Sunday, 17 October 2021 00:00

“የበሮቹ አድማ” የተሰኘ ህጻናት መፅሀፍ ዛሬ ይመረቃል

Written by  ናፍቆት ዩሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

  በደራሲ ነፃነት ፈለቀ በአማርኛና በእንግሊዘኛ የተዘጋጀውና “የበሮቹ አድማ” የሚል ስያሜ ያለው የህጻነት የተረት መፅሀፍ ዛሬ ጥቅምት 6 ቀን 2014 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 ጀምሮ ጥቅምት 6 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ቀበና በሚገኘው “ኢትዮጵያ ሪድስ” ግቢ ይመረቃል፡፡
በእለቱ የመፅፍ ዳሰሳ፣መዝሙርና የመፅሀፉ ታሪክ በድራማ መልክ በልጆች የሚቀርብ ሲሆን የመፅፉን ዳሰሳ የሚያቀርቡት ታላቋ የህፃናት መፃሀፍት ደራሲ ሜሬ ጃፋር መሆናቸው የመፅሀፉ ደራሲ ወጣት ነፃነት ፈለቀ ለአዲስ አድማስ ገልፃለች፡፡
በዕለቱ ፕሮፌሰር ደረጀ ገብሬን ጨምሮ በርካታ ደራሲያን የስነ-ፅሁፍ አፍቃሪያን የሚገኙ ሲሆን መድረኩን ደራሲ ይታገሱ ጌትነት እንደሚያጋፍረው ተገልጿል፡፡
ደራሲ ሜሪ ፈለቀ በእንግሊዘኛ ቋንቋና ሥነ-ፅሑፍ የመጀመሪያ ዲግሪያዋን ያገኘች ሲሆን በኢዱኬሽንና ሳይኮሎጂ ሁለተኛ ዲግሪዋን በመስራት እንደምትገኝ እና፣ በአሁኑ ሰዓት የልጆችን የንባብ ባህል ለማሳደግ በሚሰራው “ኢትዮጵያ ሪድስ” የተሰኘ የበጎ አድራጎት ድርጅት ውስጥ እየሰራች እንደምትገኝ ለማወቅ ተችሏል፡፡

Read 1051 times