Thursday, 09 June 2022 13:18

ኦላ ኢነርጂ ኢትዮጵያ አዲስ ብራንድ ሊያስተዋውቅ ነው

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

ኦላ ኢነርጂ ኢትዮጵያ፤ በሀገሪቱ ውስጥ ባሉ የነዳጅ ማደያና የአገልግሎት መስጫ ጣቢያዎቹ ውስጥ በሚገነቡ የፕሪሚየም የመኪና ጥገና ማዕከላት በመታጀብ፣ አዲሱን ብራንድ ለማስተዋወቅ በዝግጅት ላይ መሆኑ ተገለጸ፡፡
 አዲሱ ብራንድ በመጀመሪያ በአዲስ አበባ ውስጥ በሚገኙ በተመረጡ የነዳጅ ማደያና አገልግሎት መስጫ ጣቢያዎች የሚተገበር ሲሆን፣ በመቀጠልም በመላው ሀገሪቱ በሚገኙ የችርቻሮ አውታሮቹ  በሙሉ ደረጃ በደረጃ እንደሚከናወን ኦላ ኢነርጂ ኢትዮጵያ አስታውቋል፡፡
የኦላ ኢነርጂ ግሩፕ አካል የሆነው ሊቢያ ኦይል ኢትዮጵያ ሊሚትድ ስሙን በህጋዊ መንገድ ቀይሮ ከጥር 29 ቀን 2014 ዓ.ም. ጀምሮ ኦላ ኢነርጂ ኢትዮጵያ ሊሚትድ መባሏን ያስታወሰው  ኩባንያው፤ በአፍሪካ ውስጥ ዳግም ብራንድ ከተደረጉት የኦላ ኢነርጂ ግሩፕ ኔትወርክ (የሪቴይል/የችርቻሮ መሸጫ አውታረ መረቦቹ) ጋር ለመቀላቀል በዝግጅት ላይ መሆኑን ጠቁሟል፡፡
በመስቀል አደባባይ የነዳጅ ማደያና አገልግሎት መስጫ ጣቢያ የሚገኘውን አክሰል አውቶ ኬር ማዕከሉን እያስተዋወቀ መሆኑን የጠቆመው ኩባንያው፤ይህም በሀገሪቱ በሚገኙት የአገልግሎት መስጫ ጣቢያዎቹ ለሚመጣው ለእያንዳንዱ ጎብኚ ከፍተኛ ጥራት ያለው አገልግሎት ለመስጠት ወሳኝ ነው ብሏል።

Read 4419 times