Saturday, 13 November 2021 12:28

ዌስተርን ዩኒቨርስቲ ኮሌጅ 10ኛ ዙር ተማሪዎቹን አስመረቀ

Written by 
Rate this item
(0 votes)


               ዌስተርን ዩኒቨርስቲ ኮሌጅ በመጀመሪያና በሁለተኛ ዲግሪ ያስተማራቸውን ተማሪዎች ባለፈው ቅዳሜ ለ10ኛ ጊዜ በኢሊሌ ኢንተርናሽናል ሆቴል አስመረቀ፡፡ ዩኒቨርስቲ ኮሌጁ አሜሪካ ካሊፎርኒያ ግዛት ከሚገኘው የሊንከን ዩኒቨርስቲ ጋር በመተባበር በዓይነቱ ለየት ያለ ድንበር ተሸጋሪ የድህረ ምረቃ (MBA) ፕሮግራምና በመጀመሪያ ዲግሪ በማስተማር ላይ እንደሚገኝም ታውቋል፡፡
 ዌስተርን ዩኒቨርስቲ ኮሌጅ ባለፉት አስር ዓመታት ጥራቱን የጠበቀ ትምህርት ሲሰጥ የቆየው ከአሜሪካ በሚመጡና ከፍተኛ ክህሎት እንዲሁ ተጨባጭ የስራ ልምድ ባላቸው እውቅ ፕሮፌሰሮች አማካኝነት በመደበኛ ደረጃ በክፍል ውስጥ ፊት ለፊት በሚሰጥ ትምህርት እንደሆነ በምርቃቱ እለት ንግግር ያደረጉት የዩኒቨርስቲ ኮሌጁ ፕሬዝዳንት አቶ አቤቱ መላኩ ተናግረዋል፡፡ የዩኒቨርስቲ ኮሌጁ በማስተርስ ኦፍ ቢዝነስ አድሚኒስትሬሽን (MBA)20 ተማሪዎችን መጀመሪያ ዲግሪ ደግሞ 70 በድምሩ 90 ተማሪዎችን ያስመረቀ ሲሀን፣ በትምህርት ብልጫ  ላሳዩ ተማሪዎች ሽልማትና እውቅና ሰጥቷል፡፡
በምርቃት ሥነ ስርዓቱ ላይ የትምህርት ሚኒስቴርና የሊንክን ዩኒቨርስቲ ተውካዮች፣የተማሪ ቤተሰቦችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችም  ታድመው ነበር፡

Read 802 times