቸው ጊዜያት ስለስነተዋዶ ጤና እና ጾታን መሰረት ያደረገ ጥቃት በሚመለከት ያገኘነውን እውቀት በማካፈል ወጣቶቹ እራሳቸውን በምን መንገድ መጠበቅ እንዳለ ባቸው እናስረዳለን ብላለች ፍሬ ሕይወት፡፡
ሌሎቹ ያነጋገርቸው ወጣቶች የአብስራ እና ብሩክ ከዳግማዊ ምኒሊክና ቀለመወርቅ ትምህርት ቤት ናቸው፡፡ ለመሆኑ የስነተዋልዶ ጤና ሲባል የማን ጉዳይ ነው ለሚለው ጥያቄአችን የሰጡት መልስ ቀደም ሲል ስለችግሩ ምንም ግንዛቤ ያልነበራቸው በመሆኑ በተለያዩ ምክንያቶች ለአደጋ የሚጋለጡት ሴቶች በመሆናቸው የሴቶች ጉይ ነው ብሎ መውሰድ የሚቻልበትን መንገድ ያመላክታል፡፡ በእርግጥ የስነተዋልዶ ጤና ጉዳይ የወንዱም የሴትዋም መሆኑ አይካድም ነበር ያሉን፡፡  ዛሬ በትምህርት ቤቶቻቸው ስላለው የግዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ሲገልጹ በኢንጀንደር ኼልዝ ድጋፍ በምናገኘው እውቀት ተመስርተን በሳምንት አንድ ቀን ፕሮጀክቱ ባለባቸው ትምህርት ቤቶች በስርአተ ጾታ ክበብ አዳራሽ ስልጠናው ይሰጣል ብለዋል የአብስራ እና ብሩክ ፡፡
ከአራዳ ክፍለ ከተማ አጋዝያን ትምህርት ቤት ምክትል ርእሰ መምህር የሆኑት አቶ በላይ ፀጋዬ በአዳማ በስልጠናው ላይ ከነበሩት መካከል ናቸው። እሳቸውም እንደሚሉት በአጠ ቃላይ ከስነተዋልዶ ጤና ጋር በተያያዘ በትምህርት ቤታቸው ብዙ ስራዎች በመሰራት ላይ ናቸው፡፡ ከኢንጀንደር ኼልዝ ፕሮጀክት ጋር ተያይዞ የጤና እና የስርአተ ጾታ ክበብ እንዲ ሁም የኪነ ጥበብ ክበብ የተቋ ቋመ በመሆኑ እነዚህም አብረው ተጣምረው ስራ እንዲሰሩ እየተደረገ ይገኛል። በዚህም መሰረት ወጣቶቹ በተለይም ህይወታቸውን በምን መንገድ መምራት እንደሚገባቸው፤ በራ ሳቸው ጉዳይ ላይ እንዴት መወሰን እንዳለባቸው በሚ መለከቱ ጉዳዮች ላይ ብዙ ስልጠ ናዎች እየተሰጡ ነው፡፡ በዚህ አመትም በአጠቃላይ ወደ ሁለት መቶ ሀምሳ የሚሆኑ ተማሪ ዎችን ማስመረቅ ተችሎአል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በሚኒ ሚድያ አስተማሪ፤ አነቃቂ፤ አዝናኝ የሆኑ ነገሮች ለተማሪዎቹ የሚተላለፉበት አሰራር አለ አቶ በላይ ፀጋዬ የአጋዛያን ትምህርት ቤት ምክትል ርእሰ መምህር እንደጠቀሱት፡፡
ከስነተዋልዶ ጤና ጋር በተያያዘ ሴት አፍላ ወጣቶች እና ወጣቶቹ የሚቸገሩበት አንዱ ነገር የወር አበባ ነው። ይህን በሚመለከት ሴት አፍላ ወጣቶች እና ወጣቶች እራሳቸውን በንጽህና ጠብቀው፤ ከትምህርታቸው ሳይቀሩ፤ ሳይፈሩና ሳይሸማቀቁ በትምህርት ቤታቸው ውለው እንዲሄዱ የሚያስችሉ የተለያዩ ድጋፎች ይደረግላቸዋል፡፡ አቶ በላይ እንደሚሉት የወርአበባ መቀበያ ፓዶችን ከተለያዩ ድርጅቶች በድጋፍ ስለሚያገኙ በነጻ ለተማሪዎች ይሰራጫል። እንዲሁም ከኢንጀንደር ኼልዝ ጋር በመነጋገር በራሳቸው የሚሰሯቸው የመ ቀበያ ፓዶችንም በቀላሉ እንዲጠቀሙ በማድረግ ተማሪዎቹ ካለምንም ችግር የወር አበባ ሂደቱን እንዲያጠናቅቁ አስችሎአል፡፡ ስለሆነም በዚህ ምክንያት ከትምርታቸው ሳይሰናከሉ በትክክል ይከታተላሉ፡፡ በእርግጥ ይህ ስራ እንደተጀመረ አንዳንድ አስቸጋሪ የሆኑ ነገሮች ነበሩት፡፡ ግልጽነት መጉደል፤ ከትምህርታቸው መቅረት፤ የንጽህና መጠበቂያውንም ከሴት አስተማሪዎች ብቻ ለመቀበል ዝግጁ መሆን የመሳሰሉት ነገሮች ይታዩ የነበረ ሲሆን አሁን ግን ያ ሁሉ ተቀርፎ በነጻነትና በግልጽነት ወንድና ሴት ሳይመርጡ ፓድ እፈልጋለሁ የሚለውን ጥያቄ እያቀረቡ እየተስተናገዱ ይገኛሉ ብለዋል አቶ በላይ፡፡
አቶ በላይ እንደሚሉት ይህ ስልጠና የወጣት አማካሪ ካውንስል ቲም አባላትን ያካተተ ነው፡፡ ይህ ቲም በኢንጀንደር ኼልዝ ስር ሆኖ የሚንቀሳቀስ እንዲሁም ከትምህርት ቤት በዘለለ የኢትዮጵያን ወጣቶች ተደራሽ ለማድረግ የሚንቀሳቀስ ቲም ነው፡፡ ስለዚህም የሚሳተፈው መምህርም ይሁን ወጣቱ በትምህርት ቤቱ ብቻ የተገደበ ሳይሆን በአጠቃላይ የኢትዮጵያን ወጣት እንዴት ተደራሽ እናድርግ የሚለው ነገር ላይ የሚያተኩር ነው፡፡ ስለዚህም የአቅም ማጎልበት፤ የህዝብ ግንኙነት የመሳሰሉ ሁሉ አሉ፡፡ ለምሳሌ የህዝብ ግንኙነት የሚባለው ጎዳና ላይ ፕሮራሞችን አዘጋጅቶ ቅስቀሳ ማድረግና ግንዛቤ ማስጨበጥ ስራዎችን ሊሰራ የሚችል ነው፡፡ ስልጠናው ያስፈለገበት ዋናው ምክንያት እኛ እራሳችን ግንዛቤ ሳይኖረን ለሌሎች መልእክት ማስተላለፍ ስለማንችል እና እናስተምራለን ብለን ልናሳስት ስለምንችል በቅድሚያ እንድናውቅ ነው፡፡ስለዚህም እነዚህ የወጣት አማካሪ ካውንስል አባላት በኢትዮጵያ ደረጃም እንዲሁም በትምህርት ቤቶቻቸው ሲሄዱ ለሌሎቹ ወጣቶች ግንዛቤን የማስፋት ስራ እንዲሰሩ ይጠ በቃል ብለዋል ምክትል ርእሰ መምህር በላይ ፀጋዬ፡፡



Read 11246 times