Saturday, 16 April 2022 14:11

የኮሮና ቫይረስ ክትባት ለህጻናት…..

Written by  ፀሐይ ተፈረደኝ ከኢሶግ
Rate this item
(0 votes)

 የአለም ጤና ድርጅት እንዳወጣው መረጃ ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ ከJanuary 2020 እስከ April 2022 ድረስ 469,979 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ 7,508 ሰዎች በቫይረሱ ምክንያት ለህልፈት ተዳርገዋል፡፡ እስከ ማርች 22 ድረስ 29,373,478 የሚሆኑ ሰዎች ክትባት ወስደዋል፡፡ የአለም የጤና ድርጅት እንደገለጸው ከሆነ ወደ 343,954 የሚ ሆኑ ሰዎች አቅምን ማጎልበቻ ወይንም ተጨማሪ ክትባትን ለ3ኛ ጊዜ ወስደዋል፡፡  
ከኢትዮጵያ April 11/2022 የወጣው መረጃ እንደሚያሳየው ደግሞ 470,050 የሚሆኑ ሰዎች በቫይረሱ እንደተያዙና 7,509 የሚሆኑት መሞታቸውን እንዲሁም 453,570 የሚሆኑት ደግሞ  ከበሽታው ማገገማቸውን ይጠቁማል፡፡
ህጻናትን ከኮሮና ቫይረስ ለመከላከል ክትባት እንዲወስዱ ማድረግ ተገቢ መሆኑንና ይህም በአለም ላይ በተግባር ላይ መዋሉን መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ ወደክትባት ከማለፋችን በፊት ከአሁን ቀደም ለንባብ ብለነው የነበረውን ህጻናትን ከCovid-19 ጋር የተመለከትንበትን ጽሁፍ ለትውስታ ለንባብ ብለነዋል፡፡
ህጻናት በኮሮና ቫይረስ ለመያዝ ቅርብ የመሆናቸውን ያህል ነገር ግን እንደወጣቶቹ ወይንም ትልልቅ ሰዎች በቀላል የማይታመሙ ሲሆን ምልክታቸውም ቀለል ብሎ የሚታይ ነው፡፡ ሕጻናቱን ከቫይረሱ ጋር በማያያዝ ያለውን እውነታ ለማየት የሚያስችል በቂ ጥናት ባይ ኖርም ከአሜሪካ የህጻ ናት ሆስፒታል እንደተገኘው መረጃ ከሆነ ከሚታከሙት ህጻናት 10 % የሚሆኑት ብቻ የኮሮና ቫይረስ እንደሚገኝባቸው መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ በመጠኑም ቢሆን የተደረጉ ጥናታዊ ስራዎች እንደሚያመላክቱ ትም እድሜያቸው ከ20 አመት ጀምሮ ከፍ ከሚሉት በተሻለ ህጻናቱ በቫይረሱ እንደማይያዙ ብሎም እንደማይጎዱ ያመላክታል፡፡ በሆስፒታል አልጋ የሚይዙት ህጻናትም ቁጥር አነስተኛ መሆኑን አጥኚዎቹ ይናገራሉ፡፡ CDC እንደገለጸው ህጻናቱ በቫይረሱ ከተያዙ ሊረዱ የሚገባቸው በጽኑ ሕሙማን ክፍል መሆን አለበት፡፡ አንዳንድ ጊዜ ህጻናት ከኮሮና ቫይረስ ጋር ሊገናኝ የሚችል ከባድ የሆነ የሕመም ስሜት ሊታይባቸውም እንደሚችል መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡
አዲስ የተወለዱ ህጻናት በኮሮና ቫይረስ ሊያዙ እንደ ሚችሉ አስቀድሞ ማወቅም ተገቢ ነው ፡፡ እነዚህ ጨቅላዎች በቫይረሱ ሊየዙ የሚችሉባቸው የተ ለያዩ ምክንያቶች ሊኖሩ ሲችሉ ከእነዚህም መካከል በሚወለዱበት ጊዜ ሊኖራቸው ከሚችል ተጋላጭነት አንዱ ሲሆን ይህም ከእናቶቻቸው ወይንም ከተንከባካቢዎቻቸው ሊሆን ይችላል፡፡ ልጆቹ ከተወለዱ በሁዋላም ቢሆን እናቶች የኮሮና ቫይረስ የያዛቸው ከሆኑ ወይም ደግሞ ይዞአቸው ወይንም አልያዛቸው እንደሆነ ለማወቅ ለምርመራ በመጠባበቅ ላይ ከሆኑ የመከላከያ ጭምብል (የአፍና የአፍ ንጫ) መሸፈኛ ሳያደርጉ ህጻኑን መንከባከብ እንደ ሌለባቸው ጥናቶች ይጠቁማሉ፡፡ እናቶች ወይንም ተንከባካቢዎች ህጻኑን ከመንካታቸው በፊት እጃቸውን በሚገባ መታጠብ እንዳለባ ቸውም መዘንጋት የለባቸውም፡፡ አዲስ የተወለዱ ህጻናትን በሆስፒታል ውስጥ በራሳ ቸው አልጋ ላይ የሚተኙ ሲሆን ወደመኖሪያ ቤት ሲሄዱ ግን በተቻለ መጠን አቅም በፈቀደ እርቀታቸውን ጠብቆ ማስተኛት ተገቢ ነው። በዚህ መንገድ ጥንቃቄ ከተደረገ አዲስ የተወ ለዱ ህጻናት በኮሮና ቫይረስ የመያዛቸው እድል እጅግ አነስተኛ ይሆናል፡፡ ጥናቶች እንደሚ ያሳዩት  የኮሮና ቫይረስ ካለባቸው እናቶች የተወለዱ ጨቅላዎች ከ2%-5% የሚ ሆኑት ብቻ  እንደተወ ለዱ ሲመረመሩ ቫይረሱ በደማቸው ተገኝቶአል፡፡ አንዲት እናት በኮሮና ቫይረስ ከፍ ባለ ሁኔታ የታመመች ከሆነች አዲስ ከተወለደው ጨቅላ ህጻን መራቅ ይገባታል፡፡
የኮሮና ቫይረስ የያዛቸው ጨቅላ ህጻናት ቫይረሱ ይያዛቸው አይያዛቸው ለመለየት እንዲቻል በተለያየ ምክንያት ምርመራ ሊደረግላቸው ካልቻለ እና ጨቅላዎቹም ምንም ምልክት የማያሳዩ ከሆነ እንደጤነኛ ህጻን ከሆስፒታል ሊወጡ ይችላሉ፡፡ በእንደዚህ ያለው አጋጣሚ በሆስፒታል ያሉ አገልግሎት ሰጪዎች ከጨቅላው ልጅ ቫይረሱ ሊተላለፍባቸው እንደሚችል ምንም ጥር ጥር የለውም፡፡ ስለዚህ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የሚያስችሉትን የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማድረግ እንዲሁም እጅን በሚገባ መታጠብን አዘውትረው መተግበር ይጠበቅባቸዋል፡፡ የህጻኑን ጤንነት ለተወሰኑ ቀናት የመከላከል ስራም በስልክ ወይንም በኮምፒዩ ተር በመታገዝ እና ጥንቃቄ በተሞላበት መንገድ በማድረግ ህጻኑ ጤነኛ መሆኑ ሲረጋገጥ ወደቤቱ መሄድ እንደሚችል ባለሙያዎች ይገልጻሉ፡፡
ህጻናት ኮሮና ቫይረስ ሲይዛቸው የሚያሳዩት ምልክት፡-
ምንም እንኩዋን ህጻናትና አዋቂዎች በኮሮና ቫይረስ ሲያዙ ተመሳሳይ ምልክት ቢያሳዩም ህጻናቱ ላይ ግን የሚታየው በአነስተኛ ደረጃ ሊሆን ይችላል፡፡ አብዛኞቹ ህጻናትም በአንድ ወይንም በሁለት ቀን ከህመሙ ሊያገግሙ ይችላሉ፡፡ ሊኖሩ የሚችሉት የህመም ምልክቶ ችም እንደሚከተለው ተዘርዝረዋል፡፡
ትኩሳት… በአፍንጫ ፈሳሽ (ንፍጥ) መታየት፤
ሳል…የጉሮሮ ሕመም፤
የትንፋሽ ማጠር ወይንም ለመተንፈስ መቸገር፤
የአቅም ማነስ…..ራስ ምታት…..የጡንቻ ሕመም፤
ተውከት….ተቅማጥ…..የምግብ ፍላጎት ማጣት፤
የማሽተት ወይንም የማጣጣም ችግር፤
የአይን መቅላት….የሆድ ሕመም፤
አንድ ህጻን ከላይ የተጠቀሱትን ምልክቶች ካሳየ በኮሮና ቫይረስ የመያዝ ምልክት ሊሆን ስለሚችል በአስቸኳይ የህክምና ባለሙያ እንዲጎበኘው ማድረግ ይገባል፡፡ ህጻኑ በቤት ውስጥ ክትትል ሊደረግለትና በተቻለ መጠን ከህክምና ባለሙያ በስተቀር ከሌሎች መራቅ አለበት፡፡ ከተቻለ ህጻኑ ከሌላው የቤተሰብ አካላት ተለይቶ ለብቻው አንድ ክፍል ቢሰጠው ጥሩ ነው፡፡ ባጠቃላይም የአለም የጤና ድርጅት ወይንም የአገሩ መንግስት በኮሮና ቫይረስ ምክንያት በሚያወጣው ራስን የማግለል አሰራር መሰረት ሁሉም መተግበር ይገባዋል፡፡    
ሕጻናት የኮሮና ቫይረስ ሲይዛቸው አፋጠኝ የሆነ የህክምና እርዳታ የሚያስፈልጋቸው የህመም ደረጃ አለ፡፡ በሰውነታቸው ወይንም በእንቅስቃሴአቸው አለዚያም በአመጋገባቸው ላይ ትልቅ ልዩነት ይታያል፡፡ ለምሳሌም፡-
ለመንቃት መቸገር ወይንም እንደነቁ መቆየት ሊያቅታቸው ይችላል፡፡
መተንፈስ ሊያቅታቸው ይችላል፡፡
ደረት ላይ ሕመም ወይንም የማይለቅ ጫና ያለው ስቃይ ሊኖር ይችላል፡፡
ህጻኑ ያለመረጋጋት እና የመነጫነጭ ባህርይው ግራ በሚያጋባ መልክ ሊሆን ይችላል፡፡
ከንፈር ወይንም ፊት ሰማያዊ ቀለም ሊኖረው ይችላል፡፡
ህጻናት ኮሮና ቫይረስ በሚይዛቸው ወቅት የሚኖራቸው ትኩሳት የመሳሰለው ስሜት በተለያዩ የሰውነት ክፍሎች ላይ ሊከሰት የሚችል መሆኑን ጥናቶች ያሳያሉ፡፡ ለምሳሌም በልብ ላይ፤ በደም ስሮች፣በኩላሊት፣በአእምሮ ወይም በአይኖች ፤በቆዳ ላይ ሁሉ ሊገለጽ ወይንም የህመም ስሜቱ ሊታይ ይችላል፡፡ ይህ የሚያሳየው ምናልባትም ችግሩ በታየበት ወቅት ብቻ ሳይሆን ቀደም ሲል ቫይረሱ ይዞአቸው ቆይቶ ሊሆን እንደሚችል ነው፡፡
CDC ባወጣው መረጃ እንደተገለጸው ህጻናት ኮሮናን ለመከላከል የተዘጋጀውን ክትባት መውሰድ አለባቸው፡፡ በእርግጥ የመድሀኒቱ አይነትና እድሜያቸው በባለሙያ እንደሚወሰን መረጃው ይገልጻል፡፡ እ.ኤ.አ ኤፕሪል /2022 ለንባብ ይፋ የሆነው መረጃ እንደሚያሳየው የክትባቱ መውሰጃ እድሜ የሚጀምረው ከአምስት አመታቸው ጀምሮ ሲሆን በተለይም ከ5-17 እድሜ ያሉት ህጻናት የሚወስዱት የክትባት አይነትም Pfizer-BioNTech የተባለውን ነው፡፡
በእድሜአቸው ከ12-17 አመት የሚሆኑት ህጻናት የተጠቀሰውን Pfizer-BioN- Tech የተባለውን  ክትባት የሚወስዱት ትላልቅ ሰዎች የሚወስዱትን መጠን ሲሆን እድሜአቸው ከ5-11 የሚደርሱት ደግሞ ለእነርሱ እድሜ የተወሰነውን መጠን ያህል እንደሚከተቡ መረጃው ይጠቅሳል፡፡፡
ይህ ወደፊት ሊሻሻል ወይንም ሊለወጥ የሚችል ሲሆን ወላጆች በተሰጠው መረጃ መሰረት ሐኪማቸውን እያማከሩ ልጆቻቸውን የማስከተብ ወይም የመንከባከብ ግዴታ አለባቸው፡፡

Read 10487 times