Saturday, 23 October 2021 12:39

‹ያልታደለው ጥበብ›› ዛሬ በብሄራዊ ቲያትር ይመረቃል

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

 በዳንስ ጥበብ ባለሙያው ሽፈራው ታሪኩ ቢረጋ የተዘጋጀው  ‹‹ያልታደለው ጥበብ›› የተሰኘ  አዲስ መፅሐፍ ዛሬ ከረፋዱ 4 ሰዓት ጀምሮ በብሄራዊ ቲያትር ይመረቃል፡፡
የምረቃ ስነስርዓቱ በተለያዩ ኪነ ጥበባዊ ዝግጅቶች የሚከናወን ሲሆን፤ ከእነዚህም ውስጥ  ‹ሃገሬ› እና ‹የህሊና ሙግት› የተሰኙ ሁለት የዳንስ ቅንብሮች ይገኙባቸዋል፡፡
የክብር እንግዶችም በዳንስ ጥበብ ላይ አስተያየታቸውን እንዲሰነዝሩ ይደረጋል ተብሏል፡፡
የዳንስ ጥበብ መምህርና አቀናባሪ የሆነው ሽፈራው ታሪኩ  በኮንቴምፖራሪ የዳንስ ጥበብ ውስጥ በተለይ በአራት የተለያዩ የዳንስ ስልቶች ላይ የሚሰራ ሲሆን በአገራችን ባህላዊ ውዝውዜና በአፍሪካ ባህላዊ የዳንስ ጥበቦች ከፍተኛ ልምድ አካብቷል፡፡
በዳንስ ጥበብ ዙሪያ የሚያጠነጥነው ‹‹ያልታደለው ጥበብ›› የተሰኘው የመጀመርያ መፅሃፉ መግቢያው ላይ ባሰፈረው አስተያየት ‹‹… በአገራችንና በአንዳንድ የአፍሪካ አገራት በዳንስ ጥበብ ላይ ያሉ አመላከቶችን የሚቀይርና የተሳሳቱ አመለካከቶችን የማስተካከል አቅም ያለውና ትልቅ እርማት የሚሰጥ… ዳንሰኞች በቀላሉ የዳንስን ጥበብ ምንነትንና የመደነስ ጥበብን በበቂ ሁኔታ የሚገልፅ›› ሲል ይዘቱን ገልጾታል፡፡ በ124 ገፆች የተዘጋጀውን መፅሃፍ የታተመው በአልፋ አታሚዎች ሲሆን ዋጋው 100 ብር እንደሆነ ታውቋል፡፡


Read 12811 times