Print this page
Thursday, 28 October 2021 00:00

ኤለን መስክ የመጀመሪያው ትሪሊየነር እንደሚሆኑ ይጠበቃል

Written by 
Rate this item
(0 votes)

 የወቅቱ የአለማችን ቁጥር አንድ ባለጸጋ የሆኑት አሜሪካዊው ባለሃብት ኤለን መስክ፣ ለትርፋማው ኩባንያቸው ስፔስኤክስ ምስጋና ይግባው እና በቅርቡ ሃብታቸው በከፍተኛ ሁኔታ አድጎ የአለማችን የመጀመሪያው ትሪሊየነር ሆነው ታሪክ ሊሰሩ እንደሚችሉ ተነግሯል፡፡
የታዋቂው ተቋም ሞርጋን ስቴንሊ የቢዝነስ ተንታኞች ከሰሞኑ ባወጡት መረጃ፣ የታዋቂው ኤሌክትሪክ መኪኖች አምራች ኩባንያ ባለቤት የሆኑት ቢሊየነሩ ኤለን መስክ ስፔስኤክስ በተሰኘው የጠፈር ምርምር ኩባንያቸው አማካይነት ከፍተኛ ሃብት አፍርተው ወደ ትሪሊየነርነት ሊሸጋገሩ እንደሚችሉ ይጠበቃል፡፡
በአሁኑ ወቅት 241 ቢሊዮን ዶላር የተጣራ ሃብት ያፈሩት የአለማችን ቁጥር አንድ ቢሊየነር ኤለን መስክ፣ ከዚህ ሃብታቸው ውስጥ የስፔስኤክስ ድርሻ 17 በመቶ ብቻ ቢሆንም ኩባንያው አገልግሎቱን በከፍተኛ ሁኔታ በማስፋፋትና ትርፋማነቱን በማሳደግ ላይ የሚገኝ እንደመሆኑ በአጭር ጊዜ ውስጥ ከፍተኛ ሃብት ሊያስገኝላቸው የሚችልበት ዕድል ከፍተኛ እንደሆነ ተንታኞቹ ግምታቸውን ሰጥተዋል፡፡


Read 2893 times
Administrator

Latest from Administrator