Saturday, 19 March 2022 10:51

የአእምሮ ወይም የስነ ልቡና ጤና እና እርግዝና

Written by  ፀሐይ ተፈረደኝ ከኢሶግ
Rate this item
(0 votes)

  በዚህ እትም ሴቶች በእርግዝናቸው ወይንም ከወሊድ በሁዋላ ስለሚገጥማቸው የመንፈስ ጭንቀት ወይንም ድብርት እና ሊወስዱ ስለሚችሉት እርምጃ አስቀድሞ ምን ማወቅ ይገባል የሚለውን ከባለሙያ ያገኘነውን መልስ ለንባብ ብለናል፡፡ ባለሙያው ዶ/ር ያየህይራድ አየለ ከቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ናቸው፡፡  
ከወሊድ በኋላ (unipolar) ዋና ድብርት
ከወሊድ በኋላ የሚከሰት የስነልቦና ችግር ለሕፃናት ወይም ራስን ለመግደል ሙከራ የማድረግ አደጋ ቢያጋጥም ወደ ድንገተኛ የሥነ ልቦና ሐኪም መቅረብ ወይንም ሆስፒታል መተኛት ወይም የፀረ-አዕምሯዊ መድኃኒት መጀመር አስፈላጊ መሆኑን ያሳያል ፡፡
ልጅ መውለድ በተለምዶ አስደሳች ክስተት ቢሆንም ከወሊድ በኋላ ብዙ ሴቶች የመንፈስ ጭንቀት ምልክቶች እና ችግሮች ያጋጥሟቸዋል። ታካሚዎች በአጠቃላይ ከባድ የመንፈስ ጭንቀቶች ያሉባቸው ሊሆኑ ይችላሉ። ያልታከመ የድህረ ወሊድ ድብርት ለእናት እና አዲስ ለተወለዱ ሕፃናት አስከፊ መዘዞች ያስከትላል ፡፡
ጭንቀት ወይንም ድብርት (Postpartum) በሚጀምርበት ጊዜ በእርግዝና ወቅት ወይም ከወለዱ በኋላ ባሉት አራት ሳምንታት ውስጥ ላይ ይከሰታል፡፡
ለድብርት ወይንም “ከ puerperium ጋር ተያያዥነት ላላቸው ክፍሎች” የዓለም ጤና ድርጅት ዓለም አቀፍ የበሽታዎች ምደባ -10 ኛ ክለሳ ከወለዱ በኋላ ባሉት ስድስት ሳምንታት የሚከተሉት ሁኔታዎች ይስተዋላሉ ይላል ፡፡
Risk factor:- በእርግዝና ወቅት ወይም ከወለዱ በኋላ አስጨናቂ የሕይወት ክስተቶች (ለም ሳሌ፣ የጋብቻ ግጭት ወይም ፍልሰት)፤ ደካማ ማህበራዊ እና የገንዘብ ድጋፍ የመሳሰሉትን ያካትታል ፡፡
በድህረ ወሊድ ዋና የመንፈስ ጭንቀት መንስኤ ሊሆኑ የሚችሉ ምክንያቶች የሚከተሉትን ያካትታሉ፡፡
ያላገባ ወይንም ጋብቻው በትክክል ያልተፈጸመ የጋብቻ ሁኔታ፤
ከዚህ በፊት የድህረ ወሊድ ድብርት ወይም የአእምሮ ህመም የቤተሰብ ታሪክ፤
አካላዊ ወይም ወሲባዊ ጥቃት ታሪክ፤
ያልታሰበ ወይም የማይፈለግ እርግዝና፤
ለእርግዝና አሉታዊ አመለካከት፤
ጤናማ ያልሆነ የቅድመ-ወሊድ ሁኔታ ፤
(ለምሳሌ፣ በተፀነሰበት ጊዜ ከመጠን በላይ ውፍረት፣ ቅድመ ዝግጅት ማነስ፤ በእርግዝና ወቅት የስኳር በሽታ፣ የቅድመ ወሊድ ወይም የድህረ ወሊድ የደም ግፊት ፣ ወይም ከወለዱ በኋላ ኢንፌክሽን)
በእርግዝና ጊዜ የእንቅልፍ መዛባት…ወዘተ
የመንፈስ ጭንቀት ለመኖሩ የሚታዩ ምልክቶች
የተስፋ መቁረጥ ስሜት - እንደ ሀዘን፣ ተስፋ ቢስነት ፣ ተስፋ መቁረጥ፡፡
የፍላጎት ወይም የደስታ ማጣት …አንዳንድ ልምዶች ወይንም የትርፍ ጊዜ ማሳለፊያዎች እና እንቅስቃሴዎች አስደሳች የነበሩ አሁን ላይ ግን  “ከእንግዲህ ደንታ የላቸውም” ብለው ሊናገሩ ይችላሉ።
የምግብ ፍላጎት ማጣት ወይንም መጨመር …..ወይም የክብደት ለውጥ፤
የእንቅልፍ መዛባት…..ለመተኛት ችግር…..በእኩለ ሌሊት መነሳት፣ ወደ እንቅልፍ ለመመለስ መችግር… ከወትሮው ቀድሞ መነሳት እና ነቅቶ መጠበቅ (ደግሞ መትኛት አለምቻል) …. ረዘም ያለ የሌሊት እንቅልፍ፣ ወይም የቀን እንቅልፍ …ወዘተ
ድካም ወይም የኃይል ማጣት … (በቀን ላይ የማረፍ ፍላጎት ሊሰማቸው ይችላል፣ ሰውነት የመክበድ ስሜት፣ ወይም እንቅስቃሴዎችን ለመጀመር ወይም ለማጠናቀቅ ከባድ እንደሆነ ሊሰማቸው ይችላል፡፡)
የማሰብ፣ የማተኮር ወይም ውሳኔ የማድረግ ችሎታ መዳከም… አጠቃላይ የሰውነት እንቅስቃሴ፣ አስተሳሰብ ወይም ንግግር መቀዛቀዝ፡፡
ዋጋ ቢስነት ስሜት ወይም ከመጠን በላይ የጥፋተኝነት ስሜት
ራስን የማጥፋት አስተሳሰብ እና ባህሪ
በእርግዝናም ይሁን ከወሊድ በሁዋላ ድብርት ወይንም መጨነቅ የደረሰባቸው ህመምተኞች ብዙውን ጊዜ በአእምሮአቸው ሞት ወይም ራስን የማጥፋት ተደጋጋሚ ሀሳቦችን ሊመላለስባ ቸው ይችላል፡፡ ይህን በአእምሮአቸው ከማመላለስ ብዛት የራሳቸውንም ሆነ የልጃቸውን ህይወት የማጥፋት ሙከራ ሊያደርጉ ይችላሉ፡፡ ሙከራቸውን በመግፋትም የራስን ወይንም የተወለ ደውን ህጻን ሕይወት የማ ጥፋት አስተሳሰብ ተግባራዊ ሊሆን ይችላል፡፡ ይህን የሚያደርጉ ትም  ሕይወት ማለት ምንም ትርጉም የሌለው ነገር ነው ከማለት ወይንም መኖር ዋጋ ወይም ጥቅም የለውም ከሚል አስተሳሰብ ነው፡፡
ከእርግዝና በሁዋላ ወይንም ከወሊድ በሁዋላ በሚከሰት ድብርት ምንያት ከመኖር ይልቅ በሽ ተኛው ቢሞት ኖሮ የተሻለ እንደሚ ሆን በተደጋጋሚ በማሰብ የሚፈጸመው ድርጊት አደገኛ ውሳኔ ነው፡፡ በድብርት የተያዘችው ሴት ራስን በማጥፋት ሀሳብ፡ መሞት ወይም ራስን መግ ደል በመፈ ለግ ዝንባሌ የታየ ጊዜ በሽተኛውም በጠና መታመሙዋን የሚያሳይ ስለሆነ ከፍተኛ እርዳታ ያስፈልጋታል፡፡ በተጨማሪም፣ የራስን ሕይወት የማጥፋት ዕቅዶች፣ የቅድመ ዝግጅት ድርጊቶች አሉት፡፡  
ራስን ለመግደል ጊዜና ቦታ መምረጥ፣
ከፍተኛ መጠን ያለው መድኃኒት ወይም ሽጉጥ መግዛት፣
ራስን የማጥፋት ማስታወሻ መጻፍ እና ራስን የማጥፋት ሙከራዎች ሊኖሩ ይችላሉ፡፡
የስነ-ልቦና ባህሪዎች በትኩረት ካልተከታተልናቸው በቀር ብዙውን ጊዜ የተደበቁ  ናቸው። ምልክቶቹ በተደጋጋሚ የሚታዩ ሳይሆኑ ስውር ወይም ጊዜያዊ ሊሆኑ ይችላሉ፣ እናም ህመምተኞች በሌሎች ላይ ጥርጣሬ ስላሚያድርባቸው እና የአእምሮ ሕመምተኛ ተብለው እንዳይፈረጅ ስለሚፈሩ ብዙውን ጊዜ ስነልቦናቸውን ይደብቃሉ በተጨማሪም  ሀሳቦቹ ብዙውን ጊዜ ለራስ አሳማኝ ናቸው፡፡
ለምሳሌ፣ ወንጀል ሰርቻለሁ፣ ጎረቤቶቼ እየረበሹኝ ነው፣ ወይም“ ሕመም አለብኝ) …ወዘተ የሚሉትን ስሜቶች ያካትታሉ፡፡
የስነልቦና ባህሪዎች ይዘት በተለምዶ ስሜትን የሚነካ ነው፣ ማለትም ፣-
ዋጋ ቢስነት፣
ጥፋተኝነት፣
ተገቢ ቅጣት፣ ኒሂልዝም (የሚመጣ አደጋ)፤
እና ተስፋ ቢስ ከሆኑ ተስፋ አስቆራጭ ጭብጦች ጋር የሚስማማ ነው፡፡ በእርግጥ የማይ መጣጠኑ የስነ-ልቦና ባህሪዎች ከድብርት ጭብጦች ጋር በቀጥታ የተዛመዱ አይደሉም፤
ለምሳሌም፤- የአንዱን አስተሳሰብ ወደሌላው ማስገባትን ያካትታሉ (ጉዋደኛዬ በጭንቅላቴ ውስጥ ሀሳቦችን እያስገባ ነው) የሚል ሊሆን ይችላል፡፡
ሀሳብን ማሰራጨት (ሀሳቦቼን በኢንተርኔት እያሰራጨሁ ነው) የሚሉ እራስን የማሳመን ጉዳዮች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ባጠቃላይም በእርግዝና ጊዜም ይሁን ከወሊድ በሁዋላ ሊከሰት የሚችለው የድብርት ሁኔታ በቤተሰቡ የቅርብ ክትትልና ትኩረት ሊደረግትና እርዳታ የሚፈልግ መሆኑን አስቀድሞ ማወቅ ይገባል ዶ/ር ያየህይራድ ቅጣው እንደገለጹት፡፡
ከወሊድ በሁዋላ ሴቶች ከድብርት ባሻገርም ወደአእምሮ ሕመም ሊሄዱ የሚችሉበት እድል አልፎ አልፎ ይከሰታል፡፡ በሚቀጥለው እትም ዶ/ር ያየህይራድ አየለ የሰጡንን ማብራሪያ እናስነብባችሁዋለን፡፡

Read 11326 times