Saturday, 28 August 2021 12:52

ለ10 ወራት በዘለቀው ጦርነት 12 አለማቀፍ የረድኤት ሰራተኞች ተገድለዋል

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(2 votes)

  የከፋ ደም መፋሰስ እያስተናገደች ባለውና ባለፉት 10 ወራት በዘለቀው ትግራይ ክልል ጦርነት እስካሁን 12 የዓለማቀፍ የረድኤት ሰራተኞች መገደላቸው ተገልጿል፡፡
በታጠቁ ሃይሎች በተፈፀሙ ጥቃቶች መገደላቸው የተገለፀው የረድኤት ሠራተኞች በውጭ ተቋማት ተቀጥረው ይሰሩ የነበሩ ኢትዮጵያውያን ጨምሮ የተለያዩ ሃገራት ዜጎች መሆናቸውን የተባበሩት መንግስታት የሠብአዊ ድጋፍ ማስተባበሪያ ፅ/ቤት መረጃ ያመለክታል፡፡
የረድኤት ሠራተኞቹ የተገደሉት በህወኃት ታጣቂዎች መሆኑ የተመለከተ ሲሆን አሁንም በረድኤት ሠራተኞች ተንቀሳቅሶ የመስራት ዋስትና አደጋ ላይ የወደቀ መሆኑ በሪፖርቱ ተካቷል፡፡
ከተገደሉት 12 የረድኤት ሠራተኞች 3ቱ የድንበር የለሽ ሃኪሞች ቡድን አባላት መሆናቸውም፣ እንዲሁም አራቱ የዳኒሽ የስደተኞች ካውንስል ሠራተኞች መሆናቸውን ተመልክቷል፡፡
በአሁኑ ወቅት በትግራይ እንዲሁም ግጭት ባለባቸው የአራቱ የወለጋ ዞኖች አከባቢ የረድኤት ሠራተኞች ደህንነታቸው ተጠብቆ መንቀሳቀስ እንደማይችሉ ያመለከተው ሪፖርቱ በዚህም በርካታ ተፈናቃዮች ተገቢውን እርዳታ እንዳያገኙ እያደረገ ነው ተብሏል፡፡
ሁሉም የግጭቱ አካላት ለረድኤት ሠራተኞች ደህንነት እንዲጠነቀቁ ተቋሙ ጥሪ አቅርቧል፡፡



Read 11451 times