• ፈጣሪ ድምጽ እንድንሰጥ ቢፈልግ ኖሮ እጩዎችን ያቀርብልን ነበር፡፡
ጄይ ሌኖ
• በሰው አዕምሮ ላይ የሚካሄድ ማናቸውንም ዓይነት ጭቆና እቃወማለሁ፡፡
ቶማስ ጄፈርሰን
• በአሜሪካ ማንም ሰው ፕሬዚዳንት መሆን ይችላል። ያ ነው ችግሩ።
ጆርጅ ካርሊን
• አንድን ሰውን ወደ ምክር ቤት ልትመራው ትችላለህ፤ እንዲያስብ ግን ልታደርገው አትችልም፡፡
ሚልተን በርሌ
• እርስ በርሱ የተከፋፈለ ቤት መቆም አይችልም።
አብርሃም ሊንከን
• መሳሳት ሰውኛ ነው፤ ስህተትን በሌላ ፓርቲ ላይ ማላከክ ፖለቲካ ነው።
ያልታወቀ ተናጋሪ
• እጅግ ከሚያስፈልገው በላይ ግብር መሰብሰብ ህጋዊ ዝርፊያ ነው፡፡
ካልቪን ኩሊጅ
• የምንኖረው ፖለቲካ ፍልስፍናን በተካበት ዓለም ውስጥ ነው፡፡
ማርቲን ኤል.ግሮስ
• እኛ መንግስትን ስንዋሽ ወንጀል ነው፡፡ እነሱ እኛን ሲዋሹን ፖለቲካ ነው፡፡
ቢል ሙሬይ
• እያንዳንዱ ምርጫ የሚወሰነው ድምጽ ለመስጠት ወደ ምርጫ ጣቢያው በሚወጡ ሰዎች ነው፡፡
ላሪ ጄ. ሳባቶ
• ዲሞክራሲ ድምጽ የመስጠት መብት ብቻ ሳይሆን በክብር የመኖር መብትም ነው፡፡
ናኦሚ ክሌይን
• የታሪክ ጥናት የጥበብ መጀመሪያ ነው፡፡
ዣን ቦዲን
Published in
ፖለቲካ በፈገግታ
Latest from Administrator
- የእስራኤል እና የኢራን ፍጥጫ
- Insights on Israel's Response: Interview with Mr. Tomer Bar-Lavi, Chargé d’Affaires at the Embassy of Israel to Ethiopia
- Barr, a vocal Trump critic, says he will ‘support the Republican ticket’ in November
- Iran president warns of ‘massive’ response if Israel launches ‘tiniest invasion’
- "አልሞቷል" ፊልም ዛሬ በዓለም ሲኒማ ይመረቃል