Print this page
Saturday, 23 October 2021 14:20

የዘላለም ጥግ

Written by 
Rate this item
(2 votes)

 • ሞት የህይወት ተቃራኒ አይደለም፤ የህይወት አካል እንጂ፡፡
  ሃሩኪ ሙራካሚ
• ሁላችንም እንሞታለን። ግቡ ለዘላለም መኖር አይደለም፤ ለዘላለም የሚኖር ነገር መፍጠር ነው።
  ቹክ ፓላህኒዩክ
• ህይወትን ጣፋጭ የሚያደርገው ተመልሶ የማይመጣ መሆኑ ነው።
  ኢሚሊ ዲከንሰን
• በቅጡ ለተደራጀ አዕምሮ፣ ሞት ቀጣዩ ትልቅ ጀብዱ ነው።
  ጄ.ኬ.ሮውሊንግ
• ህይወትን በጥልቀት የሚኖሩ ሰዎች ሞትን አይፈሩም።
  አናይስ ኒን
• ውጭያዊ ፅናት ያለው ሰው መሞትን ሲደፍር፤ ውስጣዊ ፅናት ያለው ሰው መኖርን ይደፍራል።
  ላኦ ትዙ
• ያለ አንዳች ጠባሳ መሞት አልፈልግም።
  ቹክ ፓላህኒዩክ
• ሞት ለወጣት የሩቅ አሉባልታ ነው።
  አንድሪው ኤ.ሩኒ
• ሰው መፍራት ያለበት ሞትን አይደለም፤ መኖር አለመጀመርን ነው።
  ማርከስ ኤዩሬሊዩስ
• መጥፋት ያለበት የመጨረሻው ጠላት ሞት ነው።
  ጄ.ኬ.ሮውሊንግ
• ሞትን መፍራት የባርነት መጀመሪያ ነው።
  ሮበርት አንቶን ዊልሰን
• ሞት ምንም ዓይነት ጉቦ አይቀበልም።
  ቤንጃሚን ፍራንክሊን
• መሞት ቀላል ነው፤ መኖር ነው እንደ ሞት የሚያስፈራኝ።
  አኒ ሌኖክስ
• ሞትን የማይፈራ ሰው አንዴ ብቻ ነው የሚሞተው።
  ጆቫኒ ፋልኮን

Read 1121 times
Administrator

Latest from Administrator