Saturday, 13 November 2021 14:56

ዳሽን ባንክ የቀጥታ “ሬሚታንስ” ማስተላለፊያ ቴክኒሎጂ አስተዋወቀ

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

 ዳሽን ባንክ በየትኛውም አለም የሚገኙ ዜጎች ቀጥታ ሬሚታንስ የሚያስተላፍ  “ቱንስ” (thuens) የተሰኘ አዲስ ቴክኖሎጂ አስተዋወቀ፡፡
ባንኩ  ባፈው ሀሙስ ህዳር 2 ቀን 2014 ዓ.ም ረፋድ ላይ በባንኩ የስብሰባ አዳራሽ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ፤ ቴክኖሎጂው የትኛውም ዓለም ላይ የሚገኙ ዜጎች ቱንስን በመጠቀም የሚልኩትን ገንዘብ በዳሽን ባንክ አካውንታቸው ወይም በአሞሌ ዋሌታቸው በቀጥታ ማስገባት የሚችሉበት ቀላል፣ አስተማማኝና የአገልግሎት ክፍያውም ዝቅተኛ የሆነ ዓለም አቀፍ ተቋም መሆኑን አስታውቋል፡፡
ይህ ዓለም አቀፍ ገንዘብ አስተላላፊ ተቋም እስካሁን እንደ sasai, mony trans, hello pasai እና ከሌሎችም 14 የዓለም አገራት ገንዘብ አስተላለፊዎች ጋር በጥምረት የሚሰራ ሲሆን በዱባይ፣ በእንግሊዝ፣ በአሜሪካ በሲንጋፖር፣ አሁን ደግሞ በኢትዮጵያ በድምሩ በሰባት  የዓለም አገራት ቢሮዎች እንዳሉት የቱንስ የምስራቅ አፍሪካ ተጠሪ ሚስተር ጆሴፍ በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ አብራርተዋል፡፡
የዳሽን ባንክ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አስፋው ዓለሙ በበኩላቸው፤ ኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሬ ከምታገኝባቸው መንገዶች አንዱ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ለዘመድ፣ ለወዳጅ ወይም ለግል ጉዳያቸው የሚልኩት የውጭ ምንዛሬ እንደሆነ ጠቁመው፣ በዚህም በየአመቱ ከ3-4 ቢሊዮን ዶላር ከተለያዩ የዓለም አገራት እንደሚላክ ይገመታል ብለዋል፡፡
ይህ ገንዘብ በአስተማማኝ፣በቀልጣፋና በዝቅተኛ የአገልግሎት ክፍያ አንደ ቱንስ ባሉ ቴክነሎጂዎች ሲላክና ላኪዎችም በቀጥታ ወደ ዳሽን አካውንታቸው ወይም ወደ አሞሌ ዋሌታቸው ሲያስገቡ ጠቀሜታው ብዙ መሆኑን አብራርተዋል፤ “ምንም እንኳን አገር በአስቸጋሪ ሁኔታና ጫና ውስጥ ብትሆንም ሌላውን መደበኛ ሥራ በአግባቡና በጥንካሬ መቀጠል አለበት እኛም በዚህ መልኩ ስራችንን ቀጥለን እንደ መሪ ቃላችን “ሁሌም አንድ እርምጃ ቀዳሚ” ሆነን አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን እያስተዋወቅን ነው” ብለዋል ዋና ስራ አስፈጻሚው፡፡

Read 1714 times