ሱዳን በ245.1 በመቶ የዋጋ ግሽበት ትመራለች አፍሪካን
ከአፍሪካ ሃገራት በወቅታዊ የሸቀጦች የዋጋ ግሽበት ኢትዮጵያ በ3ኛ ደረጃ ላይ የምትገኝ ሲሆን ሱዳን ከአፍሪካ ቀዳሚ ሆናለች፡፡ የአለም ባንክ ከሰሞኑ ያወጣው ሪፖርት እንዳመለከተው፡ በፖለቲካ ሁከትና አለመረጋጋት ውስጥ የምትናጠው ሱዳን፣ በ245.1 በመቶ የሸቀጦች የዋጋ ግሽበት አፍሪካን ትመራለች፡፡
በየጊዜው የሸቀጦች የዋጋ ግሽበት ቀውስ የማንጣት ዚምባብዌ ደግሞ፣ በ86.7 በመቶ የዋጋ ግሽበት በሦስተኛ ደረጃ ላይተቀምጣለች። ኢትዮጵያ በ34.5 በመቶ የዋጋ ግሽበት በሦስተኛ ደረጃ ላይ ስትገኝ፡፡ አንጎላ 23.9 በመቶ፣ ሴራሊዮን 17.3 በመቶ፣ ጋና 16.፣3 በመቶ፣ናይጀሪያ 16.1 በመቶ፣ደቡብ ሱደን 16 በመቶ፣ዘምቢያ 15.7 መቶ በማስመዝገብ እስከ 10ኛ ያለውን ደረጃ ይዘዋል በቅድመ ተከተላው መሰረት፡፡
ከአፍሪካ ሃገራት በጣም ዝቅተኛ የሸቀጦች ዋጋ ግሽበት ያስመዘገቡ አስር ሃራት ደግሞ ደቡብ ሱዳን፣ቤኒን፣ሲሸልሲ፣ ካሜሮን፣ ኤርትራ፣ ማዕከላዊ አፍሪካ ረፐብሊክ ኢኳቶሪያል ጊኒ፣ ጋቦን ስዋዚላንድ እና ቻድ ናቸው፡፡
በኢትዮጵያ ከፍተኛ የሸቀጦች ዋጋ ግሽበት የተመዘገበው በምግብና ምግብ ነክ ቁሳቁሶች እንዲሁም በግንባታ የግብአቶች ላይ መሆኑም ተመልክቷል፡፡
ከፍተኛ የዋጋ ግሽበት ያስመዘገቡ ሃገራት የህዝባቸውን የኑሮ ሁኔታ ማሻሻል ላይ መትጋት እንደለባቸው የዓለም ባንክ ሪፖርት አሳስቧል፡፡
Published in
ዜና
Latest from Administrator
- የእስራኤል እና የኢራን ፍጥጫ
- Insights on Israel's Response: Interview with Mr. Tomer Bar-Lavi, Chargé d’Affaires at the Embassy of Israel to Ethiopia
- Barr, a vocal Trump critic, says he will ‘support the Republican ticket’ in November
- Iran president warns of ‘massive’ response if Israel launches ‘tiniest invasion’
- "አልሞቷል" ፊልም ዛሬ በዓለም ሲኒማ ይመረቃል