የአልሸባብ ቃል አቀባይ አሊ መሐመድ ለኤፍፒ በሰጡት መግለጫ፤ በፕሬዚዳንት ተብዬው እና በኬኒያው የውጪ ጉዳይ ሚ/ር ላይ ለተሞከረው ግድያ ሀላፊነቱን እንወስዳለን” ያሉ ሲሆን “የምርጫ ሂደቱ ህጋዊ አይደለም፡፡ ከተመራጩ ፕሬዚዳንት ጋር ምንም አይነት የግል ቁርሾ የለንም፡፡ ነገር ግን ሂደቱ በሙሉ የጠላት ፕሮጀክት ነው” ብለዋል፡፡
ጥቃቱን ተከትሎ የአውሮፓ ህብረት የውጪ ፖሊሲ ሃላፊ ካትሪን አሽተን፤ የግድያ ሙከራው የተፈፀመው በፕሬዚዳንቱ እና በቅርቡ እየታየ ባለው የሶሚሊያ የፖለቲካ መረጋጋት ላይ ነው በማለት የግድያ ሙከራውን አውግዘዋል፡፡ “የሰኞው ሰላማዊውና ውጤታማው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ የተስፋ እና የለውጥ ጭላንጭልን ያሳየ ነበር” ብለዋል፤ካተሪን አሽተን፡፡