Saturday, 07 August 2021 14:12

“ሞላ ማሩ የጥረት አብነት” መፅሐፍ ለንባብ በቃ

Written by  ናፍቆት ዩሴፍ
Rate this item
(0 votes)

     የእውቁ የንድና የስራ ፈጣሪ ቀኛዝማች ሞላ ማሩን የልጅነት የእድገትና የስራ ስኬት ታሪክ የያዘው “ሞላ ማሩ የጥረት አብነት” መፅሐፍ ለንባብ በቃ”።
በእውቁ ደራሲ ብርሃኑ ሰሙ የተዘጋጀው ይኸው የህይወትና የስኬት ተሞክሮ መፅሐፍ የቀኛዝማች ሞላ ማሩን የትውልድ መንደርና ህይወት መነሻ በማድረግ የባለታሪኩን አካባቢ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ባህላዊ ጉዳዮች የዳሰሰ ነው ተብሏል። መፅሐፉ ከሊስትሮነት ተነስተው እስከ ኢንዱስትሪዎችና ፋብሪካዎች ባለቤትነት የዘለቀውን የሞላ ማሩን ህይወት፣ ለወገናቸው የፈጠሩትን የስራ እድል፣ በአገር ኢኮኖሚ ላይ ያበረከቱትን አስተዋፅኦ፣ በማህበረሰቡ ላይ የፈጠሩትን የሥራ መውደድና ማክበር ባህል ሁሉ ይዳስሳል ተብሏል።
በ1918 ተወልደው ከ40 ዓመታት በፊት በ1972 ህይወታቸው ያለፈው ቀኛዝማች ሞላ ማሩ እስዛሬም ድረስ የመጠጥ ፋብሪካቸውን ጨምሮ በስማቸው የሚጠሩ በርካታ የንግድ ድርጅቶች ቢኖሯቸውም ይህ መፅሐፍ ደግሞ ይበልጥ ህያው መታሰቢያ ሆኖ ለትውልድ እንዲተላለፍ በማሰብ መዘጋጀቱንም ልጆቻቸው ገልፀዋል። በሶስት ዋና ዋና ክፍሎች የተዘጋጀው መፅሐፉ በ232 ገፅ መቀንበቡም ታውቋል።


Read 11295 times