Monday, 24 January 2022 00:00

አንጌላ መርኬል የተመድን ሹመት አልቀበልም አሉ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

 በቅርቡ ስልጣናቸውን የለቀቁት የጀርመኗ መራሂተ መንግስት አንጌላ መርኬል፣ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬስ የቀረበላቸውን የተመድ ከፍተኛ አማካሪ ቡድን ሊቀ-መንበርነት  ሹመት አልቀበልም ማለታቸውን ደችዌሌ ዘግቧል፡፡
አንቶኒዮ ጉቴሬስ ባለፈው ሳምንት የተመድ አለማቀፍ የሸቀጦች ጉዳይ ከፍተኛ አማካሪ ቡድን ሊቀ መንበር ሆነው እንዲሰሩ ለአንጌላ መርኬል ጥሪ ማቅረባቸውን ያስታወሰው ዘገባው፣ መርኬል ግን ለሹመት በመታጨታቸው ምስጋናቸውን በማቅረብ በግል ምክንያት የተነሳ ሹመቱን እንደማይቀበሉ ማስታወቃቸውን ነው ያመለከተው፡፡
ላለፉት 16 አመታት የጀርመን መራሂተ መንግስት ሆነው ያገለገሉትና ከወራት በፊት ከሃላፊነታቸው የለቀቁት የ67 አመቷ አንጌላ መርኬል የጠቆመው ዘገባው፣  መርኬል ፖለቲካውን እርም ቢሉም በቀጣይ የጡረታ ዘመናቸውን በምን ለመግፋት እንዳሰቡ እስካሁን ምንም ፍንጭ አመለስጠታቸውን ገልጧል፡፡

Read 2077 times