Print this page
Saturday, 30 April 2022 14:47

ጆሹዋ ቡጌምቢን ይተዋወቁት

Written by  ናፍቆት ዩሴፍ
Rate this item
(0 votes)

   የ12 ዓመት ታዳጊና የሞተር ስፖርት ተወዳዳሪ ነው
በእናቱ ኢትዮጵያዊና በአባቱ ዩጋንዳዊ ሲሆን የለንደን ከተማ ነዋሪ ነው
ጆሹዋ  በእሱ እድሜ ከሚወዳደሩ በጣት የሚቆጠሩ ጥቁር ታዳጊዎች ታዋቂውና በሽልማት የሚንበሸበሸው ነው
በለንደን በበርካታ ታዋቂ  መጽሄቶችና ጋዜጦች እንዲሁም የቴሌቪዥን ጣቢያዎች ብዙ ተጽፎለታል -ተነግሮለታል
ውድድር የጀመረው እ.ኤ.አ በ2020 ነው፤ በግማሽ ዓመት ብቻ 4 ዋንጫዎች ተሸልሟል
በ2021 ሙሉ ዓመቱን ተወዳድሮ 26 ዋንጫ ተሸልሟል
በክለብ ሻምፒዮንሽፕ ከእኩዮቹ ጋር ተወዳድሮ ሲያሸንፍ፤ በሌላም ውድድር “Driver of the year” በሚል ተመርጧል
በዚህ የሞተር ስፖርት ኢትዮጵያንና አፍሪካን የማስጠራት ህልም አለኝ ብሏል
(የአዲስ አድማስ ጋዜጠኛ ናፍቆት ዮሴፍ፣ ከጆሹዋ እናት ኢትዮጵያዊቷ ዴሊና ጋር ያደረገችውን  ቃለ ምልልስ በመጪው ሳምንት  እናስነብባችኋለን።)


Read 1124 times