Saturday, 19 March 2022 11:15

ህገ-ወጥ ልደትን ታሪክ ለማድረግ ያለመ ተግባር

Written by 
Rate this item
(0 votes)

   በተለያዩ ማህበራዊ ችግሮች ሳቢያ በአፍሪካ ተምረው መለወጥ ሰርተው ራሳቸውን መቻል አቅቷቸው ለስደት የሚዳረጉ ወገኖችን በማስተማርና የስራ ማስጀመሪያ ድጋፍ በማድረግ ራሳቸውን እንዲችሉ የሚያደርግ ላይቭ አዲስ የተሰኘ ተቋም ሰሞኑን አንድ ፕሮግምራ አዘጋጅቶ ነበር።
ፕሮግራሙ እነዚህን ከተለያዩ አካባቢዎች የተውጣጡ ከስደት የተመለሱና ለስደት ተጋላጭ የሆኑ ወጣቶችን በማሰልጠን የራሳቸውን ስራ የሚጀምሩበትን ድጋፍ የሚያደርግበት ፕሮግራም ነው።
ከአለም አቀፍ የሥራ ድርጅት (ILO) በተሰኘ የገንዘብ ድጋፍ በአዲስ አበባ ከተማ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ተግባራዊ በተደረገው በዚህ ፕሮጀክት ከሁለቱ ክፍለ ከተሞች 152 ለሚሆኑ የፕሮጀክቱ ተሳታፊዎች ስልጠናና ድጋፉ ተደርጓል።
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ መሰብሰቢያ አዳራሽ በተካሄደው በዚህ የምርቃትና የስራ ማስጀመሪያ ድጋፍ ማድረጊያ ፕሮግራም ላይ የተገኙት የአለም አቀፍ የስራ ድርጅት (ILO) ተወካይዋ አይዳ አወል እንደተናሩት ወጣቶቹ የሙያ ስልጠናና  ስራ መጀመር የሚያስችላቸውን ድጋፍ ማድረጉ በህገ-ወጥ መንገድ ለስደት የሚዳርጉ ወገኖች በአገራቸው ሰርተው መለወጥ እንደሚቻል ማሳያ ነው ብለዋል። ስልጠናና ድጋፉ ከስደት ተመላሾቹንና ለስደት ተጋላጭ ወገኖችን አቅም በመገንባት ብቁ ዜጋ ለማድረግ የሚያስችልም ነው ብለዋል።
የላይቭ አዲስ መስራችና ስራ አስኪያጅ አቶ ዓለማየሁ ተሸመ በፕሮግራሙ ላይ እንደተናገሩት የፕሮጀክቱ ተሳታፊዎች የተለያዩ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች ማለትም የሕይወት ክፍሎች፣ የጤና፣ የሰላማዊ ተግባቦትና የህገ-ወጥ ስደትን አስከፊነት የሚመለከቱ ስልጠናዎች በመሰጠትና ስራ ለመጀመር የሚያስችላቸውን ድጋፍ በማድረግ ራሳቸውን እንዲችሉ የማድረጉ ተግባር አሁንም ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል። ወጣቹ በተለያዩ ማበራዊ ችግሮች ሳቢያ ዓላማቸውን እውን ለመድረግ ሳይችሉ እንዳይቀሩ የሚቻውን ጥረት በማድረግ ከራሳቸው አልፈው ቤተሰቦቻቸውን ብሎም አገራችን የሚጠቅሙ ብቁ ዜጎች እንዲሆኑ ለማድረግ እንሰራለን ብለዋል። የፕሮጀክቱ ተሳታፊ ወጣችም በተሰጣቸው ስልጠናና በተደረገላቸው የገንዘብ ድጋፍ ታግዘው ራሳቸውን ለመለወጥ ጥረት እንደሚያደርና በአገራቸው ሰርተው መለወጥ እደሚችሉ በተሰጣቸው ስልጠና መገንዘባቸውን ተናግረዋል። ላይቭ አዲስ ለችግር በተጋለጡ ኢትዮጵያውያን ወጣቶች ህይወት ላይ ዘላቂ ለውጥ ለማምጣት ታስቦ እ.ኤ.አ ግንቦት 2005 ዓ.ም የተቋቋመ ድርጅት ነው።

Read 1698 times