Saturday, 07 August 2021 13:54

በግጭትና ጦርነት ምክንያት ሆስፒታሎች በቁስለኞች ተጨናንቀዋል ተባለ

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(1 Vote)

      በኢትዮጵያ የሚገኙ አብዛኞቹ ሆስፒታሎች በጦር ቁስለኞች መጨናነቃቸውን፣ አንዳንዶቹም የህክምና ቁሳቁስ እጥረት እየጠማቸው መሆኑን አለማቀፍ የቀይ መስቀል ኮሚቴ መረጃ ያመለክታል፡፡
አለማቀፍ የቀይ መስቀል ኮሚቴ ከኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ጋር በጋራ ቁስለኞችን ተቀብለው እያስተናገዱ ለሚገኙ ሆስፒታሎች መሰረታዊ ድጋፍ እያደረገ መሆኑንም አስታውቋል፡፡
በሀገሪቱ ሰሜናዊ ክፍል ከሚደረገው ጦርነት ባሻገር በተለያዩ የሃገሪቱ አካባቢዎች የተከሰቱ ግጭቶች ከፍተኛ ሰብአዊ ጉዳት እያደረሱ መሆኑም ተመልክቷል፡፡
በርካታ ቁስለኞችን እያስተናገዱ ከሚገኙ ሆስፒታሎች መካከል በትግራይ ክልል የሚገኙት የመቀሌ ውቅሮ፣አዲግራት ፣ሽረ፣መሆኒ እና ሽራሮ ሆስፒታሎች ተጠቅሰዋል፡፡
በተመሳሳይ በአማራ ክልል የሚገኙት ሰቆጣ ፣ደባርቅ፣ወልዲያ፣ዳንግላ መርሳ ላሊበላና ጎንደር ዩኒቨርስቲ ሆስፒታሎች በቁስለኞች መጨናነቃቸው ታውቋል፡፡
በምዕራብ ወለጋ የሚገኙ ሆስፒታሎች፣ በአፋርና ሶማሌ ክልል ያሉ ሆስፒታሎችም በአሁኑ ወቅት በግጭት ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸውን ዜጎች በብዛት ተቀብለው እያስተናገዱ መሆኑን መረጃው ያመለክታል።
ዓለማቀፍ የቀይ መስቀል ኮሚቴ በተጨማሪም በጦርነትና ግጭት ውስጥ ተሳታፊ የሆኑ አካላት በሙሉ መሰረታዊ የሰብአዊ መብት ጉዳዮችን እንዲያከብሩና ንጹሀንን ከማንኛውም ጥቃት የመጠበቅ ግዴታቸውን እንዲወጡ አሳስቧል፡፡

Read 12093 times