Print this page
Saturday, 23 October 2021 12:51

የዘር ተኮር ጥቃት ስጋት ባለበት የወለጋ አካባቢ የፌደራል ጸጥታ ሃይል እንዲሰማራ ኢሰመኮ ጠየቀ

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

ተደጋጋሚ ዘር ተኮር ጥቃት በሚፈፀምበት የኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋና ሆሮ ጉድሩ ወለጋ አካባቢዎች የዜጎችን ደህንነት መጠበቅ የሚችል በቂ የጸጥታ ሃይል እንዲሰማራ የኢትዮጵያ ሰበአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አሳሰበ።
ኮሚሽኑ በቅርቡ በተለይ በምስራቅ ወለጋ ኪረሙ ወረዳ የተፈጸመውን ዘር ተኮር ጥቃት አስታውሶ አሁንም በአካባቢው የተመሳሳይ ጥቃት  ስጋት መኖሩን መጠቆም የፌደራሉ መንግስት ለጉዳዩ ትኩረት እንዲሰጥ  ጠይቋል።
በተለይ ጊዳ ኪረሙ ወረዳን ጨምሮ በተለያዩ  የምስራቅ ወለጋ ወረዳዎች የሚገኙ ነዋሪዎች  በአካባቢው በቂ የፀጥታ ሃይሎች እንደ ሌሉ በመግለጽ በከፍተኛ ስጋት ውስጥ እንደሚገኙ ተገንዝቤአለሁ ብሏል- ኢሰመኮ።
በአካባቢው የሚፈጸሙ የሲቪል ሰዎች ግድያ ባህሪያቸውን በመቀየር ብሄር ተኮር እየሆኑ ጥቃቱ ለበርካቶች ህይወት መጥፋት እንደመጡ የጠቆመው ኮሚሽኑ አካባቢው የሚያስገቡ የተዘጉ መንገዶች በሙሉ በአፋጣኝ ክፍት ተደርገው የፌደራል ፀጥታ ሃይሎች ከክልሎች ጋር በመቀናጀት አካባቢውን በቋሚነት ሊቆጣጠሩ እንደሚገባም አሳስቧል።
በምስራቅ ወለጋ ያለው ዘር ተኮር ጥቃት ወደ እርስ በእርስ መጠቃቃት እርምጃ ካልተወሰደ በቀጣይ የከፋ ውጤት ሊፈጥር እንደሚችል ያስጠነቀቀው ሪፖርቱ፤ መንግስት ለጉዳዩ ከፍተኛ ትኩረት እንዲሰጥና ቅድመ መከላከል ላይ እንዲያተኩር አሳስቧል።



Read 12559 times
Administrator

Latest from Administrator