Saturday, 22 January 2022 00:00

የደቡብ ሱዳን ሙርሌ ጎሳዎች በጋምቤላ በፈፀሙትጥቃት 8 ሰዎች መገደላቸው ተገለፀ

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(0 votes)

በጋምቤላ ክልል ከደቡብ ሱዳን ድንበር አሳብረው የገቡ የሙርሌ ጎሳ ታጣቂዎች ከትናንት በስቲያ ሃሙስ ድንገተኛ ጥቃት በመክፈት 8 ሰዎችን ሲገድሉ፣ 5ቱ ደግሞ መቁሰላቸውን የጋምቤላ ክልል ፕሬስ ሴክሬተሪያት በድረ ገፁ አስታውቋል፡፡ በተደጋጋሚ ወቅትና ጊዜ እየጠበቁ ጥቃት የሚሰነዝሩት የደቡብ ሱዳን የሙርሌ ታጣቂዎች፣ ሃሙስ ጥር 12 ቀን 2014 ዓ.ም በኑዌር ዞን አካቦ ወረዳ፣ በካንካን ቀበሌ ድንገተኛ ተኩስ በመክፈት ነው ጥቃቱን ያደረሱት፡፡ የክልሉ መንግስት ጥቃት አድራሾችን ተከታትሎ ለማደን ጥረት እያደረገ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን የተጠናከረ ጥበቃም እየተደረገ ነው ተብሏል፡፡ ከዚህ ቀደም እነዚሁ ታጣቂዎች በኑዌር ዞና አኙዋ ዞኖች ገብተው በርካታ ህፃናትን አፍነው መውሰዳቸውና ከአንድ መቶ ሰባ በላይ ሰዎችን መግደላቸው ይታወቃል፡፡ በወቅቱ ታፍነው ከተወሰዱ ህፃናት መካከል ከ100 በላይ የሚሆኑ በተካሄዱ ድርድሮችና በመከላከያ ሃይል ጥረት ወደ ቤተሰቦቻቸው እንዲመለሱ መደረጉ ይታወሳል፡፡

Read 3472 times