የጅብ ቆዳ ገፍፈን - ከበሮ ብንወጥር፥ “እንብላው” ጩኸቱ - በተመታ ቁጥር:: ኧረ ምን ኾነናል? በሰላም ዐልጋ ላይ - በጦርነት መብረቅ - ስናልቅ ይታየናል! ምነው ሰላም ፈራን? የሚጮኸው ኹሉ - ወደ ባሩድ ሽታ - ዘውትር የሚመራን?