Sunday, 10 July 2022 19:40

ከ100 በላይ አለም አቀፍ የግንባታ ኩባንያዎች የሚሳተፉበት አውደ ርዕይ ሊካሄድ ነው

Written by 
Rate this item
(0 votes)

 በአለም አቀፍ ደረጃ የኮንስትራክሽን ንግድ ትርዒት በማዘጋጀት የሚታወቀው  “ቢግ ፋይቭ” የተባለው ድርጅት አገር በቀል ከሆነው ኤትኤል ኤቨንትና ኮሚዩኒኬሽን ጋር በመተባበር በሚያዘጋጁት አውደርዕይ ላይ ከ100 በላይ አለም አቀፍ የግንባታና የኮንስትራክሽን ኩባንያዎች ይሳተፉበታል ተብሏል። በአውደ ርዕዩ የሚሳተፉት ስመጥር አለምአቀፍ የግንባታ ኩባንያዎች ልምዳቸውን ለአገር በቀል ኩባንያዎቹ የሚያካፍሉበት መርሃ ግብር እንደሚኖርም ተጠቁሟል።
አውደ ርዕዩ በኢትዮጵያ በግንባታው ዘርፍ የሚታዩ ችግሮችን ለመቅረፍ የሚያስችል ልምድ የሚገኝበት መሆኑን የተናገሩት ኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ዮናስ አያሌው በአለምበአቀፍ ገበያ ለመወዳደር የሚያስችለን ልምድና ቴክኖሎጂ ወደ አገራችን እንዲመጣ እንዲሁም በአገራን በዘርፉ የተሰማሩ ኩባንያዎች የአለም ገበያን ለመቀላቀል የሚችሉበት ዕድል የሚያስገኙበት ይሆናል ብለዋል።
አውደርዕዩ በተጨማሪ የሚሳተፉ ከአለም አቀፍ የግንባታ ዕቃ አምራቾችና ተቋራጮች ጋር የንግድና ስራ ትስስር ለመፍጠር ያስችላል ያሉ ዋና ስራ አስፈጻሚው፤ ከተለያዩ የግንባታ ዕቃ አምራቾች ጋር እንድንተዋወቅም ያግዘናል ብለዋል።
“ቢግ ፋይቭ” ኮንስትራክሽን በአለም አቀፉ ደረጃ የሚዘጋጁ ታላላቅ አውደርዕዮችን በማዘጋጀት የሚታወቅ አለም አቀፋዊ ተቋም ሲሆን ወደ አገራችን ሲመጣ ይህ የመጀመሪያው እንደሚሆንና በቀጣይም በቋሚነት ለመስራት መዘጋጀቱ ታውቋል።
በሥራና ከተማ ልማት ሚኒስቴር ሙሉ ዕውቅና የተሰጠው ይኸው አውደ ርዕይ ከመጪው ሐምሌ 10 እስከ 15 ቀን 2015 ዓ.ም በሚሊኒየም አዳራሽ እንደሚካሄድም አዘጋጆቹ ተናግረዋል።




_______________________________________________


Read 1280 times