Saturday, 09 April 2022 15:01

የጡት ወተት ለማጥባት…መጠኑና...እርቀቱ…

Written by  ፀሐይ ተፈረደኝ ከኢሶግ
Rate this item
(0 votes)

   ገና የተወለዱ ጨቅላዎችን በመጀመሪያዎቹ ቀናት፤ ሳምንታት እና ወራት ምን ያህል መጠን በምን ያህል ፍጥነት ማጥባት እንደሚገባ CDC ለንባብ ያለውን እነሆ ታነቡ ዘንድ ጋብዘናል፡፡
በመጀመሪያዎቹ ቀናት፤
እናትየው ወይንም ቤተሰብ ስለልጆቻቸው እድገት ምን ያህል የጡት ወተት መስጠት እንዳለባቸው ካላወቁ የህጻናት ሐኪሞችን ወይንም ነርሶችን አስቀድሞ ማነጋገር ጠቃሚ ነው፡፡ ገና የተወለዱ ህጻናት ሆድ ትንሽ ወይንም ጠባብ ነው፡፡ ስለዚህ በእያንዳንዱ የማጥባት ወቅት ብዙ ወተት ሊሰጣቸው አይመከርም፡፡
አዲስ የተወለዱ ህጻናት ከ1-3 ሰአት ድረስ ባለው ጊዜ መመገብ ሊፈልጉ ይችላሉ። በተደጋጋሚ መመገብ ወተት በብቃት እንዲመረት እድል እንደሚፈጥር እሙን ነው፡፡ በተጨማሪም ህጻናቱ ወተቱን በብቃት እንዲጠቡ ወይንም እንዲስቡ እና እንዲውጡ እድሉን ይሰጣቸዋል፡፡ ህጻናቱ ጡት በሚጠቡበት ወቅት እናትየው እንዴት እንደሚስብ ልታዳምጠው ትችላለች፡፡
አብዛኞቹ የእናት ጡት ወተት መጥባት የቻሉ ጨቅላ ህጻናት በተለይም በመጀመሪያዎቹ ጥቂት ቀናት በምንም አይነት በኢንዱስትሪ የተዘጋጀ ወተት እንዲጠጡ ማድረግ አይገባም። ምናልባ ትም የጡት ወተትን በማጥባት በኩል ችግር ካጋጠመ ችግሩን ለመፍታት በምን መንገድ መጓዝ እንደሚገባ የህክምና ባለሙያን ወይንም ነርሶችን በቅድሚያ ማማከር ይገባል፡፡
ወላጆች ወይንም አሳዳጊዎች አንድ ሊያውቁ የሚገባቸው ነገር አለ፡፡ አንዳንድ ህጻናት ምግብ ከመውሰድ ይልቅ መተኛትን ሊመርጡ ይችላሉ፡፡ በተጨማሪም በመጀመሪያዎቹ ቀናት አንዳንድ  ጨቅላዎቹ ከ2-4 ሰአት ባለው የጊዜ ልዩነት ለእድገታቸው የሚረዳቸውን በቂ ምግብ ሊፈልጉ ይችላሉ፡፡
ከላይ የተጠቀሰው ሰአት የሚያመላክተው ህጻኑን እየቀሰቀሱ ጡት ማጥባት እንደሚያስፈልግ ነው፡፡ ስለዚህም መነካካት፤ ልብሱን መገላለጥ፤ ዲያፐሩን መለወጥ የመሳሰሉትን ስራዎች በመስራት ህጻኑ ከእንቅልፉ እንዲነቃ በማድረግ መመገብ ይቻላል፡፡
ልጁ በቀን ምን ያህል እንደሚተኛና እንደሚመገብ በመረዳት ምክር ከህጻኑ ሐኪም መጠየቅ ብልህነት ነው፡፡
በመጀመሪያዎቹ ሳምንታትና ወራት፤
አዲስ የተወለዱ ህጻናት እያደጉ በሚሄዱበት ጊዜ ሆዳቸውም አብሮ ያድጋል፡፡ ስለሆነም ህጻናቱ የጡት ወተት አመጋገባቸው መጠንም ይጨምራል፡፡
በመጀመሪያዎቹ ጥቂት ሳምንታት ወይንም ወራት የመመገቢያ ሰአታቸው በአማካይ ከ2-4 ሰአታት ሊራራቅ ይችላል፡፡ አንዳንዶች ደግሞ በየሰአቱ መመገብ  ለሎች ደግሞ በመ ኝታ ረዘም ያለ ጊዜ ወስደው የሚጠቡበት ሰአት ከ4-5 ሰአት ያህል ሊቆይ ይችላል፡፡
ህጻናቱ ጡት የሚጠቡበት ፍጥነት እንደቀኑ ወይንም እንደ ሰአቱ ሁኔታ ሊለዋወጥ ይችላል፡፡ አንዳንዱ ማጥባት ረዥም ጊዜ ሊወስድ ሲችል አንዳንዱ ደግሞ በአጭሩ ሊቋረጥ ይችላል፡፡ ይህ እንደችግር የሚወሰድ አይደለም፡፡ ህጻናቱ በየአንዳንዱ መጥባት ወቅት መጥባት የሚፈልጉትን ያህል ጠብተው መጥገብ ሲሰማቸው ሊያቆሙት ይችላሉ። በብቃት የጡት ወተት ከወሰዱ የመ ተኛት ሁኔታ ይታይባቸዋል፡፡
ባጠቃላይም ህጻናቱ በ24 ሰአት ጊዜ ውስጥ ከ8-12 ጊዜ ጡት ይጠባሉ፡፡  
ከ6 እስከ 12 ወራት፤
ጡት የጠቡ ህጻናት የምግብ ስርአታቸው ማለትም በምን ያህል ድግግሞሽ ወይንም ለምን ያህል ጊዜ ይመገባሉ የሚለው እንደ እድገታቸውና ከጡት ወተት በተጨማሪ ሌላ ምግብ እንደአወሳሰዳቸው ሁኔታ ሊጨምር ይችላል፡፡ ህጻናቱ የመራብ ስሜት ይኑራቸው አይኑራቸው መከታተል እና የጡት ወተት መውሰድ እንደሚፈልጉ ማረጋገጥ ያስፈልጋል።
ህጻናቱ ተጨማሪ ምግብ መውሰድ ከጀመሩ በሁዋላ ጡት የመጥባት ፍላጎታቸው ከቀነሰ ሌላ ምግብን ከመስጠት በፊት የጡት ወተቱን እንዲጠቡ ማድረግ ይገባል፡፡ ህጻናቱ ምንም እንኩዋን ሌላ ተጨማሪ ምግብ መውሰድ ቢጀምሩም የጡት ወተቱ ብቃት ያለውን የተሟላ ንጥረ ነገር የያዘ ምግብ መሆኑን ባለመዘንጋት ለህጻናቱ በተጨማሪነት መስጠት ያስፈልጋል፡፡
ከ12-24 ወራት፤
በዚህ ጊዜ ያለው የጡት ወተት አመጋገብ እንደ ሁኔታው ሊለያይ ይችላል፡፡ አንዳንድ ህጻናት የጡት ወተቱን በመኝታ ሰአት ማለትም ከመተኛታቸው አስቀድሞ ወይንም ጠዋት ከእንቅልፋ ቸው ሲነሱ ብቻ ሊፈልጉ ይችላሉ፡፡ አንዳንዶች ደግሞ የጡት ወተትን በቀን ውስጥ ከሚወስ ዱት ምግብ ከፍተኛውን ደረጃ እንዲይዝ ይፈልጋሉ፡፡ ለማንኛውም ህጻኑ የእናቱን ጡት ወተት መውሰድ የሚፈልገው መቼ እንደሆነ በመከታተል እና በመረዳት ለልጁ ምቹ ማድረግ ከሁሉም እናቶች ይጠበቃል፡፡
ጡትን በማለብ ወተትን መስጠት፤  
እናት በተለያዩ ምክንያቶች ከልጅዋ ልትርቅ የምትገደድ ከሆነ በተለያዩ የመርጃ መሳሪያዎች ወይንም በእጅ ጡትን በማለብ ለልጁ ወተት ማጠራቀም ይቻላል፡፡
የወሊድ ፍቃድ ተጠናቆ ወደስራ ሲገባ ወይንም ወደትምህርት ገበታ የሚመለሱ መሆኑን ሲያውቁ ጊዜው ከመድረሱ አስቀድሞ ባሉት ሳምንታት ጡት ማለብ መጀመርና ሰውነትንና አሰራሩን ማለማመድ ይቻላል። ይህ ለእናትየውም ልምምድ ለማድረግ የሚረዳ ሲሆን ህጻኑም የጡት ወተት እንዳያጡ ለማድረግ ጠቃሚ ፕሮግራም ነው፡፡
በምን ያህል መጠን ማለብ ይገባል ለሚለውን በሚመለከት መረጃው የሚጠቁመው ምንጊዜም እናትየው ከል ጅዋ ተለይታ የምትሄድ ከሆነ ህጻኑ ወተቱን ሊመገብ በሚችልበት ወይንም ማለቡ በተለመደ ሰአት በማለብ ወተቱን በጡጦ ቢያስቀምጡት ለህጻኑ ጠቃሚ ሲሆን በሌላም በኩል ሰውነት መታለብን በመልመድ ካለምንም ችግር የሚፈለገውን ያህል የጡት ወተት ሊያመነጭ ይችላል፡፡
በኤሌትሪክ ወይንም በእጅ የሚሰራ ጡት ማለቢያ ማግኘት ካልተቻለ ጡቱ በሞላ ጊዜ በእጅ አማካኝነት ጡትን ማለብ መለማመድ ጠቃሚ ነው፡፡ በእጅ ጡትን ለማለብ በመጀመሪያ ጡትን በመዳበስና በማሻሸት እንዲሁም በወተት የተወጠረ ከሆነ እንዲላላ በማድረግ በእጅ በመጨመቅ ለህጻኑ የጡት ወተት በቀላሉ ማዘጋጀት ይቻላል፡፡ ይህንን ድርጊት ካለማቋረጥ ከፈጸሙ ልጅ በተከታታይ ለ6 ወራት ካለምንም ተጨማሪ ምግብ በእናት ጡት ወተት ብቻ መቆየት ይችላል፡፡
የእናት ጡት ወተት ከታለበ በሁዋላ የሚቀመጥበት እቃ ጠቀሜታው ሲያልቅ የሚጣል መሆን የለበትም፡፡ ከጠርሙስም ይሁን ከፕላ ስቲክ የተሰራ ሆኖ ታጥቦ ጥቅም ላይ የሚውል መሆን አለበት፡፡
ስለጡት ማጥባትጡት በማጥባት ጊዜ የጡት ወተት ማምለጥ-መንስኤዎች እና የመከላከያ ምክሮች - PAMPEREDPEOPLENY.COM -  እርግዝና-አስተዳደግከጡት የታለበ ወተት ከ6-8 ሰአት ድረስ ሙቀቱ ከ77°F(ዲግሪ ፋራናይት) ወይንም ከ25°C  (ዲግሪ ሴንቲግሬድ) በላይ ባልሆነ ቤት ውስጥ ቆይቶ ከጥቅም ላይ መዋል ይችላል፡፡ ከዚህ በላይ የሚቆይ ከሆነ ግን ወደማቀዝቀዣ ውስጥ መግባት አለበት፡፡
የታለበ የእናት ጡት ወተት ቅዝቅዛቄው እስk 39°F ወይንም 4°C በሆነ ማቀዝቀዣ ውስጥ እስከ አምስት ቀን ድረስ መቆየት ይችላል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ከ3-6 ወር ድረስ ቆይቶ ለህጻኑ መስጠት ይቻላል፡፡ አንድ ጊዜ በታለበው ወተት ላይ ሌላ ወተት አልቦ መጨመር ግን አይቻልም። በማቀዝቀዣ ውስጥ ሲቀመጥም ከበሩ ላይ ሳይሆን ወደውስጥ ገባ ብሎ መሆን አለበት። ይህም የማቀዝቀ ዣው በር በተከፈተ በተዘጋ ቁጥር የሚኖረውን የቅዝቃዜ መዋዠቅ ለመቆጥጠር ሲባል ነው፡፡ ሁል ጊዜ በተለያዩ ጊዜ የታለቡትን ወተቶች ከማቀዝቀዣ ሲያስገቡ በእቃዎቹ ላይ ምልክት ማድረግ ይገባል፡፡

Read 11061 times