በኢትዮጵያ የእርሻ ልማትን ለማሻሻልና ለማስፋፋት ከፍተኛ አስተዋፅኦ አድርገዋል በማለት ጠ/ሚ መለስን ከሸለመ በኋላ፤ ከተለያዩ የአፍሪካ አገራት በእርሻና በገጠር ልማት መስኮች ከፍተኛ ስኬት አስመዝግበዋል ተብለው የተመረጡ 7 የቢዝነስ መሪዎችንና የተቋም መስራቾችን ሸልሟል።ዶ/ር እሌኒ፤ በኢትዮጵያ የእርሻ ገበያ ውስጥ በአዲስ አቅጣጫ መሰረታዊና ውጤታማ ለውጥ የሚያመጣ ስራ አከናውነዋል የሚለው ያራ ፋውንዴሽን፤ በዶ/ር እሌኒ መሪነት የተመሰረተው የኢትዮጵያ የእህል ገበያ ድርጅት በተለይ የቡና አምራች ገበሬዎች ያለ ብዙ ወጪ እንዲገበያዩ አስችሏል ብሏል። ኢትዮጵያ ውስጥ አዲስና ዘመናዊ የገበያ አሰራርን መፍጠር ፈታኝና ውስብስብ እንደነበረ ፋውንዴሽኑ ጠቅሶ፤ ዶ/ር እሌኒ ውጤታማ አሰራሮችን በመፍጠርና አዳዲስ መንገዶችን በማሳየት ስኬት አስመዝግበዋል ያለው ፋውንዴሽኑ፤ ለሌሎች የአፍሪካ አገራትም አነቃቂ አርአያ ሆነዋል በማለት ለሽልማት እንደመረጣቸው ገልጿል።በሽልማቱ እንደተደሰቱ የተናገሩት ዶ/ር እሌኒ፤ የኢትዮጵያ እህል ገበያ ድርጅት በአጭር ጊዜ ውስጥ እውቅና ማግኘቱንና ኢትዮጵያ በጥቂት አመታት ውስጥ ለሽልማት መመረጧን ጠቅሰው ጠ/ሚ መለስ ይሄን ሳያዩ ማለፋቸው ግን ይቆጫል ብለዋል። ጠ/ሚ መለስ ከያራ ፋውንዴሽን ያገኙትን ሽልማት የገጠር ሴት ተማሪዎችን ለመደገፍ እንዳበረከቱ የሚታወስ ሲሆን፤ ዶ/ር እሌኒም ሽልማታቸውን ለተመሳሳይ አላማ እንደሚያውሉት ገልፀዋል።