Saturday, 22 September 2012 11:29

“የዘመን ንቅሳት”

Written by  ደረጀ በላይነህ
Rate this item
(0 votes)

“የዘመን ንቅሳት”

የሚያስቁና የሚነክሱ ግጥሞች

ሁለት ዘመን ግጥሞች!

አደይ አበባ ሲፈካ፣ ዛፎች ሲደንሱ፣ ወንዙ ሲዘምር፣ ሰማይ በክዋክብት ሲነድድ… ምድረ በዳው ጌጠኛ ቀሚስ ሢያጠልቅ …. ገጣሚ ስንኝ ይቋጥራል፡፡ ድቅድቅ ባለ ምሽት ወይም በፈካ ሰማይ ብዕሩ ትባትታለች፡፡… የደራሲውም እንዲሁ!... ግለቱና ጥድፊያው ሊሳሳት ይችላል-እንጂ!

ገጣሚ እንደብረት ምጣድ መሆኑ ግን እውን ነው፡፡ሲግልም ሲቀዘቅዝም ፈጣን ነው፡፡

እኛ ሃገር ደሞ በግጥም ዓይነቶች ሳይሆን እጥረትና ርዝመት ክርክር አለ፡፡ የቀደሙት ግጥም አፍቃሪያን የአሁኖቹን “ይህቺ ምንድናት ግጥም መሆንዋ ነው”ሲሉ የአሁን አፍቃሪያን ደግሞ “ሞዛዛ!... ምንም አስደናቂ ሃሳብ የሌለው!ተደጋጋሚና አሰልቺ!” በማለት ይወርፋሉ፡፡ ረዥም አድናቂዎች የአጫጭሮቹ ችግር  የቋንቋ ወይም የቃላት አቅም ማጣት ይመስላቸዋል፡፡ አጭር ግጥም አድናቂዎች በበኩላቸው፤ “የአዲስ ሃሳብ እጦት ነው” በማለት፣ አንዱ በአንዱ ላይ ፊት ያዞራል፡፡ እንዲያውም አንድ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህር፤ አጫጭር ግጥምና አጭር ርቀት ሩጫ አይሆነንም ብለዋል፡፡ እኔ ይህንን የማይገጥም ቅዠት ነው የምለው፡፡ አጭርም ረዥምም ቢሆን አያከራክርም፤ ግን ውብ ቢሆን ጥሩ ቋንቋ፣ የላቀ ቋንቋ ቢኖረው ይመረጣል፡፡

ይሁንና በዚህ ዘመን ጎልቶ የሚታየውና የተለመደው አጫጭር ግጥም ነው፡፡…አንዳንዴ በርግጥ ረዣዥም ግጥሞች ወደ አደባባይ ይወጣሉ፡፡ ለማስታወስ ያህል የበድሉ ዋቅጅራና የሰለሞን ሽፈራው ግጥሞችን መጥቀስ ይቻላል፡፡ ነፍስ አላቸው ከሚባሉት በዚሁ ዓመት ደግሞ የዳዊት ጸጋዬ “አርነት የወጡ ሃሳቦች” የሚለው የአጫጭር ግጥሞች ስብስብ  አንባቢ ጋ ደርሷል፡፡ ዛሬ ደግሞ አንድ በጣም ረዣዥም ግጥሞችን የያዘና ቃናውም ያለፈውን ዘመን ግጥሞች የሚያስታውሰን የግጥም ስብስብ ታትሞ ወጥቷል፡፡ … “ወጣ” ተብሎ ዝም የሚባል ግን አይደለም፡፡ ነፍስ አለው፡፡

የዚህን ገጣሚ ግጥሞች አልፎ-አልፎ ሰምቻቸዋለሁ፡፡ አንዳንዶቹን ግጥሞች አሳጥሮ በቃሉ የሚያነበንብልኝ የአጫጭር ግጥሞች አፍቃሪና ገጣሚ ወዳጄ አለ፡፡ ለምሳሌ፡-ዕድሜ ጸጋውን ሳይነፍገን ሁሉን እንይ ከተባለ፣ በቦታው ላይ ሁሉም የለም፤ ካለቦታው ሁሉም አለ … የሚለው ዓይነት፡፡

ከረዣዥም ግጥሞቹ መሃል እጅግ ጥቂት ግጥሞች አሉ፤ ከነርሱ ጥቂት እወስዳለሁ፡፡ ረዥሞቹም አይቀሩም….

“ስንብት” የሚለውን ርዕስ ልውሰድ፡፡

ድውይ ያቺ የቀን መርገምት…..ቀንበጡን በጥሳ ጥላ

ከዛጎል መሃል ያለን ዕንቁ…ከዛጎል መሃል ነጥላ

ከታች መሆኑ ከፍቶታል….ከላይ ቢሆን ያምራል ብላ

ያምፖል ፈርጥ የመብራት ጌጥ….

አረገችው አንጠልጥላ፡፡

….ይህ ግጥም ተሰቅሎ ለሞተ ሰው የተጻፈ ነው የሚመስለው፡፡ ምናልባትም ለቤተዘመድ የተጻፈ ይመስላል፡፡ ያው ግጥም ስሜት ስለሚያቀጣጥል ያኔ የነደደው እሳት ወረቀት ላይ ፍም ወይም በረዶ ሆኖ ሊኖር ይችላል፡፡

ለመስፍን አሸብር መታሰቢያነት የተጻፈው”ለኛ ወይስ ለሱ”የሚል  ግጥም አድርባይነትን የሚጎነትል ይመሥላል፡፡ በዚያ ላይ በሚገባ ሣይፈካ፣ የረገፈ አበባ ነውና ያሳዝናል፡፡ ”የዘመን ንቅሳት” ገጣሚና ጋዜጠኛ መስፍንን ጥቂት ከተረከ በኋላ እርሱን ዘወር አድርጎ ራሱንና ሌሎች መሰሎቹን ይሞግታል- ገጸ ባህሪው፡፡

እንዲህ ስለ መስፍን፡-

ብዕሩን በፈለፈለ…ግብሩ ቱባ ደደረ!

ስጋው እንጂ የበደነ…ባፈር መዝጊያ የተከደነ

እሱማ ህላዌ ሆነ…እሱማ ለነፍሱ አደረ

በቀን ተሲያት ጀንበር … ብዕረኛው ሕይወት ጠምቶት

አበቅቴው ሲጠወልግ

መኖሩን ጠግቦ እንዲጠጣት…ተስፋውን እንደማሳደግ

ጅብ ከሄደ ውሻ ጮኸ …ምን ይሉታል የኛን ሽር ጉድ

ለስጋችን አጎንብሰን…ለቁም ሞታችን ስናረግድ

ለሱማ ትበቃው የለ…ለበድን ገላው ሶስት ክንድ

እሱማ ለነፍሱ አደረ

ሕይወት ወላፈኗ አቃጥሎት…ብዕሩ በታጠፈ፣ቀንበጡ

በተቀጠፈ

ቀጥፎ ማሽተት ልምድ ሆኖብን…መቃብሩ ላይ

ቆመን…ሀዘናችን ከቀለጠፈ

በወረት ከተጠለፈ

ገና እስትንፋሱ ሲከስም ነው…ሞቱ ሲሰማ ነው

ሞታችን…ገበናችንን የለፈፈ!

ተው!...ተው!...አታልቅሱ ገጣሚው ለኛ አልሞተም

የዘራው ስንኝ አልታጨደም…መኸሩ አልተከተተም

አስቀድሞ እንዳለቀስን …ቀድሞ አፈር ቢንተራስም

በብዕሩ ህይወት ዘርቷል…ለገጣሚው አናለቅስም

...እያለ ይቀጥላል፡፡ለሞተ ማልቀስ ሳይሆን ቀድሞ ሁሉን ማድረግ ነው የሚለው፡፡

አድናቆትም፤ ፍቅርም! እንደዚያ ሳናደርግ ቀርተን አታሞ ብንደልቅ ዋጋ የለውም፤ እርሱ ስራው ውስጥ ይኖራል እኛ ግን ወዮልን!!... ይመስላል፡፡ …የኛ ነገር! የዮሃንስ ግጥሞች ሁለት አይነት ጥርሶች ያሏቸው ይመስላሉ፡፡አንዳንዶቹ ይስቃሉ፤ ያስቃሉ፤ አንዳንዶቹ ልብን ይነክሳሉ፡፡ነፍስን ያኝካሉ፡፡

“ጥሎ አይጥልም”…የምትለውን ግጥሙን እንይለት

ያልሰማሁት መዓልት ያላወኩት ወራት፣ያልኖርኩት ዓመታት

ከነግስንግስ በድኔን ተሸክሞ…ሲጎተት…ሲጎተት

ድንገት ጊዜ ጥሎኝ ሲነጉድ አየሁና…ከእንቅልፌ ብነቃ

ዙሪያ ከከበበኝ…ድህነት ቀጣና…ሀዘንና መስቃ

ባሻገር አየኋት በተስፋ መቀነት…ወገቧን አጥብቃ

በደስታ ካባዋ ድርብብ ተደርብባ…ዘመን በኔ ስቃ!

ሆ! ባይ ጠማጅ አራሽ…እንደምገሽረው… እንደሰኔ መሬት

በሞት…በሞት…ምሬት ባይነውሃ ላቦት

ሰገገው ጅስሜ…ላላወኩት ስሜ…ላልኖርኩት ክራሞት

ማለፊያ ቢሆነኝ…በጊዜ ልገርፈው…ክራሬን ልቃኛ

እንዴት ነሽ ትዝታ ያበሻ መጽናኛ!

ትዝታ ብሶት፣ጥዝታ ቁጭት ነው፡፡…አንጀት ሲያኝክ ፣ነፍስ ሲቆረጥም ነው፡፡ ተስፋና ትዝታ ምስራቅና ምዕራብ ናቸው፡፡ ...ገጣሚ ዮሃንስ ገ/መድህን የቀደሙ ገጣሚያን ዓይነት አጻጻፍ ስልት የሚከተል ይመስላል፡፡ በቅርብ ከወጡ የሃገራችን ግጥሞች የሙሉጌታ ተስፋዬ፣የበድሉ ዋቅጅራ፣አሁን ደግሞ የዮሃንስ ረዘም ያሉ ናቸው፡፡ የቋንቋ አጠቃቀማቸውም ሸጋ የሚባል አይነት ነው፡፡ የበድሉ ጥቂት ረዣዥም ግጥሞች ግን እጅግ የላቀ ውበት ያላቸው ይመስለኛል፡፡ ዘይቤያዊ ድምቀታቸው አሁንም ይጣፍጠኛል!! የዮሃንስ ግጥሞችም ተስማምተዉኛል፡፡ ጥሩ ሃሳብ በቂ አገላለጥ አላቸው፡፡

ግጥሞቹን ለማሳየት ርዝመታቸው ስላስቸገረኝ አንድ የፍቅር ግጥም ልዋስና ልደምድም፡፡ …ደስ የሚለው ግን ዘመኑ አጫጭር ግጥም ቢበዛውም ረዣዝሙም ያለመጥፋቱ ነው፡፡ሁለቱም በየራሳቸው ዉብ ናቸው፡፡ ምናልባት ስለ አሜሪካ ስነጽሁፍ ብናወራ አጫጭር ግጥሞች ጸሃፊዋ ኤሚሊ ዲክንሰንና እጅግ ረዣዥም ግጥሞች ጸሃፊው ዋልት ዊትማን ሁለቱም የ19ኛው ክፍለዘመን ክዋክብት ነበሩ፡፡ ወሳኙ መርዘሙ ወይም ማጠሩ አይደለም፤ሃይሉና ውበቱ እንጂ!!

“ባይንሽ አቀብዪኝ”

ጠረንሽ  ቢርቀኝ…አቅፎኝ ብቸኝነት

አቃጥሎ ቢፈጀኝ…የእምባዬ ትኩሳት

ሸክሙን አልችል ብል…የፍቅርሽን ቅጣት

ልመና ጀመርኩኝ…ዓለሜዋ ምፅዋት

ጠንካራው መንፈሴን…ጅንን ኩሩ ልቤን

ማጤን የገራውን…አይበገር ቀልቤን

ራብ አሰከረው

ዐይኔን አንከራቶ…ደጅሽ ላይ አስቀረው፣

ላመል ኩርማን እህል…ቀልቤ የተጠየፈ

የተራበው ዐይኔ…ዓይን አይቶ ሊጠግብ

ደጅሽ ላይ አረፈ፣

ከቤትሽ አጠገብ…መንገድ ማዶ ቆሜ

የግቢሽን በራፍ…እያየሁ አግድሜ

ቃና ድምፅሽ ጠምቶኝ

ኩርማን ፍቅር ርቦኝ

ምጽዋት እያልኩኝ ነው…ባክሽ ተዘከሪኝ

ባይመችሽ እንኳ...ለምጄው ናፍቆኛል

ፍርፋሪ ፍቅር ባይንሽ አቀብዪኝ

የዚህ ግጥም አጨራረስ ትንሽ የተበላሸ ይመስላል፡፡ ታኮ የሌለው መኪና ይመስል ተንጠልጥሎ ቀርቷል፡፡ ሆን ብሎ አድርጎት ይሆናል፡፡ እኔ ግን አላስደሰተኝም፡፡ መጽሃፉ ባጠቃላይ ጥሩ ነው፡፡ ሽፋኑ ቆንጆ፣ነው፡፡ ፎንቱ የበቆሎ ፍሬ ማከሉና ግድፈቱ ያበሳጫል፡፡ ግድ የለሽነትም ይመስላል፡፡ ሆኖም ህይወትን ጥሩ አድርጎ በብዕሩ ዘልዝሏታል፡፡…

“የዘመን ንቅሳት”
የሚያስቁና የሚነክሱ ግጥሞች
ሁለት ዘመን ግጥሞች!
ደረጀ በላይነህ
አደይ አበባ ሲፈካ፣ ዛፎች ሲደንሱ፣ ወንዙ ሲዘምር፣ ሰማይ በክዋክብት ሲነድድ… ምድረ በዳው ጌጠኛ ቀሚስ ሢያጠልቅ …. ገጣሚ ስንኝ ይቋጥራል፡፡ ድቅድቅ ባለ ምሽት ወይም በፈካ ሰማይ ብዕሩ ትባትታለች፡፡… የደራሲውም እንዲሁ!... ግለቱና ጥድፊያው ሊሳሳት ይችላል-እንጂ!
ገጣሚ እንደብረት ምጣድ መሆኑ ግን እውን ነው፡፡ሲግልም ሲቀዘቅዝም ፈጣን ነው፡፡
እኛ ሃገር ደሞ በግጥም ዓይነቶች ሳይሆን እጥረትና ርዝመት ክርክር አለ፡፡ የቀደሙት ግጥም አፍቃሪያን የአሁኖቹን “ይህቺ ምንድናት ግጥም መሆንዋ ነው”ሲሉ የአሁን አፍቃሪያን ደግሞ “ሞዛዛ!... ምንም አስደናቂ ሃሳብ የሌለው!ተደጋጋሚና አሰልቺ!” በማለት ይወርፋሉ፡፡ ረዥም አድናቂዎች የአጫጭሮቹ ችግር  የቋንቋ ወይም የቃላት አቅም ማጣት ይመስላቸዋል፡፡ አጭር ግጥም አድናቂዎች በበኩላቸው፤ “የአዲስ ሃሳብ እጦት ነው” በማለት፣ አንዱ በአንዱ ላይ ፊት ያዞራል፡፡ እንዲያውም አንድ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህር፤ አጫጭር ግጥምና አጭር ርቀት ሩጫ አይሆነንም ብለዋል፡፡ እኔ ይህንን የማይገጥም ቅዠት ነው የምለው፡፡ አጭርም ረዥምም ቢሆን አያከራክርም፤ ግን ውብ ቢሆን ጥሩ ቋንቋ፣ የላቀ ቋንቋ ቢኖረው ይመረጣል፡፡
ይሁንና በዚህ ዘመን ጎልቶ የሚታየውና የተለመደው አጫጭር ግጥም ነው፡፡…አንዳንዴ በርግጥ ረዣዥም ግጥሞች ወደ አደባባይ ይወጣሉ፡፡ ለማስታወስ ያህል የበድሉ ዋቅጅራና የሰለሞን ሽፈራው ግጥሞችን መጥቀስ ይቻላል፡፡ ነፍስ አላቸው ከሚባሉት በዚሁ ዓመት ደግሞ የዳዊት ጸጋዬ “አርነት የወጡ ሃሳቦች” የሚለው የአጫጭር ግጥሞች ስብስብ  አንባቢ ጋ ደርሷል፡፡ ዛሬ ደግሞ አንድ በጣም ረዣዥም ግጥሞችን የያዘና ቃናውም ያለፈውን ዘመን ግጥሞች የሚያስታውሰን የግጥም ስብስብ ታትሞ ወጥቷል፡፡ … “ወጣ” ተብሎ ዝም የሚባል ግን አይደለም፡፡ ነፍስ አለው፡፡
የዚህን ገጣሚ ግጥሞች አልፎ-አልፎ ሰምቻቸዋለሁ፡፡ አንዳንዶቹን ግጥሞች አሳጥሮ በቃሉ የሚያነበንብልኝ የአጫጭር ግጥሞች አፍቃሪና ገጣሚ ወዳጄ አለ፡፡ ለምሳሌ፡-ዕድሜ ጸጋውን ሳይነፍገን ሁሉን እንይ ከተባለ፣ በቦታው ላይ ሁሉም የለም፤ ካለቦታው ሁሉም አለ … የሚለው ዓይነት፡፡
ከረዣዥም ግጥሞቹ መሃል እጅግ ጥቂት ግጥሞች አሉ፤ ከነርሱ ጥቂት እወስዳለሁ፡፡ ረዥሞቹም አይቀሩም….
“ስንብት” የሚለውን ርዕስ ልውሰድ፡፡
ድውይ ያቺ የቀን መርገምት…..ቀንበጡን በጥሳ ጥላ
ከዛጎል መሃል ያለን ዕንቁ…ከዛጎል መሃል ነጥላ
ከታች መሆኑ ከፍቶታል….ከላይ ቢሆን ያምራል ብላ
ያምፖል ፈርጥ የመብራት ጌጥ….
አረገችው አንጠልጥላ፡፡
….ይህ ግጥም ተሰቅሎ ለሞተ ሰው የተጻፈ ነው የሚመስለው፡፡ ምናልባትም ለቤተዘመድ የተጻፈ ይመስላል፡፡ ያው ግጥም ስሜት ስለሚያቀጣጥል ያኔ የነደደው እሳት ወረቀት ላይ ፍም ወይም በረዶ ሆኖ ሊኖር ይችላል፡፡
ለመስፍን አሸብር መታሰቢያነት የተጻፈው”ለኛ ወይስ ለሱ”የሚል  ግጥም አድርባይነትን የሚጎነትል ይመሥላል፡፡ በዚያ ላይ በሚገባ ሣይፈካ፣ የረገፈ አበባ ነውና ያሳዝናል፡፡ ”የዘመን ንቅሳት” ገጣሚና ጋዜጠኛ መስፍንን ጥቂት ከተረከ በኋላ እርሱን ዘወር አድርጎ ራሱንና ሌሎች መሰሎቹን ይሞግታል- ገጸ ባህሪው፡፡
እንዲህ ስለ መስፍን፡-
ብዕሩን በፈለፈለ…ግብሩ ቱባ ደደረ!
ስጋው እንጂ የበደነ…ባፈር መዝጊያ የተከደነ
እሱማ ህላዌ ሆነ…እሱማ ለነፍሱ አደረ
በቀን ተሲያት ጀንበር … ብዕረኛው ሕይወት ጠምቶት
አበቅቴው ሲጠወልግ
መኖሩን ጠግቦ እንዲጠጣት…ተስፋውን እንደማሳደግ
ጅብ ከሄደ ውሻ ጮኸ …ምን ይሉታል የኛን ሽር ጉድ
ለስጋችን አጎንብሰን…ለቁም ሞታችን ስናረግድ
ለሱማ ትበቃው የለ…ለበድን ገላው ሶስት ክንድ
እሱማ ለነፍሱ አደረ
ሕይወት ወላፈኗ አቃጥሎት…ብዕሩ በታጠፈ፣ቀንበጡ
በተቀጠፈ
ቀጥፎ ማሽተት ልምድ ሆኖብን…መቃብሩ ላይ
ቆመን…ሀዘናችን ከቀለጠፈ
በወረት ከተጠለፈ
ገና እስትንፋሱ ሲከስም ነው…ሞቱ ሲሰማ ነው
ሞታችን…ገበናችንን የለፈፈ!
ተው!...ተው!...አታልቅሱ ገጣሚው ለኛ አልሞተም
የዘራው ስንኝ አልታጨደም…መኸሩ አልተከተተም
አስቀድሞ እንዳለቀስን …ቀድሞ አፈር ቢንተራስም
በብዕሩ ህይወት ዘርቷል…ለገጣሚው አናለቅስም
...እያለ ይቀጥላል፡፡ለሞተ ማልቀስ ሳይሆን ቀድሞ ሁሉን ማድረግ ነው የሚለው፡፡
አድናቆትም፤ ፍቅርም! እንደዚያ ሳናደርግ ቀርተን አታሞ ብንደልቅ ዋጋ የለውም፤ እርሱ ስራው ውስጥ ይኖራል እኛ ግን ወዮልን!!... ይመስላል፡፡ …የኛ ነገር! የዮሃንስ ግጥሞች ሁለት አይነት ጥርሶች ያሏቸው ይመስላሉ፡፡አንዳንዶቹ ይስቃሉ፤ ያስቃሉ፤ አንዳንዶቹ ልብን ይነክሳሉ፡፡ነፍስን ያኝካሉ፡፡
“ጥሎ አይጥልም”…የምትለውን ግጥሙን እንይለት
ያልሰማሁት መዓልት ያላወኩት ወራት፣ያልኖርኩት ዓመታት
ከነግስንግስ በድኔን ተሸክሞ…ሲጎተት…ሲጎተት
ድንገት ጊዜ ጥሎኝ ሲነጉድ አየሁና…ከእንቅልፌ ብነቃ
ዙሪያ ከከበበኝ…ድህነት ቀጣና…ሀዘንና መስቃ
ባሻገር አየኋት በተስፋ መቀነት…ወገቧን አጥብቃ
በደስታ ካባዋ ድርብብ ተደርብባ…ዘመን በኔ ስቃ!
ሆ! ባይ ጠማጅ አራሽ…እንደምገሽረው… እንደሰኔ መሬት
በሞት…በሞት…ምሬት ባይነውሃ ላቦት
ሰገገው ጅስሜ…ላላወኩት ስሜ…ላልኖርኩት ክራሞት
ማለፊያ ቢሆነኝ…በጊዜ ልገርፈው…ክራሬን ልቃኛ
እንዴት ነሽ ትዝታ ያበሻ መጽናኛ!
ትዝታ ብሶት፣ጥዝታ ቁጭት ነው፡፡…አንጀት ሲያኝክ ፣ነፍስ ሲቆረጥም ነው፡፡ ተስፋና ትዝታ ምስራቅና ምዕራብ ናቸው፡፡ ...ገጣሚ ዮሃንስ ገ/መድህን የቀደሙ ገጣሚያን ዓይነት አጻጻፍ ስልት የሚከተል ይመስላል፡፡ በቅርብ ከወጡ የሃገራችን ግጥሞች የሙሉጌታ ተስፋዬ፣የበድሉ ዋቅጅራ፣አሁን ደግሞ የዮሃንስ ረዘም ያሉ ናቸው፡፡ የቋንቋ አጠቃቀማቸውም ሸጋ የሚባል አይነት ነው፡፡ የበድሉ ጥቂት ረዣዥም ግጥሞች ግን እጅግ የላቀ ውበት ያላቸው ይመስለኛል፡፡ ዘይቤያዊ ድምቀታቸው አሁንም ይጣፍጠኛል!! የዮሃንስ ግጥሞችም ተስማምተዉኛል፡፡ ጥሩ ሃሳብ በቂ አገላለጥ አላቸው፡፡
ግጥሞቹን ለማሳየት ርዝመታቸው ስላስቸገረኝ አንድ የፍቅር ግጥም ልዋስና ልደምድም፡፡ …ደስ የሚለው ግን ዘመኑ አጫጭር ግጥም ቢበዛውም ረዣዝሙም ያለመጥፋቱ ነው፡፡ሁለቱም በየራሳቸው ዉብ ናቸው፡፡ ምናልባት ስለ አሜሪካ ስነጽሁፍ ብናወራ አጫጭር ግጥሞች ጸሃፊዋ ኤሚሊ ዲክንሰንና እጅግ ረዣዥም ግጥሞች ጸሃፊው ዋልት ዊትማን ሁለቱም የ19ኛው ክፍለዘመን ክዋክብት ነበሩ፡፡ ወሳኙ መርዘሙ ወይም ማጠሩ አይደለም፤ሃይሉና ውበቱ እንጂ!!
“ባይንሽ አቀብዪኝ”
ጠረንሽ  ቢርቀኝ…አቅፎኝ ብቸኝነት
አቃጥሎ ቢፈጀኝ…የእምባዬ ትኩሳት
ሸክሙን አልችል ብል…የፍቅርሽን ቅጣት
ልመና ጀመርኩኝ…ዓለሜዋ ምፅዋት
ጠንካራው መንፈሴን…ጅንን ኩሩ ልቤን
ማጤን የገራውን…አይበገር ቀልቤን
ራብ አሰከረው
ዐይኔን አንከራቶ…ደጅሽ ላይ አስቀረው፣
ላመል ኩርማን እህል…ቀልቤ የተጠየፈ
የተራበው ዐይኔ…ዓይን አይቶ ሊጠግብ
ደጅሽ ላይ አረፈ፣
ከቤትሽ አጠገብ…መንገድ ማዶ ቆሜ
የግቢሽን በራፍ…እያየሁ አግድሜ
ቃና ድምፅሽ ጠምቶኝ
ኩርማን ፍቅር ርቦኝ
ምጽዋት እያልኩኝ ነው…ባክሽ ተዘከሪኝ
ባይመችሽ እንኳ...ለምጄው ናፍቆኛል
ፍርፋሪ ፍቅር ባይንሽ አቀብዪኝ
የዚህ ግጥም አጨራረስ ትንሽ የተበላሸ ይመስላል፡፡ ታኮ የሌለው መኪና ይመስል ተንጠልጥሎ ቀርቷል፡፡ ሆን ብሎ አድርጎት ይሆናል፡፡ እኔ ግን አላስደሰተኝም፡፡ መጽሃፉ ባጠቃላይ ጥሩ ነው፡፡ ሽፋኑ ቆንጆ፣ነው፡፡ ፎንቱ የበቆሎ ፍሬ ማከሉና ግድፈቱ ያበሳጫል፡፡ ግድ የለሽነትም ይመስላል፡፡ ሆኖም ህይወትን ጥሩ አድርጎ በብዕሩ ዘልዝሏታል፡፡…

Read 2259 times Last modified on Saturday, 22 September 2012 11:53