Saturday, 31 July 2021 00:00

“የራስ ፍርድ” ትርጉም መፅሀፍ ለንባብ በቃ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

በእውቁ አሜሪካዊ ደራሲ ጆን ግሪሻም “A time to kill” በሚል ርዕስ በ1989 እ.ኤ.አ ተፅፎ ለንባብ የበቃው ረጅም ልቦለድ በተርጓሚ እሸቱ ግርማ “የራስ ፍርድ” በሚል ወደ አማርኛ ተመልሶ ለንባብ በቃ።
መፅሐፉ እጅግ ልብ አንጠልጣይ፣ በጭብጥ አያያዙ፣ በታሪክ ፍሰቱና በሴራ መዋቅሩ የተዋጣት እንደሆነ የተመሰከረለት ሲሆን፣ በ29 የዓለም ቋንቋዎች ተተርጉሞ ለንባብ ከመብቃቱም በላይ ታሪኩ በፊልም የተሰራለት የወንጀልና የፍትህ ስርዓት ላይ ያተኮረ ድንቅ መፅሀፍ መሆኑም ተገልጿል። በእውነተኛ ታሪክ ላይ ተመስርቶ የተፃፈው ይሄው መፅሐፍ የሰው ልጆች መኖር ለአደጋ መጋለጥ፣ የዓለም ቅርፅ አልባነትና ውጥንቅጥ፣ የግል ስምና ክብር ከህግና ከፍትህ በላይ ማስቀመጥ፣ የሰዎች ዕብለት፣ የሃይማኖት መሪዎች ሙሰኛነት፣ የገንዘብ ወዳድነት፣ የዘረኝነት፣ ጫፍና እሱን ተከትሎ የሚመጣው የፍትህ ስርዓት መናጋትና በርካታ ጉዳዮች ተዳስሰውበታል።
ተርጓሚው ይህን ረጅም ልቦለድ በጥሩ ቋንቋ፣ ለሀገራችን አንባቢ ምቹ አድርጎና ያለውን ነባራዊ ሁኔታ ግምት ውስጥ በማስገባት አሳምሮ መተርጎሙን በሀዋሳ ዩኒቨርስቲ የቋንቋና ስነ-ጽሁፍ መምህር የሆኑት ዘመዱ ደምስስ በመፅሀፉ ጀርባ ባሰፈሩት አስተያየት ገልፀዋል። በ593 ገፅ የተመጠነው የራስ ፍርድ መፅሐፍ በ280 ብር ለገበያ ቀርቧል።

Read 831 times