Friday, 08 July 2022 00:00

የኑሮ ውድነትን ለመቀነስ በመንግስት የተቀመጡ 4 አቅጣጫዎች

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(0 votes)

 በቀጣይ ዓመት መንግስት የሃገሪቱን ምጣኔ ሃብት ከቀውስ ለመታደግና የኑሮ ውድነቱን ለመቀነስ  አራት የትኩረት አቅጣጫዎችን እንደሚከተል ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ አመልክተዋል።
መንግስታቸው ባለፉት ሁለት ዓመታት የዋጋ ንረትን ለማረጋጋትና የኑሮ ውድነትን ለመቆጣጠር ጠንካራ እርምጃዎች ባይወስድ ኖሮ ከፍተኛ ቀውስ ያጋጥም እንደነበር ያወሱት ጠ/ሚኒስትሩ፤ በቀጣይም በ2015 የበጀት ዓመት በዋናነት የዋጋ ንረትንና የኑሮ ውድነትን በመቆጣጠር ላይ በልዩ ትኩረት ይሰራል ብለዋል።
መንግስታቸው በቀጣዩ የበጀት ዓመት የኑሮ ውድነትን ለመቀነስና የሃገሪቱን ምጣኔ ሃብት ከቀውስ ለመታደግ የሚወስዳቸው አራት አበይት እርምጃዎች፡- ብድርን መቀነስ፣ የበጀት ጉድለትን መቀነስ፣ ሃገሪቱ  ያላትን ሃብት በቁጠባ መጠቀም እንዲሁም የዋጋ ንረትን ማረጋጋት ሲሆን ለዚህም ጠንካራ የፋይናንስ ቁጥጥር ስርአት ይተገበራል ብለዋል።
በሁሉም ዘርፍ ምርታማነትን ማሳደግ፣ በግብርና የተጀመረውን የበጋ መስኖ ስራ አጠናክሮ ማስቀጠልና በቂ የእህል ምርት በማምረት በምግብ ራስን መቻል እንዲሁም የተጀመሩ ፕሮጀክቶችን ማጠናቀቅ መንግስት በልዩ ትኩረት የሚሰራባቸው መሆኑን የጠቆሙት ጠ/ሚኒስትሩ፤ በቀጣይ በጀት አመት አዳዲስ ሜጋ ፕሮጀክቶች እንደማይጀመሩ አመልክተዋል።
የምጣኔ ሃብት ሁኔታን ለማስተካከል መንግስት ከታለመው አቅጣጫ በተጨማሪ ለቀጣይ አመት የሃገሪቱን ሰላምና ደህንነት ማስጠበቅ እንዲሁም በግጭትና በተለያዩ ምክንያቶች ከቀያቸው የተፈናቀሉ ዜጎችን መልሶ የማቋቋም ተግባር ላይ በልዩ ትኩረት ይሰራል ብለዋል- ጠ/ሚኒስትሩ።

Read 9889 times