Saturday, 13 November 2021 12:33

ሀሰተኛ ወታደራዊ ማዕረጎችንና ወታደራዊ የደንብ ልብሶችን ሲያዘጋጁ የተገኙ በቁጥጥር ስር ዋሉ

Written by  መታሰቢያ ሳሣዬ
Rate this item
(0 votes)

   ሃሰተኛ ወታደራዊ ማዕረጎችን ጨምሮ የፌደራል ፖሊስ፣ የማረሚያ ቤቶች፣ የአፋር ክልል ልዩ ሃይል፣ የትግራይ ክልል ልዩ ሃይልና የደንብ ልብሶችን ሲያዘጋጁ የተገኙ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ፌደራል ፖሊስ አስታወቀ።
የፌደራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል ዘርፍ ኃላፊ ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል መላኩ ፈንታና አዲሰ አበባ ፖሊስ ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው  በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መሰረት በወንጀል መከላከልና ምርመራ ረገድ በተካሄደው ኦፕሬሽንና በተገኙ ውጤቶች ዙሪያ በሰጡት መግለጫ ላይ እንደተናገሩት፤ የሽብር ቡድኑ አገር የማፍረስ ዓላማውን ለማፈጸም የሚረዱትን የሸኔ፣ ቅማንትና ጉምዝ ታጣቂዎችን በማስተባበር ሽብሩን ወደ መሃል አገር ለመላክና አዲስ አበባን የሽብር መናኸሪያ ለማድረግ እየሰራ እንደሆነ ተደርሶበታል ብለዋል። ይህንኑ የሽብር ዓላማ ለማሳካትም ወደ ከተማው ውስጥ ተመሳስሎ ለመግባት ሙከራ እያደረገ መሆኑንና ለዚህ ተግባርም የሚያገለግሉትን የደንብ አልባሳት እያዘጋጀ እንደሆነ ተደርሶበታል ብለዋል።
ቡድኑ ለሽብር ተግባሩ ማስፈጸሚያ የሚሆኑ የአገር ውስጥና የውጭ አገራት ገንዘቦች፣ አሳሳች መረጃዎች፣የተለያዩ የጸጥታ አስከባሪ አካላት የደንብ ልብሶች በቁጥጥር ስር መዋላቸውንም  ጠቁመዋል፡፡

Read 1109 times