Saturday, 14 August 2021 12:04

5 የዓለምና 4 የኦሎምፒክ ሪከርዶች በኢትዮጵያ ኦሎምፒያኖች

Written by  ግሩም ሠይፉ
Rate this item
(0 votes)

   ጥሩነሽ ዲባባ 6 ሜዳልያዎች (3 የወርቅና 3 የነሐስ) ቀነኒሳ በቀለ 5 ሜዳልያዎች (3 የወርቅ 1 የብርና 1 የነሐስ)

            ATHLETICS STATISTICS BOOK Games of the XXXII Olympiad Tokyo 2020 በሚል ርዕስ በ470 ገፆች የተሰናዳ ታሪካዊ ሰነድ ነው፡፡ በዚህ  ታሪካዊ መዝገብ ላይ የኢትዮጵያ ኦሎምፒያኖችን ሙሉ ዝርዝር ታሪክ በተለይ በአትሌቲክስ ዘርፍ ያለውን ማግኘት ይቻላል፡፡ ኢትዮጵያውያን በኦሎምፒክ መድረክ ልዩና አስደናቂ ሪከርዶችን በተለይ በረጅም ርቀት ሩጫ በ5ሺ፤ በ10ሺ ሜትር እና በማራቶን የኦሎምፒክ ውድድሮች አስመዝግበዋል፡፡  ETH በሚለው ምህፃረ ቃል የኢትዮጵያውያን የኦሎምፒክ ገድል ከሰነዱ ላይ እንዲህ ፈልፍዬ አቀርብላችኋለሁ፡፡
5 የዓለም ሪከርዶች በኢትዮጵያ አትሌቶች
- 3:50.07 1500 ሜትር ሴቶች ገንዘቤ ዲባባ በፈረንሳይ ሞናኮ 17 Jul 15
- 14:06.62 በ5000 ሜትር  ሴቶች ለተሰንበት ግደይ በስፔን ቫሌንሽያ 7 Oct 20
- 29:01.03 በ10,000 ሜትር ሴቶች ለተሰንበት ግደይ በሆላንድ ሄንግሎ 8 Jun 21
- 5:23.75i በ2000 ሜትር ሴቶች ኢንዶር  ገንዘቤ ዲባባ በስፔን ሳቤዴል 7 Feb 17
- 64:31 በሴቶች ግማሽ ማራቶን በራስ አል ካሃይማህ 21 Feb 20
4 የኦሎምፒክ ሪከርዶች በኢትዮጵያ ኦሎምፒያኖች
29:17.45  በኦሎምፒክ 10ሺ ሜትር ሴቶች አልማዝ አያና  በኦሎምፒክ  ሪዮ ዲጀኔሮ 12 Aug 16 (ይህ ክብረወሰን የተመዘገበው  ሁለቴ ሲሆን የለተሰንበት ከመፅደቁ በፊት የዓለም ሪከርድ ተብሎ በሰነዱ ላይ እንደሰፈረ ነው፡፡ በርቀቱ ሁለተኛው ፈጣን ሰዓት ነው፡፡)
2:23:07  በኦሎምፒክ የሴቶች ማራቶን ቲኪ ገላና በእንግሊዝ ለንደን  5 Aug 12
12:57.82 በ5000 ሜትር ወንዶች ቀነኒሳ በቀለ ቻይና ቤጂንግ 23 Aug 08
27:01.17 በ10,000 ሜትር ወንዶች ቀነኒሳ በቀለ ቻይና ቤጂንግ 17 Aug 08
በከፍተኛ ውጤት  የኢትዮጵያ የምንግዜም ምርጥ ኦሎምፒያኖች  
በስታትስቲክስ ሰነዱ ላይ በሁሉም የኦሎምፒክ ውድድሮች ለዓለማችን የምንግዜም ምርጥ ኦሎምፒያኖች በወጣው ደረጃ  በሴቶች ምድብ ጥሩነሽ ዲባባ በ6 ሜዳልያዎች (3 የወርቅና 3 የነሐስ) በ42 ነጥብ 13ኛ ደረጃ ስትይዝ ቀነኒሳ በቀለ በ5 ሜዳልያዎች (3 የወርቅ፤ 1 የብርና 1 የነሐስ) በ36 ነጥብ 23ኛ ደረጃን ከአሜሪካዎቹ ኦሎምፒያኖች ሃሪ ሂልማን፤ ዋልተር ተዌክስበሪና ጆርጅ ቦናንግ ጋር ተጋርቷል፡፡
በከፍተኛ ውጤት  የኢትዮጵያ የምንግዜም ምርጥ ኦሎምፒያን  በአራት ኦሎምፒኮች በ2004 አቴንስ፤ በ2008 ቤጂንግ፤ በ2012 ለንደንና በ2016 ሪዮ ዲጄኔሮ ላይ 6 ሜዳልያዎችን (3 የወርቅና 3 የነሐስ) የተጎናፀፈችው ጥሩነሽ ዲባባ ናት፡፡ ቀነኒሳ በቀለ በ5 ሜዳልያዎች (3 የወርቅ 1 የብርና 1 የነሐስ) ሁለተኛው ከፍተኛ ውጤት አለው፡፡


Read 1044 times