Print this page
Saturday, 18 December 2021 14:29

4ኛው የሪልእስቴት ኤግዚቢሽንና ባዛር በአዲስ አበባ ሊካሄድ ነው

Written by 
Rate this item
(3 votes)

  በኢትዮጵያ ቢያንስ 380 ሺህ መኖሪያ ቤቶት በየአመቱ መገንባት አለባቸው

            በኢትዮጵያ እየተስተዋለ ካለው ፈጣን የከተማ ልማት ጅማሮና እድገት አንፃር በየጊዜው የሚፈጠረውን የቤት ፍላጎት ለማሟላት ቢያንስ 381 ሺህ ቤቶት በየአመቱ መገንባት እንዳለባቸው ጥናቶት ይጠቁማሉ። በአሁኑ ወቅት በግል ባለሀብቶች የተያዙ ከ600 በላይ ሪልእስቴት ቢዝነሶች ያሉ ሲሆን፤ ፍላጎትን ከሞላጎደል በማሟላት ረገድም ትልቅ ሚና እየተጫወቱ ይገኛሉ፡፡
በሀገሪቱ የኮሙኒኬሽንና ማርኬቲንግ ዘርፍ ላይ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያደረገ የሚገኘው "251 ኮሙኒኬሽንና ማርኬቲንግ"ም የነዋሪውን የቤት ፍላጎት ከግምት ውስጥ በማስገባት ቤት ገንቢውና ገዢው እንዲሁም በዘርፉ የሚገኙ የተለያዩ ንግዶችና ምርቶች በአንድ ቦታ ይገናኙ ዘንድ 4ኛውን የሪልእስቴት ኤክስፖ ታህሳስ 23 እና 24 ቀን 2014 ዓ.ም ለሁለት ተከታታይ ቀናት በአዲስ አበባ ሂልተን ሆቴል ያካሂዳል፡፡  
"251 ኮሙኒኬሽንና ማርኬቲንግ" በየዓመቱ በሚያዘጋጀው በዚህ ኤግዚቢሽን፤ በርካታ ሪልእስቴቶች የገነቧቸውን ቤቶች ተመጣጣኝ በሆነ ዋጋ ይዘው እንደሚቀርቡ ታውቋል፡፡
በተጨማሪም በርካታ የግንባታ እቃ አቅራቢዎች፣ ፈርኒቸር ቤቶች፣ ቤት አስዋቢዎች እንዲሁም የቤት ማስዋቢያና ኤሌክትሮኒክስ እቃ አቅራቢዎች በአንድ ጣርያ ስር ይገናኛሉ ተብሏል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ ለመጪው የገና በዓል የተደረገውን ጥሪ ተከትሎ፣ አንድ ሚሊዮን ትውልደ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ይመለሳሉ ተብሎ ይጠበቃል። ይህም የሀገር ምርቶችንና ግንባታዎችን ለማበረታታት እንዲሁም ዘላቂ ደንበኛ ለማትረፍ ምቹ አጋጣሚን እንደሚፈጥር አዘጋጁ ጠቁሟል፡፡
ለሁለት ተከታታይ ቀናት በሚካሄደው በዚህ የሪልእስቴት ኤግዚቢሽን ላይ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት፣ የተለያዩ ባለድርሻ አካላትና በሺዎች የሚቆጠሩ ጎብኚዎች እንደሚገኙ ይጠበቃል፡፡  

Read 1748 times
Administrator

Latest from Administrator