Monday, 20 September 2021 00:00

የአለማችን ቢሊየነሮች 3 ሺህ 204 መድረሳቸው ተነገረ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

የአለማችን ቢሊየነሮች ቁጥር ባለፈው አመት ታይቶ በማይታወቅ መጠን በከፍተኛ ሁኔታ በመጨመር 3ሺህ 204 መድረሱንና የቢሊየነሮቹ አጠቃላይ ሃብት 10 ትሪሊዮን ዶላር መድረሱን ዌልዝኤክስ የተባለው ተቋም ከሰሞኑ ባወጣው የ2021 አለማቀፍ የቢሊየነሮች ሁኔታ አመላካች ሪፖርት አስታውቋል፡፡
የቢሊየነሮች ቁጥር አምና ከነበረበት የ13.4 በመቶ ጭማሬ ማሳየቱን የጠቆመው ሪፖርቱ፣ አጠቃላይ የሃብት መጠናቸው በአንጻሩ በ5.7 በመቶ ማደጉን አመልክቷል፡፡
ከአጠቃላዩ የአለማችን ቢሊየነሮች መካከል 60 በመቶ ያህሉ በራሳቸው ጥረት ለባለጸጋነት የበቁ መሆናቸው ታውቋል፡፡ ከአለማችን አገራት መካከል በቢሊየነሮች ቁጥር ከፍተኛውን ጭማሪ ያስመዘገበቺው አሜሪካ መሆኗን የጠቆመው ሪፖርቱ፣ በዓለም ላይ ከሚገኙት ቢሊየነሮች 29 በመቶ የሚሆኑት በአሜሪካ እንደሚገኙና ቻይና በ13 በመቶ፣ ጀርመን ደግሞ በ5 በመቶ እንደሚከተሉም አክሎ ገልጧል፡፡
በሌላ ኢኮኖሚ ነክ ዜና ደግሞ፣ አለማቀፉ ብድር በፍጥነት በማደግ ወደ 300 ትሪሊዮን ዶላር መድረሱን ኢንስቲቲዩት ኦፍ ኢንተርናሽናል ፋይናንስ የተባለው ተቋም ከሰሞኑ ባወጣው ሪፖርት አስታውቋል፡፡ አለማቀፍ ብድሩ የመንግስታት፣ የግለሰቦች፣ የኩባንያዎችና የባንኮች ብድሮችን እንደሚያጠቃልል ተጠቁሟል፡፡


Read 2800 times