Saturday, 24 July 2021 00:00

ኢዜማ በምርጫው ጉዳይ ለፍ/ቤት አቤቱታ አቀረበ

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

 ኢዜማ በ28 የምርጫ ጣቢያዎች ላይ ምርጫው እንዲደገም ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ያቀረበው ማመልከቻ ተቀባይነት በማጣቱ ጉዳዩን ወደ ፍ/ቤት መውሰዱ ታውቋል፡፡
ሰኔ 14 ቀን 2013 በተካሄደው 6ኛው አገር አቀፍ ምርጫ ኢዜማ ከተወዳደረባቸው የምርጫ  ክልሎች 28 ያህሉ ላይ የተለያዩ ማጭበርበሮች ተፈፅመዋል የሚል አቤቱታ ውጤቱ  ከመገለፁ በፊት ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ማስገባቱን፣ ነገር ግን ቦርዱ የምርጫ ክልሎቹን በተመለከተ የቀረቡበትን ቅሬታዎችና ማስረጃዎች  ሳይገመግም ውሳኔ ማሳለፉ ቅሬታ እንደፈጠረበት አመልክቷል። ይህን የቦርዱን ምላሽ ተከትሎም ጉዳዩን ወደ ጠቅላይ ፍ/ቤት ለመውሰድ መገደዱን ነው ያስታወቀው፡፡
ኢዜማ ምርጫው እንዲደገም አቤቱታ ያቀረበባቸው የምርጫ ክልሎች 27 በደቡብ አንድ በጋምቤላ ክልል የሚገኙ ሲሆን ከእነዚህም አራቱ የክልል ም/ቤት ምርጫ ብቻ  የተካሄደባቸው መሆኑ ተጠቁሟል፡፡
ኢዜማ ከተወዳደረባቸው ከ4 መቶ በላይ የምርጫ ወረዳዎች በአምስቱ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ወንበር ያገኘ ሲሆን እነዚህም በደቡብ ክልል የሚገኙ የምርጫ ወረዳዎች መሆናቸው ታውቋል፡፡

Read 11143 times