Print this page
Saturday, 23 October 2021 12:37

ቢጂአይ ኢትዮጵያና አጋሩ ካርፒዲየም ጋር በጋራ ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ አደረጉ

Written by 
Rate this item
(2 votes)

  ቢጂአይ ኢትዮጵያ ከአጋሩ ካርፒዲየም ፒኤልሲ ጋር በጋራ በሰሜን ጦርነት ከሰሜን ጎንደር ዞን ለተፈናቀሉ ወገኖች ግምቱ 1.ሚ ብር የሚሆን የምግብ ድጋፍ አደረጉ። ባለፈው ሳምንት ጥቅምት 5 ቀን 2014 ዓ.ም ባህርዳር ከተማ የድጋፍ ርክክቡ የተደረገ ሲሆን ይህ ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም በቢጂአይ ኢትጵያ የማበራዊ ሃላፊነት ጉዳዮች ዘርፍ ተጠሪ የሆኑት ወ/ሪት ሜሮን ተናግረዋል።
ቢጂአይ ኢትዮጵያ ስራ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ በኢትዮጵያ ከፌደራል እስከወረዳና ቀበሌዎች የልማት ስራዎችን በመስራት፣ የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋዎች ሲከሰቱ፣ ለልማት ጥሪ ሲደረግለትም ሆነ በማንኛውም ጊዜ ፈጣን ምላሽ በመስጠት ግንባር ቀደም መሆኑን የገለፁት ሃላፊዋ፣ ዛሬም ቢሆን በጦርነቱ የተፈናቀሉ ወገኖችን ለመደገፍ የሚደረገውን ርብርብ በማገዝ  ከአጋሩ ካርፒዲየም ጋር በመተባበር 1ሚ ብር ግምት ያለው የምግብ ድጋፍ ማድረጉን ተናግረዋል። ቢጂአይ ኢትዮጵያ ይህን ድጋፍ ከማረጉ ከሁለት ሳምንታት በፊት በኮምቦልቻ ለሚገኙና ከሰሜን ወሎ በጦርነቱ ለተፈናቀሉ ወገኖች ግምቱ 1 ሚ ብር ሚሆን የብርድልብስ ድጋፍ ሲያደርግ የኮምቦልቻ ቢራ ፋብሪካ ሰራተኞች ደግሞ እኛ እያለን ወሎ አይቸገርም በሚል ከደሞዛቸው በማዋጣት ከ2.2 ሚ ብር በላይ መለገሳቸውም በዕለቱ ተገልጿል።
በባህርዳሩ የእርዳታ ርክክብ  ስነ-ስርዓትላይ የተገኙት የአማራ ክልል አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ኢያሱ መስፍን በበኩላቸው ቢጂአይ በክልሉ ለሚከሰቱ ተፈጥሯዊም ሆነ ሰው ሰራሽ አደጋዎች ፈጥኖ በመድረስ ሀገራዊ ሃላፊነቱን በመወጣት ግንባር ቀደም ከሆኑት ድርጅች አንዱ መሆኑን ገልጸው አሁንም ከአጋሩ ካርፒዲየም ጋር በመተባበር በክልሉ የተለያዩ ዞኖች እያረገ ያለው የበጎነት ተግባርም እንደሌላው ጊዜ የህዝብን ችግር ለማቅለል ከሚያደርጋቸው እንቅስቃሴዎች አንዱ በመሆኑ በተረጂዎች ስም እናመሰግናለን ብለዋል።
የቢጂአይ ኢትዮጵያ የማህበራዊ ሃላፊነት ጉዳዮች ዘርፍ ሃላፊ ወ/ሪት ሜሮን በበኩላቸው  ቢጂአይ ኢትዮጵያ ለተፈናቃዮች ድጋፍ ከማድረጉም ቀደም ብሎ ጣና ሃይቅን የወረረውን እምቦጭ የተባለ መጤ አረም ለማስወገድ በሚደረገው ዘመቻ አረሙን በከፍተኛ ሁኔታ ማጨድና  ማስወገድ የሚችል ማሽን 5.6 ሚሊዮን ብር በመመደብ በሙላት ኢንዱስትሪያል አሰርቶ ለክልሉ መንግስት ማስረከቡንና ጥቅም ላይ ማዋሉን አስታውሰው በቀጣይም ቢጂአይ በማንኛውም ወቅት የሚፈለግበትን ድጋፍ  አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።
የቢጂአይ አጋር የሆነው ካርፒዲየም ፒኤልሲ ላለፉት 20 ዓመታት በአካባቢው የቢጂአይ ምርቶችን በማከፋፈል ስራ ላይ መቆየቱም ተገልጿል።

Read 12461 times
Administrator

Latest from Administrator