Saturday, 26 February 2022 11:41

በዓለም አትሌቲክስ የቤት ውስጥ የዙር ውድድር ጉዳፍና ለሜቻ ይመራሉ

Written by  ግሩም ሠይፉ
Rate this item
(0 votes)

 ዘንድሮ ለሰባተኛ ጊዜ በሚካሄደው የዓለም አትሌቲክ የቤት ውስጥ  የዙር ውድድር ላይ ኢትዮጵያውያን  በመካከለኛ ርቀት የበላይነት እያሳዩ ናቸው፡፡  በሴቶች 1500 ሜ ደግሞ ጉዳፍ ፀጋይ እንዲሁም በወንዶች 3000ሜ ለሜቻ ግርማ ዓለምን እየመሩ ናቸው፡፡ የዓለም አትሌቲክ የቤት ውስጥ  የዙር ውድድሩ ከሳምንት በኋላ የወርቅ ደረጃ በተሰጠው ዎርልድ ኢንዶር ቱር በማድሪድ ከተማ ስፔን ላይ ይቀጥላል፡፡
የኢትዮጵያ አትሌቶች በሁሉም ደረጃዎች ከተካሄዱት በፈረንሳይ፤ በእንግሊዝና በፖላንድ በተካሄዱት የዙር ውድድሮች ባለፈው 1 ወር  ተሳትፎ ነበራቸው፡፡ በወንዶች 3000 ሜትር በሁለት ውድድሮች 20 ነጥብ አስመዝግቦ በአንደኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው ለሜቻ ግርማ ሲሆን፤ ሰለሞን ባረጋ በሁለት ውድድሮች 14 ነጥብ በማስመዝገብ ሶስተኛ ፤ በሪሁ አረጋዊ በ1 ውድድር 14 ነጥብ 4ኛ እንዲሁም ጌትነት ዋለ በ2 ውድድር 8 ነጥብ በማስመዝገብ ሰባተኛ ደረጃ ላይ ናቸው፡፡ በሴቶች ምድብ ደግሞ በተለይ በ1500 ሜትር ኢትዮጵያውያኑ ከፍተኛ የበላይነት በማሳየት ላይ ናቸው፡፡ ጉዳፍ ፀጋይ በሁለት ውድድሮች 20 ነጥብ በማስመዝገብ ስትመራ፤ አክሱማይት አምባዬ በ2 ውድድር 17 ነጥብ፤ ሂሩት መሸሻ በሁለት ውድድር 12 ነጥብ እንዲሁም ፍሬወይኒ ሃይሉ በ2 ውድድር 10 ነጥብ አስመዝግበው እስከ 4ኛ ደረጃ ተቀምጠዋል፡፡ ዳዊት ስዩም በ1 ውድድር 10 ነጥብ ይዛ 5ኛ ደረጃ ላይ ስትቀመጥ ለምለም ሃይሉ ደግሞ በ1 ውድድር 7 ነጥብ በመያዝ 7ኛ ደረጃ ላይ ናቸው፡፡
የዓለም አትሌቲክ የቤት ውስጥ የዙር ውድድር ከ6 ዓመታት በፊት በዓለም አቀፉ የአትሌቲክስ ፌደሬሽኖች ማህበር IAAF ተመስርቷል፡፡ እንደ ዓለም አትሌቲክስ የዳይመንድ ሊግ ውድድር ለቤት ውስጥ የትራክና የሜዳ ላይ ስፖርቶች የዙር ውድድሩን በየክፍለ ዓለማቱ ለማካሄድ በተያዘ እቅድ ነው፡፡ በትራክ እና በሜዳ ላይ የአትሌቲክስ ውድድሮች የዙር ውድድሩን የሚያሸንፉ አትሌቶች በተመሳሳይ የውድድር ዘመን የዙር ውድድሩ በ2016 እኤአ ላይ ለመጀመርያ ጊዜ ሲካሄድ አስተናጋጆቹ 1 የአሜሪካ እና 3 የአውሮፓ ከተሞች ናቸው፡፡  ላይ  በሚደረገው  የዓለም የቤት ውስጥ የአትሌቲክስ ሻምፒዮና ቀጥታ ተሳትፎ ያገኛሉ፡፡
ባለፉት የውድድር ዘመናት በተካሄዱት የዓለም አትሌቲክስ የቤት ውስጥ የዙር ውድድሮች  አራት ኢትዮጵያውያን አሸናፊ ሲሆኑ፤  በወንዶች ምድብ ሁለት አትሌቶች ደግሞ በሴቶች ምድብ ደግሞ 6 አትሌቶች በየውድድር መደባቸው የዙር ውድድሩን አሸናፊ ሆነዋል፡፡ በ2018 ዮሚፍ ቀጀልቻ በ3000 ሜትር፤ በ2019 ሳሙኤል ተፈራ በ1500 ሜትር፤ በ2020 ጌትነት ዋለ በ3000 ሜትር እንዲሁም  በ2021 ሰለሞን ባረጋ በ1500 ሜትር ሲያሸንፉ፤ በሴቶች ደግሞ በ2016 አክሱማዊት አምባዬ በ1500 ሜትር፤ በ2017 ገንዘቤ ዲባባ በ1500 ሜ፤ በ2019 ሃብታም አለሙ በ800 ሜ እና አልማዝ ሳሙኤል በ3000 ሜ፤ በ2020 ጉዳፍ ፀጋይ በ1500 ሜ፤ በ2021 ሃብታም አለሙ በ800 ሜ እንዲሁም ለምለም ሃይሉ በ3000 ሜ አሸናፊዎች ነበሩ፡፡ በሌላ በኩል በዓለም አትሌቲክስ የቤት ውስጥ ውድድር ከተመዘገቡ ሪከርዶች መካከል አምስቱ በኢትዮጵያውያን የተያዙ ናቸው፡፡ በወንዶች  በ1500 ሜትር  በ2019 እኤአ ላይ በበርሚንግሃም ኢንዶር ግራንድፐሪ ሳሙኤል ተፈራ 3:31.04 በሆነ ጊዜ እንዲሁም በ2021 እኤአ ላይ በ3000 ሜትር   በሌይቪን ፈረንሳይ ጌትነት ዋለ 7:24.98 በሆነ ጊዜ ያስመዘገቧቸው ናቸው፡፡  በሴቶች ደግሞ በ800 ሜትር በ2021 በቱሮን ኮፐርኒከስ ካፕ ሃብታም አለሙ 1:58.19 ፤ በ1500 ሜትር  እንዲሁም በ3000ሜ በቪላ ዲ ማዲሪድ ጉዳፍ ፀጋይ 3:53.09 እና  8:22.65 በሆኑ ጊዜዎች የውድድሩን ክብረወሰን ይዘዋል፡፡  በዓለም አትሌቲክስ የቤት ውስጥ ውድድር 3 ውድድሮች ላይ በማሸነፍ ከፍተኛውን ውጤት ያስመዘገበችው በ1500 እና በ3000 ሜትር የተሳካላት ገንዘቤ ዲባባ ናት፡፡
በ2022 እኤአ ላይ የዓለም አትሌቲክስ ማህበር የቤት ውስጥ የዙር ውድድሩን 5 አህጉራትን አፍሪካ፤ አውስትራሊያ፤ አውሮፓ፤ ሰሜንና ደቡብ አሜሪካን እንዲያካልል አድርጓል፡፡ የወርቅ፤ የብርና የነሐስ ደረጃ የተሰጣቸው 36 ውድድሮች  በመላው ዓለም የሚካሄዱ ሲሆን  የወርቅ ደረጃ  ከተሰጣቸውን 7 ውድድሮች አውሮፓ አምስቱን አሜሪካ ደግሞ ሁለቱን በከተሞቻቸው ያስተናግዳሉ፡፡ በዓለም አትሌቲክስ የቤት ውስጥ የዙር ውድድሩን የስፖርት አይነቱ በየሚያሸንፉ አትሌቶች በ2021 እኤአ ላይ 10ሺ ዶላር የቦነስ ሽልማት አግኝተዋል፡፡



Read 999 times