Tuesday, 07 September 2021 00:00

የቴሌግራም ዳውንሎድ መጠን ከ1 ቢሊዮን አለፈ

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

 ታዋቂው የመልዕክት መላላኪያ አፕሊኬሽን ቴሌግራም በመላው አለም በተጠቃሚዎች ዳውንሎድ የተደረገበት መጠን ባለፈው ሳምንት አርብ ከ1 ቢሊዮን ማለፉ ተነግሯል፡፡
አፕሊኬሽኑ በ2021 የመጀመሪያዎቹ 6 ወራት ጊዜ ውስጥ ብቻ 214.7 ሚሊዮን ጊዜ ዳውንሎድ መደረጉን ያስታወሰው ቴክ ክራንች ድረገጽ፣ ካለፈው አመት ተመሳሳይ ጊዜ ጋር ሲነጻጸር የ61 በመቶ ጭማሪ እንዳለውም አስነብቧል፡፡
እ.ኤ.አ በ2013 ለመጀመሪያ ጊዜ በአገልግሎት ላይ የዋለው ቴሌግራም እስካሁን ዳውንሎድ ከተደረገው ውስጥ 22 በመቶ ያህሉ ዳውንሎድ የተደረገው በህንድ መሆኑንና በሩስያና በኢንዶኔዥያ በብዛት ጥቅም ላይ መዋሉንም አመልክቷል፡፡
ከቴሌግራም በተጨማሪ ከ1 ቢሊዮን ጊዜ በላይ ዳውንሎድ ከተደረጉት ሌሎች 14 የወቅቱ የዘመናችን ተወዳጅ አፕሊኬሽኖች መካከልም ዋትሳፕ፣ ሜሴንጀር፣ ፌስቡክ፣ ኢንስታግራም፣ ስናፕቻት፣ ስፓቲፋይና ኔትፍሊክስ ይገኙበታል፡፡



Read 2819 times