Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 13 October 2012 10:13

“አቡነ መርቆሬዎስ እስካሉ ቤተክርስቲያኒቱ በእንደራሴ ትመራለች” (የቤተክህነት ምንጮች)

Written by 
Rate this item
(4 votes)


በሌላ በኩል በድሬዳዋ ሀገረ ስብከት በሚገኘው የሳባ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ሕንጻ ግንባታ ጋር በተያያዘ ተፈጽሟል የተባለውን ሙስና እና በሀገረ ስብከቱ ጽ/ቤት የሰፈነውን የአስተዳደር በደል የሚያጣራ በቅዱስ ሲኖዶሱ የተሠየመ እና በምክትል ሥራ አስኪያጁ አቶ ተስፋዬ ውብሸት የሚመራ ሦስት አባላት ያሉት ልዑክ ወደ ስፍራው እንደሚያመራ ተገልጧል፡፡ ባለፉት ስምንት ዓመታት ሲጓተት በቆየው የቤተክርስትያኑ ሕንፃ ሥራ ከ5.6 ሚሊዮን ብር በላይ ለዘረፋና ብክነት የተጋለጠ ቢሆንም ግንባታው ከተቋራጩ ጋር ውል በተገባበት የሁለት ዓመት የጊዜ ገደብና በፕላኑ መሠረት አለመፈፀሙ የአጥቢያውን ካህናትና ምእመናን ለተቃውሞ ማነሳሳቱ ተዘግቧል፡፡

የአቡነ ጳውሎስን ህልፈተ ሕይወት ተከትሎ ቤተክርስቲያኒቱን እየመራ ያለው ሲኖዶስ፣ በቤተክህነቱ መዋቅር ውስጥ ተንሰራፍቷል የተባለውን የሙስናና የአስተዳደር ብልሹነት ምንጮች በመለየት መሠረታዊ መፍትሔ የሚያገኝበትን አማራጭ በመጪው የጥቅምት ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በማቅረብ አስተዳደሩን ለማጠናከር ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ እንደሚገኝ ምንጮች ለአዲስ አድማስ አስታውቀዋል፡፡   በጉዳዩ ላይ የዝግጅት ክፍላችን አስተያየታቸውን የጠየቃቸው የቤተክህነቱ ምንጮች፣ “አዲስ ፓትርያርክ ከመሾም በመለስ አቡነ መርቆሬዎስ በሕይወት እስካሉ ድረስ በቤተክርስቲያኑ ከፍተኛ የአመራር መዋቅር የሆነው ቅዱስ ሲኖዶስ በአንድ ጠንካራ እንደራሴ አልያም በዐቃቤ መንበረ ፓትሪያሪክ እንዲመራ ማድረግ ለሁለት ዐሥርት ዓመታት በአስተዳደር ተከፋፍላ ለቆየችው የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን አንድነት መጠበቅ ቀዳሚ አማራጭ ነው፤ ይላሉ፡፡ ይሁንና አማራጩ በአሁኑ ወቅት በቤተክህነቱ ውስጥ ቀጣዩን ፓትሪያሪክ ከተለያየ መነሻና ፍላጐት እናስመርጣለን በሚል እንደሚንቀሳቀሱ ከሚነገርላቸው ቡድኖችና የዕርቀ ሰላም ሂደቱ በተጀመረው አኳኋን ቀጥሎ እንዳይሠምር ዕንቅፋት ይፈጥራሉ በሚባሉት የፖለቲካ ኃይሎች ጣልቃ ገብነት ሳቢያ ተግዳሮት እንደሚገጥመው ተመልክቷል፡፡ ሕዝቡም ከሚመለከተው የቤተክርስቲያኒቱ አካል የሚሰጠውን መረጃ ብቻ እንዲከታተል አሳስቧል፡፡  ስድስተኛውን ፓትርያርክ ለማስመረጥ በተለያየ መንገድ ይንቀሳቀሳሉ የተባሉት ቡድኖች ለቦታው ከሚያስፈልገው መንፈሳዊነት እና ብቃት ይልቅ በዋናነት የተወላጅነት (የብሔር ማንነትን) መነሻ እንደሚያደርጉ ተጠቁሟል፡፡ ይህ ሁኔታ ቤተክርስቲያኒቱ የምትገኝበትን ሰላማዊ የሽግግር ሂደት ከማወክ ተለይቶ እንደማይታይ የገለፀው የጠቅላይ ቤተክህነቱ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ፤ እኒህ ቡድኖች በመንበረ ፓትርያርኩ ውስጥ ተሸሽገው ከሚያካሂዱት አፍራሽ ተግባርና ከሚነዙት አሉባልታ እንዲቆጠቡ ማስጠንቀቁ ይታወሳል፡፡ ወደ መንበራቸው ቢመለሱም በጤና ማጣትና በዕድሜ በመግፋታቸው ሳቢያ በሐላፊነት ተቀምጠው ለመቀጠል ፍላጐት እንደሌላቸው ተናግረዋል የተባሉት የቀድሞው ፓትርያርክ፤ በሕይወተ ሥጋ እስካሉ ድረስ መንበሩ ተጠብቆ የቤተክርስቲያኒቱ የበላይ አመራር የሆነው ቅዱስ ሲኖዶስ በእንደራሴ እንዲመራ ሐሳብ አቅርበዋል ተብሏል፡፡ መቀመጫውን በአሜሪካ በማድረግ በውግዘት በተለያዩት የአገር ቤቱ ሲኖዶስ እና “የስደት ሲኖዶስ” ባቋቋሙት ጳጳሳት መካከል “ዕርቀ ሰላም እንዲወርድና ውግዘቱ እንዲነሣ እየሠራ ነው” የተባለው “የሰላምና አንድነት ጉባኤ”፤ በቅርቡ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ መርቆሬዎስን ማነጋገሩን የገለጹት ምንጮቹ፤ ፓትርያርኩ ተገደው ከመንበራቸው እንዲወርዱ ከተደረገ በኋላ በሁሉም ወገን የተፈፀሙት የቀኖና ቤተክርስቲያን ጥሰቶች ተስተካክለው ማየት እንደሚፈልጉ መናገራቸውን አባ መርቆሬዎስን በመጥቀስ አስረድተዋል፡፡ ከአምስተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ሕልፈት በኋላ በሰሜን አሜሪካ “ስደተኛ ሲኖዶስ” ካቋቋሙት ጳጳሳት ጋር እየተካሄደ በሚገኘው የዕርቀ ሰላም ውይይት አራተኛው ፓትርያርክ የነበሩት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ በሕይወት እስካሉ ድረስ ሲኖዶሱ በእንደራሴነት በሚሾም ሊቀ ጳጳስ ቤተክርስቲያኒቱን እንዲመራ ሊወሰን እንደሚችል ምንጮች ገለፁ፡፡ በድሬዳዋ ቅ/ገብርኤል ተፈፀመ የተባለውን ሙስና የሚያጣራ ልኡክ ወደ ስፍራው ያመራል

Read 4027 times