Print this page
Saturday, 26 February 2022 12:05

“ኢቲኸርባል” የውበት መጠበቂያ አምራች ኩባንያ አምስተኛ ዓመቱን ዛሬ ያከብራል

Written by 
Rate this item
(0 votes)

በወጣቱ ባለራዕይና ስራ ፈጣሪ ማቲዎስ መባ የዛሬ አምስት አመት የተመሰረተውና ሁለንተናዊ እድገቶችን ያስመዘገበው ኢቲኸርባል የውበት መጠበቂያ አምራች ኩባንያ፣ ዛሬ የካቲት 19 ቀን 2014 ዓ.ም ከቀኑ 10፡00 ጀምሮ በጌትፋም ሆቴል የተመሰረተበትን አምስተኛ ዓመት እንደሚያከብር ተገለጸ። የኢቲኸርቫል መስራችና ባለቤት ወጣት ማቲዎስ መባ ለአዲስ አድማስ እንደገለጹት፤”በሀገራችን አብዛኞቹ ቢዝነሶች የተመሰረቱበትን 5ኛ ዓመት ሳያከብሩ እንደሚከስሙ ጥናቶችን ጠቅሰው የገለፁ ሲሆን ኢቲኸርባል ደግሞ በሰራተኞቹ ታጋሽነትና ጥረት በሩቅ አላሚነትና በጽናት በሁለንተናዊ እድገት ድፍን ዓምስት ዓመታትን መዝለቁን ተናግረዋል።
ስኬቱን በዝርዝር ሲያስቀምጡም ኢቲኸርባል በሶስት ሰራተኞች በተከራየው ጠባብ ቦታ ሁለት ዓይነት ምርቶችን ብቻ በማምረት ስራ መጀመሩን አስታውሰው፣ በአሁኑ ወቅት ከኪራይ ወጥቶ የራሱን ቦታ ገዝቶና ፋብሪካ ገንብቶ በራሱ ዘመናዊ ማሽነሪዎች እታገዘ ለጤናና ለውበት እጅግ ተስማሚ የሆኑ የጤና፣ የቆዳና የጸጉር መንከባከቢያ ምርቶችን እያመረተ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
አቶ ማቲዎስ አክለውም ኢቲኸርባል ስራ ሲጀምር ከተፈጥሮ ዕጽዋት ሁለት አይነት ምርቶችን ያመርት እንደነበር አስታውሰው በአሁ ሰዓት ሙሉ በሙሉ የተፈጥሮ ዕጽዋቶችን በግብአትነት በመጠቀምና ሳይንሳዊ የአመራረት ሂደትን በመከተል ምርቶቹን ከ10 በላይ ከማድረሱም በላይ በ3  ሰራተኛ የተጀመረው ስራ በአሁኑ ወቅት  ከ50 በላይ ሰራተኞችንና አከፋፋዮችን ቀጥሮ ማሰራት መቻሉንና የስራ ዕድል መፍጠሩንም አቶ ማቲዎስ ተናግረዋል።
ኢቲኸርባል የተፈጥሮ ውበትና ጤና መጠበቂያ አምራች ኩባንያ በአሁኑ ወቅት በመላ ሀገሪቱ ተወደውና ተመርጠው ጥቅም ላይ የዋሉ ሲሆን ከሚመለከተው የመንግስት አካል ሁሉንም አይነት የጤናና የውበት መጠበቂያነት መስፈርት አሟልተው የተመዘገቡና እውቅናን ያገኙ ስመሆናቸውም ታውቋል።
ዛሬ በጌትፋም ሆቴል በሚካሄድ ልዩ ስነ-ስርዓት አምስተኛ የምስረታ በዓሉን ማክበር ያስፈለገበትን ዋና ዓላማ አቶ ማቲዎስ ሲገልጹ፣ ያለ ሰራተኞቹ ልፋትና ጽናት፣ ያለ አከፋፋዮቹ ብርታትና ታማኝነት፣ ያለደንበኞች እምነት እዚህ ባለመድረሳችን እነዚህን አካላት ለማመስገንና እውቅና ለመስጠት ጭምር እንደሆነም ተናግረዋል። በስነ-ስርዓቱ ላይ ኢቲኸርባል ከጅምሩ እዚህ እስኪደርስ የተጓዘበትን መንገድና ያለፋቸውን ውጣውረዶች የሚያስቃኝ አጭር ዘጋቢ ፊልም፣ የሽልማትና የእውቅና ስነ-ስርዓት፣ ለቀጣይ ከዚህ የበለጠ ተግቶ ለመስራ ቃል ኪዳን የማድረግ ስነ-ስርዓት፣ ለወጣቶች ጠቃሚ የሆነ አነቃቂ ንግግርና የእራት ግብዣ ስነ-ስርዓት ተካሂዶ መርሃ ግሩ እንደሚጠናቀቅ አቶ ማቲዎስ መባ ተናግረዋል።
ክብ (ሰርክል) ሆኖ ተያይዞ ማደግን ፍልስፍናቸው ያደረጉትን የስራ ባልደረቦቻቸውን፣ በታማኝነት በማከፋፈል ምርቶቹ ተጠቃሚ ዘንድ እንዲደርሱ ያደረጉትንና ምርቶቹን ከጅምሩ ጀምሮ በመጠቀም ያበረታቷቸውንና ገንቢ አስተያየት የሰጧቸውን ደንበኞቻቸውንም ሁሉ አመስግነዋል።  


Read 1730 times
Administrator

Latest from Administrator