Saturday, 30 April 2022 14:16

“አንድ ነገር ስለ ሀገር” የኪነጥበብ ምሽት ሰኞ ይካሄዳል

Written by  ናፍቆት ዩሴፍ
Rate this item
(2 votes)


             በምስክር  ጌታነው ሚዲያና ፕሮሞሽን በየወሩ የሚዘጋጀው የኪነ-ጥበብ ምሽት የዚህ ወር መሰናዶ “አንድ ነገር ስለሀገር” በሚል ርዕስ ሰኞ ሚያዚያ 24 ቀን 2011 ዓ.ም  በኢትዮጵያ ብሄራዊ ቴአትር ከቀኑ 11፡00 ጀምሮ ይካሄዳል። በዕለቱ ፕ/ር አደም ካሚል፣ ዶ/ር ወዳጄነህ መሃረነ፣ መስከረም አበራና አንዷለም አራጌ ዲስኩር የሚያቀርቡ ሲሆን፣ ገጣሚያኑ ነቢይ መኮንን፣ ኤፍሬም ስዩምና ትዕግስት ማሞ ግጥም ያቀርባሉ ተብሏል። የዕለቱ ወግ አቅራቢዎች ወግ አዋቂው በሃይሉ ገ/መድህን አርቲስት ሱራፌል ተካና ረ/ፕ ተስፋዬ እሸቱ እንደሆኑ የተገለጸ ሲሆን፣ የመግቢያ ዋጋው 100 ብር ነው ተብሏል።
የመግቢያ ትኬቶቹም በጃዕፈር፣ አይናለም፣ ዮናስ መጻህፍት መደብሮች፣ ጣይቱ ሆቴልና ከካዛንቺስ በሚገኘው ጆሲ ልብስ ስፌት ቤት እንደሚገኙም ታውቋል።

Read 11360 times