Saturday, 25 June 2022 17:49

“የብረት ቆሎ” መፅሐፍ ዛሬ ይመረቃል የገነት ጦር ት/ቤት ታሪክ ከ1927-1983

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(2 votes)

 በሻምበል  ታደሰ ወልደገብርኤል የተዘጋጀውና ከ1927 እስከ 1983 ዓ.ም ድረስ ያለውን የገነት ጦር ት/ቤትን ታሪክ የሚያወሳው መጽሐፍ ዛሬ በሆለታ ገነት ትልልቅ የጦር መኮንኖች፣ የቀድሞ የኢትዮጵያ የሰራዊት አባላትና የደራሲው ጓደኞች በተገኙበት መረቃል።
“የብረት ቆሎ” የተሰኘውና የጦር ት/ቤቱን ታሪክ በስፋትና በጥልቀት የሚዳስሰው መጽሀፉ፣ ደራሲውም የነበሩበትን ያዩትን፣ ታሪኮችና የጦር ት/ቤቱ ያፈራቸውን የኢትዮጵያ ጀግኖች ትውስታ የዳሰሱበት ስራ መሆኑን ገልጸው የጦር ት/ቤቱ ካፈራቸው ድንቅ ኢትጵያዊያን መካከል ሌተናል ጀነራል አማን ሚካኤል አንዶም፣ ሜጀር ጀነራል ተፈሪ በንቲ፣ መቶ አለቃ ግርማ ወልደ ጊዮርጊስ  (ቀድሞ የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት)፣ ኮሎኔል መንግስቱ ሃይለማሪያም (የኢህድሪ ፕሬዚዳንት) ሌተናል ጀነራል ተስፋየ ገብረኪዳንን በምሳሌነት ጠቅሰዋል “የብረት ቆሎ” መጽሀፍ በ117 ገጽ ተቀንብቦ በ150 ብር ለገበያ ቀርቧል።


Read 21533 times