Tuesday, 07 June 2022 07:42

የነገር ጥግ

Written by 
Rate this item
(2 votes)

 አንድ ባለሥልጣን ገጠር ሲጎበኙ ለተሰበሰበው ህዝብ ንግግር ያደርጋሉ፡፡ የለውጡን ዓላማ ነግረው ሲያበቁ፣የህዝቡን ለውጥ አፍቃሪነት  ያደንቃሉ፡፡
 በመጨረሻም ጥያቄ ለመመለስ ዝግጁ እንደሆኑ ይገልጻሉ፡፡ ከተሰበሰቡት  ሰዎች መካከል በጊዜው
 ለውጥ ለማምጣት ከሚታገሉት ወጣቶች መካከል አንዳንዶቹ ተገኝተውበታል፡፡
ከእነዚህ አንዱ ተነስቶ ባለሥልጣኑ ለውጥ ለውጥ የሚሉት የለበጣ እንደሆነ፣ አምባገነኖች ማስመሰልና ዲሞክራሲያዊ ቃላትን እንደ በቀቀን መትፋት ዋና አመላቸው እንደሆነ፣ በኢትዮጵያ ዲሞክራሲን ለማስፈን ገና ብዙ ትግል እንደሚፈልግ፣ ባለሥልጣኑን ጨምሮ ብዙ አስመሳይ መሪዎች ከሥልጣን መወገድ እንዳለባቸው፣ የህዝብን ሰላም ሊያስከብር የሚችል በህዝብ የተመረጠ መንግስት እንደሆነ በርቱዕ አንደበት፣ በጣፈጠ አማርኛ አስረዳና ተቀመጠ፡፡
 ጭብጨባው አላቋርጥ አለ፡፡ ባለሥልጣኑ ፊታቸው ጥቀርሻ መሰለ፡፡ ያልጠበቁት ነገር ስለሆነም ለጥቂት ጊዜ ግራ-ተጋብተው ቆዩ፡፡
በመጨረሻ እንደምንም  ጭብጨባውና ውካታው ጋብ እስኪል ጠብቀው፣ ሁሉም ሲረጋጋ ቀና አሉ፡፡ ወደ ወጣቱ ዘወር አሉናም፤ ጥሩ ትናገራለህ፡፡ ግን ዕድሜህ አጭር ነው! ብለው ወደ ማረፊያቸው ሄዱ፡፡

Read 1532 times