Tuesday, 19 October 2021 18:22

የጥበብ ጥግ

Written by 
Rate this item
(2 votes)

• ፈጠራ ሌላ ሳይሆን ነገሮችን ማገናኘት ነው፡፡
  ስቲቭ ጆብስ
• የምቾት ቀጠና የፈጠራ ትልቁ ጠላት ነው፡፡
  ዳን ስቲቨንስ
• ፈጠራ የማድረግ ሀይል ነው፡፡
  ኤይ ዌይዌይ
• ፈጠራ ድፍረትን ይጠይቃል፡፡
  ሂነሪ ማቲሴ
• ፈጠራ ሌላ ሳይሆን ነጻ የተለቀቀ አእምሮ ነው፡፡
  ቶሪዬ ቲ. አሳይ
• ፈጠራ ተላላፊ ነው፤ አስተላልፈው፡፡
  አልበርት አንስታይን
• አሉታዊነት የፈጠራ ጠላት ነው፡፡
  ዴቪድ ሊንች
• ፈጠራ የሚመነጨው ከሀሳቦች ግጭት ነው፡፡
  ዶናቴላ ቨራሳሴ
• ፈጠራ ተሰጥኦ አይደለም፤ አመለካከት እንጂ ፡፡
  ጄኖቫ ቼን
• ብዙ ታላላቅ ፈጠራ የሚመነጨው ከገደቦች ነው፡፡
  ጊሌስ ዱሌይ
• ምንም ነገር መኮረጅ የማይፈልጉ፤ ምንም ነገር አይፈጥሩም፡፡
  ሳልቫዶር ዳሊ
• እኔ ህልም ወይም ቅዠት አልስልም፤ የራሴን እውነታ ነው የምስለው፡፡
  ፍሪዳ ካህሎ
• ሁሉም የፈጠራ ሰዎች ያልተጠበቀውን መስራት ይፈልጋሉ።
  ሄዲ ላማር
• ራስን መጠራጠር ለፈጠራ የከፋ ጠላት ነው፡፡
  ሲልቭያ ፕላዝ
• በልብህ ፍጠር፤ በአእምሮህ ደግሞ ገንባ፡፡
  ካሪስ ጃሚ


Read 1099 times