Saturday, 02 April 2022 12:12

እንዲያውቁ…እንዲያደርጉ…ድጋፍ ማድረግ ይገባል፡፡

Written by  ፀሐይ ተፈረደኝ ከኢሶግ
Rate this item
(0 votes)

  ‹‹…በእድሜዬ መግፋት እና በእንቅስቃሴዬ ምክንያት የማይገረሙ ሰዎች የሉም፡፡ እኔ ደግሞ እድሜዬ ገና 75 (ሰባ አምስት) ስለሆነ ለማርጀት ትንሽ ይቀረኛል ብዬ አስባለሁ፡፡ ምክንያቴ ደግሞ ጤናማ መሆኔ ነው፡፡ ታዲያ ከቤተሰቤም ይሁን ከውጭ ያሉ ሰዎች እንደዚህ ጤናማ ለመሆን አንቺ ምን ምክንያት አለሽ ብለው ይጠይቁኛል። ልጆቼ ይህንን አስተያየት ለመስጠ ትም ሆነ ለመስማት የማይፈልጉ ወይም የሚሰስቱ ቢሆንም የልጅ ልጆቼ ግን ይጠይቁኛል፡፡ እኔጋ እስከአሁን ድረስ መርሳት ፤መጉበጥ፤የእርምጃ መቀ ነስ፤የወገብ ሕመም፤የአይን መድከም የመሳሰሉት የእርጅና መገለጫዎች የሉብኝም፡፡ ታድያ ለዚህ ምክንያቱ ምንድነው ብዬ ለእራሴ ስመራመር እኔ የእናቶቼን ጡት በደንብ ጠብቼ ያደግሁኝ መሆኔ አንዱ ምክንያት ይመስለኛል፡፡ እናቶቼ ያልኩት የወለደችኝን እናቴንና በማድግበት ወቅት ለእኔ ተመድባ የነበረችውን ወተትዋን በደንብ የጠጣሁዋትን ላሜን ነው፡፡ ያቺ ላም የሞተች እለት በጣም አዝኜ ስለነበር የሌላ ላም ወተት እንድጠጣ ብጋበዝ ብጋበዝ እምቢ ብዬ እንደነበር ቤተሰቡ ሁሉ የማይረሳው ነገር ነበር፡፡ የእናቴን ጡት የጠባሁት ወንድሜ እስኪረገዝ እስከ አራት አመቴ ነበር፡፡ ዋናው የጤንነቴ እና እስከሰባ አምስት አመት እድሜዬ ጎበዝ እንድሆን መሰረት የሆነኝ ግን የእናቴን ጡት ወተት በመጥባቴ ነው ብዬ አምናለሁ። በዚያን ጊዜ ባህል ወይንም የተፈጥሮ ጉዳይ ሆኖ እንጂ እንደ አሁኑ ጡት ካላጠባችሁ የሚል ምንም ትምህርት የለም ነበር። እናቴ ግን ልጆችዋን ትወድ ስለነበር ሁላችንንም ሌላ ልጅ እስከምታረግዝ ድረስ ጡትዋን ታጠባ ነበር፡፡ ስለዚህ እናቴ ዛሬ ብትኖር ኖሮ በጣም አመሰግናት ነበር፡፡ ነገር ግን የእስዋን ውለታ ሳላውቀው ስለሞተችብኝ በጣም አዝናለሁ፡፡ እኔም የእስዋን ፈለግ ተከትዬ ለወለድኩዋቸው ልጆቼ በቻልኩት መጠን ጡቴን አጥብቻለሁ። ጉዋደኞቼ ጡት በማጥባቴ ምክንያት እየተቹኝ እኔ ግን ተወጥቼዋለሁ፡፡ እነእሱ ፎርማችን ይበላሻል፤መዘነጥ እንፈል ጋለን… ስራ ላይ ሆነን የጡት ወተታችን እንዲፈስ አንፈልግም ወዘተ… የመሳሰሉትን ምክንያቶች ሲያነሱ እኔ ግን ለሊት…ቅዳሜና እሁድ… ወደስራ ከቤት እስክወጣ…ከስራ እንደተመለስኩ… ወዘተ ባጠቃላይም ባለኝ ትርፍ ሰአት ሁሉ ጡት በማጥባት ልጆቼን አሳድጌአለሁ። እግዚአብ ሔር ይመስገን በቤታችን ምንም አይነት የጤና ችግር የለብንም፡፡…››
ስለጡት ማጥባት ልምድ ያነጋገርናቸው ወ/ሮ ታደለች ቢሻው የሰጡንን መልስ ነበር ከላይ ያነ በባችሁት፡፡ ወ/ሮ ታደለች የሁለት ሴት እና ሁለት ወንድ ልጆ እናት ናቸው፡፡ በአካባቢያቸው እጅግ በሚያስቀና ሁኔታ ማህበራዊ ኑሮን ይጋራሉ ሲል ልጃቸው ገልጾልናል፡፡ ለዚህም ነበር በአምዳችን ሀሳባቸውን እንዲያካፍሉ የጋበዝናቸው፡፡
ጡት ማጥባት ምን ያህል ጠቃሚ እንደሆነ በየጊዜው በተለያዩ መገናኛ ብዙሀን ማንበብ፤መስ ማት እና መመልከት እንደሚቻል ግልጽ ቢሆንም መረጃውን በየጊዜው ማንሳቱ ግን ጠቃሚ እንደሚሆን እሙን ነው፡፡ የአለም የጤና ድርጅት ድረገጽ ለንባብ ያበቃው ጽሁፍ Protecting, promoting and supporting በሚል እናቶች ጡት ማጥባትን እንዲያውቁ እና እንዲያደርጉ ለማስቻል ማስተማር…በተለያዩ መንገዶች ድጋፍ ማድረግ እንደሚገባ ያትታል፡፡
ይህንኑ ለመታዘብ በአንድ የማዋለጃ ሆስፒታል ተገኝተን ወላዶች ሆስፒታሉን ከመልቀቃቸው በፊት በባለሙያዎቹ የሚደረገውን እገዛ ታዝበናል፡፡ ሐኪሞቹ ፤ ነርሶቹ ሁሉ ወላዶች ለል ጃቸው ጡት ማጥባት እንዳለባቸው ይነግራሉ፡፡መናገር ብቻም ሳይሆን ይለምናሉ ማለት ይቻ ላል፡፡ አንዲት እናት የወለደችው በኦፕራሲዮን ነው፡፡ ሕመም አላት፡፡ ስለዚህ ልጅዋ ጡት እን ዲጠባ ሲነገራት እሺ ከማለት ውጭ ምንም ጥረት ስታደርግ አትታይም ፡፡ስለዚህም የህክምና ባለሙያዎቹ ቁጭ እንድትል አድርገው ጡትዋን መጨመቅ፤የመሳሰሉትን ሙከራ ሲያደርጉ ያመኛል …እምቢ…አለለቻቸው የመርፌ ሲሪንጅ አምጥተው የጡት ጫፍ እንዲወጣ ለማድረግ የተቻላቸውን ጥረት አደረጉ፡፡ እስዋ ግን ፈቃደኛ አልሆነችም፡፡ በሁዋላም ድር ጊቱን በሰውነትዋ ላይ እንድታደርገው ያመጡትን መሳሪያ ሰጥተዋት እና አባብለዋት ሄዱ፡፡ የእስዋ ውሳኔ ግን ጡጦውን ይጥባ….እኔማ አላደርገውም የሚል ነበር፡፡
አንባቢዎች…የአምዱ አዘጋጅ የታዘበችውን ነው ያካፈለቻችሁ፡፡ ለዚህ እትም ምንጭ ያደረገችው የአለም የጤና ድርጅት ስለእናት ጡት ወተት አሰጣጥ ያወጣው መረጃ የሚከተለው ነው፡፡
የእናት ጡት ወተት ልጁ ከተወለደ ከአንድ ሰአት ጀምሮ ሊሰጠው ይገባል፡፡
ጨቅላዎች ከተወለዱበት እለት ጀምሮ ለስድስት ወር ያህል ከእናት ጡት ወተት በስተቀር ምንም ተጨማሪ ምግብ ሊሰጣቸው አይገባም፡፡
ጨቅላዎች የእናት ጡት ወተት እስከ ሁለት አመት እድሜአቸው ሊሰጣቸው ይገባል፡፡
ጨቅላዎች ከተወለዱ ከስድስት ወር እድሜአቸው ጀምሮ ሌላ ተመጣጣኝ እና ጤናማ ምግብን እየተለማመዱ መቆየትና መመገብ ይገባቸዋል፡፡
እናቶች ጡት ማጥባት አንዳለባቸው እንዲያውቁ እና እንዴት ልጃቸውን መመገብ እንዳለባቸው ማስተማሩ የህጻናቱን ሕይወት ለመጠበቅ ብሎም ጤናማ ልጅን ማሳደግ የሚያስችል ነው፡፡
በአለም አቀፍ ደረጃ በከፍተኛ እና ቀጣይነት ባለው ሁኔታ የእናት ጡት ወተት ለተወለዱ ህጻናት መመገብ እየተተገበረ ሲሆን ይህም እድሜአቸው ከአምስት አመት በታች የሆኑ የህጻ ናትን ሞት በ13% ይቀንሰዋል፡፡ ለወደፊትዋ አለም እጅግ ጤናማ የሆኑና የሚጠ ቅሙ ልጆችን ለማፍራት ይረዳል፡፡
የእናት ጡት ወተት ብቻ ለ6 ወራት የጠቡ ህጻናት ለኢንፌክሽን የሚጋለጡት በጣም በጥቂቱ ነው፡፡
ለሌሎች በሽታዎች የመጋለጥ እድላቸው በጣም ትንሽ ነው፡፡ የማሰብ ሁኔታቸው የተለየ ይሆናል፡፡
በትምህርት ለከፍተኛ ውጤት የመዳረጋቸው እድል ሰፊ ነው፡፡
እናቶቻቸው ጤናማ ይሆናሉ፡፡
ጡት በማጥባት የሚገኘው ጤንነት ህብረተሰቡ በሆስፒታሎች በመሄድ እንዲያገኛቸው ለሚፈልገው የህክምና አገልግሎት እንዳይጣ በብ ጫናን ለመቀነስ ይረዳል፡፡
የተወለዱ ህጻናትን ለ6 ወራት ካለምንም ተጨማሪ ምግብ ጡት ብቻ ማጥባት ቤተሰቡ የገንዘብ እጥረት እንዳይገጥመው ያደርገዋል፡፡
ምንጫችን በስተመጨረሻ ያወጣው መረጃ የሚከተለነው፡፡
የሚያሳዝነው ይላል የአለም የጤና ድርጅት መረጃ…የሚያሳዝነው የእናት ጡት ወተትን እንደሚተኩ ተደርገው የሚተዋወቁ ነገር ግን የእናት ጡት ወተትን መተካት ቀርቶ በፍጹም ደረጃቸውን የጠበቁ ለመሆናቸው እንኩዋን ማረጋገጫ ያልተገኘላቸው ምግቦች በገበያ ላይ ስላሉ አንዳንድ እናቶችን ሊያዘናጉ ይችላሉ፡፡ ይህ ደግሞ ከምንም በላይ አደገኛነቱ ለህጻናቱ ነው፡፡ የህ ጻናቱ ጤንነት በቅርብ ጊዜም ይሁን በወደፊት እድገታቸው ላይ ችግር እንዲገጥመው ማድረጉ አይቀርም፡፡ መታወቅ ያለበት ነገር የእናት ጡት ወተትን የሚተካ ምንም አይነት ምግብ አለ መኖሩ ነው፡፡  
የአለም የጤና ድርጅት እንደሚመክረው ሀገራት ለህዝባቸው የእናት ጡት ወተትን የሚተኩ የተባሉ ምግቦችን በእናት ጡት ወተት ለመተካት እንዳይሞክሩ እና እንደ መጀመሪያ ምርጫ ተደርጎ እንዳይወሰድ እንዲመክሩ ነው፡፡ የእናት ጡት ወተትን የሚተኩ የሚሉ ማስታወቅያ ዎችም እንዳይኖሩ ማድረግ ወይንም መከላከል እንደሚገባ የአለም የጤና ድርጅት ይመክራል፡፡
(ልጅ ተወልዶ ስድስት ወር እስኪሞላው ድረስ የእናት ጡት ወተትን ብቻ መመገብ ይገባል፡፡)

Read 11078 times