በዶ/ር ፍቃዱ ደስታ አሪፎ የተፃፈ “የክስታኔ ጉራጌ” ጎርደና ሴራ እና ተያያዥ ባህሎች የተሰኘ የክስታኔ ጉራጌ ማህበረሰብ ላይ መሰረት ያደረገ መፅሐፍ ነሐሴ 1 ቀን 2013 ዓ.ም ከቀኑ 8 ሰዓት ጀምሮ በብሔራዊ ቴአትር ይመረቃል።
እንዲሁም እሁድ ነሐሴ 2 ቀን 2013 ዓ.ም ከቀኑ በ4፡00 ሰዓት በቡኢ ከተማ ይመረቃል። መፅሐፉ የክስታኔ ማህበረሰብ የዛሬ 800 ዓመት አካባቢ የነበረውን የፍትህና የዳኝነት ስርዓት የሚያስቃኝ ሲሆን ባህላዊ ህጉ አሁን ካለው ዘመናዊ ህግ ጋር በማያያዝ ቢሰራበት እንደሚጠቅም ያመለክታል። ሌሎችም የማህበረሰቡ ባህሎችን አካትቶ ያቀረበ ጥናታዊ መጽሐፍ ነው-ተብሏል። በምረቃ ስነ-ስራዓቱ ላይ ዶ/ር ወዳጄነህ ማህረነ፣ ዶ/ር ዓለማየሁ ግርማ ፣ ደራሲ ኃይለመለኮት መዋዕለ፣ ዶ/ር ዳንኤል ተመስገን በመፅሐፉ ዙሪያ ሃሳባቸው ያጋራሉ። በዕለቱ ሌሎች ምሁራንና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችም ይታደማሉ።
Tuesday, 03 August 2021 18:31
“የክስታኔ ጉራጌ ጎርደና ሴራና ተያያዥ ባህሎች” መፅሐፍ ይመረቃል
Written by ናፍቆት ዮሴፍ
Published in
ኪነ-ጥበባዊ ዜና