Saturday, 31 July 2021 00:00

“ሒድና” ፊልም በስከላ ተመረቀ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

 በደራሲ የምስራች ታደለ ተደርሶ በአርቲስት ቢኒያም ሽፋ የተዘጋጀው “ሒድና” ፊልም ሀምሌ 18 ቀን 2013 ኣ.ም የአባይ መነሻ በሆነው ስከላ በድምቀት ተመረቀ። ፊልሙ ከአባይ መነሻ ስከላ ጀምሮ የፊልምና የታሪክ ፍሰቱን ጠብቆ እስከ ታላቁ ህዳሴ ግድብ ሚዘልቅ ኢትዮጵያዊያን በፍቅር አንድ የሚሆኑበት ታሪክና መቼት ይዞ አዝናኝ ፊልም ነው ተብሏል።
የ1፡40 ሰዓት ርዝመት ያለው ፊልሙ ቀረፃው በሰከላ፣ ፒኮክ አባይ፣ አዲስ አበባ ቲሊሊ ባህርዳርና ሌሎችም የአባይ ገባር ወንዞች ያሉበት ቦታ ያደረገ ሲሆን በፊልሙ ላይ ካሳሁን ፍሰሀ (ማንዴላ) ችሮታው ከልካይ፣ የምስራች ታደለና ብሩክታዊት ሽመልስ የተሳተፉበት ሀገራዊ ፋይዳ ያለው ፊልም መሆኑን የፊልሙ ዳይሬክተር አርቲስት ቢኒያም ሽፋ ገልጿል።

Read 774 times